የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሴቶችና ህጻናት ጽ/ቤት

ወ/ሮ እስከዳር አሰፋ
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሴቶችና ሕፃናት ፅ/ቤት ኃላፊ
ራዕይ
በ2030 የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት በኢኮኖሚያዊ፤በማህበራዊና በፖለቲካዊ የልማት መስኮች ተሳታፊነታቸውና ተጠቃሚነታቸው ተረጋግጦ ህፃናት መብታቸው ተከብሮና ደህንነታቸው ተጠብቆ፤የፆታ እኩልነት ሰፍኖ ማየት ነው፡፡
ተልዕኮ
በወረዳ የሚገኙ ሴቶችና ህፃናት ንቅናቄ በመፍጠር እንዲያደራጁ ምቹ ሁኔታዎችን በማመቻቸትና በማጠናከር፤አቅማቸውን በማጎልበት፤በሁሉም አካላት እቅድና ፕሮግራም ውስጥ ጉያቸው እንዲካተት በማድረግ፤በመከታተልና በማስተባበር፤የህፃናትን መብትና ደህንነት በማስጠበቅ በልማት፤በሰላም በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ፡፡
- የሴቶችና ህፃናት መብቶችን ለማስከበር በቁርጠኝነት እንሰራለን፤እናስከብራለን
- የፆታ እኩልነትን ለማስፈፀም እንሰራለን፤
- በውጤት እናምናለን፤
- ግልፀኝነትን፤ተጠያቂነትን ፍትሃዊነትን እናሰፍናለን፤
- ተሳታፊነትንና ቅንጅታዊ አሰራርን እናጠናክራለን፤
ዓላማ
ዋና ዓላማ
የዚህ ዕቅድ ዓላማ ሴክተራዊ መሰረቶችንና እስትራቴጄያዊ ጉዳዮችን አበክሮ በመለየትና በቀጣይ በየደረጃዉ የሚገኙ ፈፃሚ አባላት ስትራቴጂያዊ ትስስሩን በማጠናከር ከዚህ ሴክቶሪያል ዕቅድ ስራ ሂደቶች የየራሳቸውን ድርሻ በመውሰድ ማቀድና መተግበር የሚችሉበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር
ዝርዝር ዓላማ
በሃገራችን ከድህነት ተላቃ የተረጋጋ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ስርዓት መፍጠር የሚያስችሉ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን ነድፎ ተግባራዊ በማድረጉ ባለፉት ዓመታት በሁሉም መስኮች ተከታታይነት ያለውን ዕድገት ማስመዝገብና የተረጋጋ ሰላም ማስፈን እንችላለን፡፡ በዚህም መላው ህብረተሰብ የልማትና የለውጡ ተጠቃሚ መሆን የጀመረ ሲሆን ከዞኑ አጠቃላይ ህዝብ 51.3 በመቶ ሴቶችና 54.6 በመቶ ድርሻ ያላቸው ህፃናት በዋናነት የስኬቱ ተቋዳሽ ሆነዋል፡፡ ይህንኑ ጅምር ስራ በሰፊው ማስኬድ እንዲቻልም የወረዳው መንግስት የተለያዩ ተቋማዊ አደረጃጀቶችን በመዘርጋት የሴቶችን ንቁ የልማት ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን በይበልጥ ለማረጋገጥ እንዲሁም የህፃናትን መብትና ደህንነትን ለማስጠበቅ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡
በዚህ መሰረት የሴቶችን መብትና ደህንነት በማስጠባቅ ረገድ የንብረትና የመሬት ባለቤትነትን የይዞታ የመጠቀም በሃብትና በንብረት ላይ ከወንዶች እኩል የመወሰንና የማስተዳደር መብታቸውን ህገ መንግስታዊ ዋስትና ከመስጠት ጀምሮ የሴቶች ጉዳይ ፖሊስ የሴቶች የልማትና የለውጥ ፓኬጅ፤ሌሎች ዝርዝር ህጎችንና የማስፈፀሚያ ስልቶችን በመቅረፅ የተለያዩ አደረጃጀቶችን ፈጥረው በስፋትና በተደራጀ ሁኔታ በልማቱ ተሳታፊና ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታዎችን ፈጥሯል፡፡በዚህም ብዛት ያላቸው የወረዳችን ሴቶች በልማት ህብረት፤በማህበርና በፌዴሬሽን ተደራጅተው ከወረዳ እስከ ቀበሌ ክልል ባለው እርከን ተቀናጅተው በራሳቸውና በሃገራቸው ጉዳይ በንቃት መሳተፍና መጠቀም እንዲችሉና የተዛባ የስርዓተ-ፆታ ግንኙነት በሴቶች ላይ ያሳደረውን አድሎና የመብት ጥሰት እንዲታገሉ አስችሏቸዋል.በተመሳሳይ የህፃናት መብትና ደህንነት በማስጠበቅ ረገድም መብቶቻቸውን ህገ መንግስታዊ ዋስትና እንዲኖረው ከማድረግ አልፎ የተለያዩ ዓለምአቀፍ ስምምነቶችና ድንጋጌዎችን የሃገሪቱ የህግ አካል በማድረግና ህፃናት አቀፍ የሆነ የማህበራዊ ደህንነትና ልማት ፖሊሲና ስትራቴጂዎች ተቀርፀው ተግባር ላይ እንዲውል በመደረጉ መብታቸው እየተከበረና ተሳትፎአቸው እየጎለበተ ይገኛል፡፡
ስለሆነም የተጀመረውን የህዳሴ ጉዞ ከግብ ለማድረስ የሴቶችንና ህፃናትን፣ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ ፤ማህበራዊና ስነልቦናዊ ችግሮች ደረጃ በደረጃ ለመቅረፍ እንዲቻል የወረዳው መንግስት እያካሄደ ባለው ጥረት ያገኘናቸውን መልካም ተሞክሮዎች በመቀመርና በማስፋት የነበሩብንን ጉድለቶች በማረም የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት የህፃናትን መብትና ደህንነት በላቀ ደረጃ ማሳደግና ማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ የ2ኛውን የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድን መሰረት በማድረግ 2015 በጀት አመት መነሻ እቅድ ተዘጋጅቶ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡