
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ በክልሉ ካሉ መዋቅሮች 3ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫና ሌሎች ሽልማቶች አግኝቷል።

መምሪያው በ2016 በጀት ዓመት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ባዘጋጀው ሴክቶሪያል ጉባኤ በተለያዩ የስራ ዘርፎች የ3ኛ ደረጃ አግኝቷል።
በዚህም በክልሉ ካሉ መዋቅሮች አራት የዋንጫና የሰርተፍኬት እንዲሁም የአንድ ዴስክ-ቶፕ ኮምፒውተር በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አማካኝነት ተበርክቶላቸዋል፡፡
የመምሪያው ኃላፊ ወ/ሮ ቤተልሄም ታደሰ ባስተላለፉት መልዕክትም ይህ ውጤት የተሳካው በሁሉም ባለድርሻ አካላት በተቀናጀ የጋራ ትብብር እንደሆነና በዚህ ሂደት ተግባሩን ከላይ እስከ ታች ድረስ በባለቤትነት ሲመሩ፣ ሲያስተባብሩ፣ ሲደግፉና ሲያግዙ ለነበሩ ሁሉ አመስግነዋል።
በመጨረሻም ኃላፊዋ እንደተናገሩት ይህ እውቅና ለመምሪያው ለተሻለ ተግባር የሚያዘጋጅና መነቃቃትን የሚፈጥር በመሆኑ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከመምሪያው ማህበራዊ ድህረ-ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

