የደቡብ ሶዶ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት

ወ/ሮ እስከዳር ሲሳይ ኃ/ማርያም
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት ሀላፊ
ዓላማ
ዋና ዓላማ
በወረዳዉ የሚገኙ ተፈጥሮአዊ ባህላዊ እና ታሪካዊ መስህቦች በማልማት ዘላቂ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ዕድገት ማረጋገጥና ወረዳዉ ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ እንድትሆ ማድረግ
ዝርዝር ዓላማ
በወረዳዉ የሚገኙ ተፈጥሮአዊ ባህላዊ እና ታሪካዊ መስህቦች እና ቅርሶች ለምተዉ ዘላቂ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ዕድገት በማረጋገጥ ለወረዳዉ ነዋሪ ህብረተሰብ የሥራ ዕድል እና የገቢ ምንጭ ድህነትን ለማስወገድ በሚደረገዉ ጥረት ሀገራዊ ድርሻ ማበርከት እንዲሁም በወረዳዉ ቀልጣፋ ዉጤታማ እና ተደራሽ የሆነ የመንግስት የኢንፎርሜሽን ስርዓት በመገንባት መንግስትንና ህዝብን ተጠቃሚ በማድረግ አንድ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ማህበረሰብን ባህላቸዉን ለመገንባት ተፈጥሮዊ እና ባህላዊ የሆኑ ቅርሶችን ማልማት፡፡
ራዕይ
የባህል ፤ ታርክ፤ቋንቋ ፤ቅርስ ተፈጥሮ እና ሌሎች ባህላዊ እሴቶች ተጠንተዉ እና ለምተዉ ታዉቀዉ ወረዳዉ ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ሆኖ ማየት እንዲሁም በኢንፎርሜሽን የበለፀገ በሀገር ግንባታ ወሳኝ ተሳትፎ የሚያደርግ ህዝብ እና የግልጸኝነት ተጠያቂነት የዳበረ መንግስት ተገንብቶ ማየት፡
ተልዕኮ
የወረዳዉ ብሄር ብሄረሰቦች ህዝቦች የባህል የታሪክ የቋንቋ የቅርስ የተፈጥሮ እና ሌሎች ባህላዊ እሴቶች እንዲጠኑ ፤እንዲጠበቁ ፤በዘላቂነት እንዲለሙና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትን የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ በማሳደግ የቱሪስት መስቦችን በሐገሩ ዉስጥ እና በዉጭ የቱሪዝም ገበያ ለማስተዋወቅ የተቋ ሙ ተሳትፎ ማሳደግ እና ልማታዊ ተሳትፎ ማሳደግ እና የህብረተሰብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ፡፡
እሴቶች
- የህዝቡ አገልጋይነት
- የብሄረሰቦች እኩልነትን እናከብራለን
- ሰዓብዊና ዴሞክራሳያዊ መብቶችን እናስከብራለን
- ፍታሃዊነት ተጠያቂነትንና አሳታፊነትን እናረጋግጣለን
- ሙስናን እንጸየፋለን
- ተፈጥሯዊ ሀብትንና አካባቢያችንን እንከባከባለን
በዳይሬክቶሬት የሚሰጡ ዝርዝር ግቦች
- የተገልጋይ እርካታ ማሳደግ
- የህብረተሰብን ተጠቃሚነት ማሳደግ
- የሀብት ምንጮችን ማስፋፋትና የበጀት አጠቃቀም ውጤታማነት ማሻሻል
- የህብረተሰብና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎንና ቅንጅታዊ አሠራር ማጠናከር፣
- የተፈጥሮ መስህቦች ጥናት፤ ጥበቃና ልማት ማሳደግ፤
- የባህልና ታሪክ ጥናትና ልማት ማሳደግ
- የቋንቋዎች ጥናት፤ልማትና አጠቃቀም ማሳደግ፡-
- የቅርስ ጥናት፤ጥበቃና ልማት ማሳደግ
- የዘረፉን አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ብዛትና የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ ማሳደግ
- የቱሪዝም ግብይት ጥናት፤ልማትንና የቱሪዝም ፍሰትን ማሳደግ







የትኩረት መስክ
- የባህል ታሪክና ቋንቋ ጥናትና ልማት ማሳደግ
- የክስታኒኛ ቋንቋ ጥናት፤ልማትና አጠቃቀም ማሳደግ
- የተፈጥሮ መስህቦች ጥናት፤ ጥበቃና ልማት ማሳደግ፤
- የቅርስ ጥናት፤ጥበቃና ልማት ማሳደግ
- የቱሪዝም ግብይት ጥናት፤ልማትንና የቱሪዝም ፍሰትን ማሳደግ
6.የሴክተሩ አጠቃላይ ገጽታ፡ ሴክተሩ በማእከላዊ ኢትዮጲያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን በደቡብ ሶዶ ወረዳ ሶዶ ወረዳ ዉስጥ ሚገኝ ተቋም ሲሆን በዉስጡ አጠቃላይ የሚያሥፈልግ ሰዉ ሃይል 17 ሲሆን በዋና ስራ ሂደት መሸፈን ያለበት 9 የተሸፈነ 2 ወ 1 ሴ1 በዉክልና 2 የስራ ሂደት የተያዘ ሲሆን በደጋፊ የሥራ ሂደት መሸፈን ያለበት 7 የተሸፈነ 2 ወ 1 ሴ1 ሲሆን ሁለት የስራ ሂደት በዉክልና ሲሆን በድምሩም 4 የሰዉ ሃይል ይገኛል፡፡ በስሩም አንድ የፈርሻታ ቡድን ሲኖር በዉስጡ ወ 10 ሴ 20 በድምሩ 30 አባላት ያሉት ሲሆን ፣ የጎርደና ሸንጎ ስራ አስፈጻሚዎች ወ 15 አባላት አሉት ፣ የዉማኖ ሴራ ስራ አስፈጻሚዎች ወ 3 ናቸዉ፡፡ እና በሶዶ ክስታኔ በመስቀል በዓል ወቅት የሚካሄድ የወጣቶች እና የልጅ አገረዶች የመተጫጫ የአዳብና ባህል ሲኖር በዉሥጡ ለባህሉ ሊያደምቁ የሚችሉ የሙዬት ጭፈራ፣ የሙዬት ክዋኔ ፣የጉራጊኛ ጭፈራዎች እና የአጋት ዝላይ እላፊ የሰባ ጫወታ ይከናወናሉ፡፡ በወረዳ ዉስጥ የሚገኙ የተለያዩ የመስህብ ስፍራ ቦታዎች ሲኖሩ ዋሻዎች ትክል ድንጋዮች እድሜ ጠገብ ቤተ ክርስቲያናት እንዲሁም የገና ባህል ይምር ይምር (የልጅ አገረዶች) ጫወታ የአዋቂዎች የፈረስ ጉግስ ውድድር የወጣት ወንዶች( የዐንቃት ጫወታዎች) ይገኛሉ፡፡እነዚህንም በማይዳሰስ እና በሚዳሰስ የቅርስ መዝገብ ለማስመዝገብ ጽ/ቤቱ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡