የደቡብ ሶዶ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት
አቶ በላይ ወርቁ
ዋና አላማ
የወረዳችን ከተሞች የልማት ማእከል እንዲሆኑና ለሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት የጎላ አስተዋፆ እንዲያደርጉ ለማስቻል እና የከተማ ነዋሪዎች የስልጣን ባለቤትና የልማት ተጠቃሚ በመሆን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ህዝቦች የደረሱበትን የኑሮ ደረጃ ላይ እንዲደርሱ ማስቻል፡፡
ዝርዝር አላማ
- ፅዱ፣ ውብ ማራኪና ለኑሮ ተስማሚ የሆኑ ከተሞችን መፍጠር
- አረንጓዴና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገሩ ችግኞችን በከተሞች ላይ ያላቸውን ሽፋን ማሳደግ
- የነዋሪዎችን የመሰረተ–ልማት ፍላጎቶች ማሟላት
- በስራ ሂደቱ የሚሰጡ አገልግሎቶችን በበቂ መጠን ጥራትና በተቀላጠፈ ሁኔታ በማቅረብ ተገልጋዮችን ማርካት በሂደቱም በፕላን የሚመሩ ከተሞች መፍጠር ነው፡፡
- የከተሞችን ፕላን ማስጠበቅና የፕላን ጥሰቶች እንዳይከሰቱ ክትትል ማድረግ
- በከተሞች ላይ የሚኖሩ ህገወጥ የመሬት ወረራን መከላከል
- ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ቤቶችን ገንብቶ ማስተላለፍ
- የመንግስት ቤቶችን በአግባቡ ማስተዳደርና መምራት
ራዕይ
- የወረዳችን ከተሞች ለነዋሪዎቻቸው ልማትና ቀልጣፋ አገልግሎት ሚያረጋግጡ ለኑሮ አመቺና በፕላን የሚመሩ እንዲሆኑ በማድረግ የአካባቢያቸው የልማት ማእከልና የዲሞክራሲ ተምሳሌት ሆነው እርስ በእርስ ተሳስረውና አገር አቀፍ ተወዳዳሪነታቸው በማረጋገጥ በልፅገው ማየት፡፡
ተልዕኮ
- በወረዳችን የሚገነቡ ግንባታዎች ወጪ ቆጣቢና ጥራቱ የተጠበቀ፣ከተማችን በፕላን በመምራት፣ የመሬት አቅርቦት እና አስተዳደርን ግልጽ ቀልጣፋና ፍትሃዊ በማድረግ፣የቤትና መሠረተ ልማት አቅርቦት በማሳደግ፣አረንጓዴ ልማት በማረጋገጥ ከተሜነትን በማስፋፋት ክፍለ ኢኮኖሚውን ማሳደግ ነው፡፡
- የመንግስት ፖሊሲና ስትራቴጂ የዕቅዶቻችን መርሆዎች ናቸው፣
- የሰው ኃይል ካሉን ሀብቶች ሁሉ ትልቁ ሀብታችን ነው፣
- በማያቋርጥ ለውጥና መሻሻል እናምናለን
- ተገልጋዮቻችን የሕልውናችን መሠረት ናቸው!
- ቅሬታ አቅራቢዎች መካሪዎቻችን ናቸው፣
- በከተማው በሚካሄዱ የልማት ሥራዎች ላይ የከተማ ነዋሪ ህብረተሰብ የተጠናከረ ተሳትፎ እንዲኖረው የአጀንዳዎች አፈጻጸም እንዲጎለብት ማድረግ፡፡
- በህብረተሰቡ ተሳትፎ የከተሞች የተቀናጀ መሠረተ ልማት ግንባታን ለማካሄድ የከተማ ነዋሪ ህብረተሰብ በገንዘብ፣ በጉልበት፣ በቁሳቁስና በእውቀት በማሳተፍ 40 ፐርሰንት.የግብዓት አቅርቦት አስተዋፅኦ እንዲኖረው ማድረግ፡፡
- በህብረተሰቡ ተሳትፎ የተለያዩ የመሰረተ–ልማት ስራዎች ማከናወን
- የከተማ መንገድ ተደራሽነትን ማሳደግ
- የከተማ መንገድ ደህንነትን መጠበቅና ደረጃ ማሻሻል
- የከተማ መንገድ ተፋሠሥ ሥራዎች መስራት
- የከተማ መንገድ መብራት ተደረሽነት ማሳደግ
- የከተማ መጠጥ ውሀ ተደረሽነት ማሳደግ
- የከተሞች የአረንጓዴ እጽዋት ልማት ሽፋን ማሳደግ
- በከተሞች የሚመነጨው የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ሽፋን ማሰደግ፤
- በከተሞች ጽዳት እና አረንጓዴ ልማት መስክ ዜጎች የስራ ዕድል ይፈጠርላቸዋል
- ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚዉል መሬት በማዘጋጀት አቅርቦትን ማሳደግ፣
- በከተማችን የተደራጀ የመሬት መረጃ ባንክ ሥርዓት መዘርጋት
- በመሬት ላይ የሚፈጸም የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባርን ከምንጩ እንዲደርቅ ይደረጋል፡፡
- ለማ/ቤት ባለሙያዎች፣ ለበከተማ ማስፋፊያ ክልል ለሚገኙ አ/አደሮች እና ለከተማ የጣቢያ አመራሮች በመሬት የህግ ማዕቀፍ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ይሰራል
- በከተማው የመሬት ግብይቱ ግልጽ፣ቀልጣፋና ዉጤታማ የአሰራር ስርዓት እንዲኖር በማድረግ መሬት በጨረታና በምደባ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ፣
- በወረዳው ከተማ ሰነድ አልባ ይዞታዎችን በመለየት ለሰነድ አልባ ይዞታዎች ሰነድ መስጠት፣ የመሬት ሀብት ቆጠራ ማከናወን እና ጊዜያዊ የመጠቀሚያ ሰርተፍኬት እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡
- የከተሞች ፕላን ዝግጀት ክትትል ግምገማ ማድረግ፡፡
- የልማት ሠራዊት ግንባታና የለውጥ ሥራዎችን ማጠናከር
- የዘርፉን የሰው ኃይል አቅም በክህሎት ክፍተት ስልጠና ማሳደግ፣
- በቤት ልማት እና ማስተላለፍ ዙሪያ አሁን ያለውን የተገልጋይ እርካታ ማሳደግ፤
- በወረዳው ከተሞችና የገጠር ማዕከላት በተለያዩ የቤት ልማት አማራጮች የመኖሪያ ቤቶች መገንባትና ለዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር፣
- የቤት ግንባታ ግብዓቶች ተደራሽነት በማረጋገጥ የቤት ግንባታውን ሂደት ማሳለጥ፣
- የተሟላ የአሠራር ስርዓት ለመዘርጋት የህግ ማዕቀፎች ማዘጋጀትና የቤት ልማትና አስተዳደር ሥራውን በጥናት መደገፍ፣
- የዘርፈ ብዙ ጉዳዮችን ትኩረት ማሳደግ፣
- ቤት በማስተላለፍ የመንግስ ቤቶች አስተዳደር የተገልጋይ እርካታ ማሳደግ
- መንግስት ቤት ላይ የሚፈጸሙ ህገ ወጥነቶችን ለመከላከልና አሰረር ሥርዓት መዘርጋት
- የተሟላ የአሰራር ሥርዓት ለመዘርጋት የህግ ማዕቀፎች ማዘጋጀትና የቤት አስተዳደር ስራ በጥናት በማሰደገፍ የመረጃ አደረጃጀት፣ አያያዝና አጠቃቀምን ማሻሻል
- የክትትልና ድጋፍ ስርዓትን ማጠናከር፣
- የዘርፈ ብዙ ጉዳዮችን ትኩረት ማሳደግ፣
- በአገ/ት አሰጣጥ የስራ ሂደቱን ተገልጋይ ርካታ ማሳደገግ
- የአፈፃፀም ሪፖርት አዘገጃጀት በወቅቱ ለሚመለከተው ማድረስ
- ማ/ቤቶችን መደገፍ የአፈፃፀም ግብረ–መልስ መስጠት
- የበጀት አፈፃፀም ሪፖርት ማዘጋጀት የካፒታል ፕሮጀክት አፈፃፀም መከታተል
- ሪፖርት ማዘጋጀትና ማስገምገም
- የሀብት አጠቃቀም ውጤታማነት ማሳደግ
- የስርዓተ –ፆታ ተግባራት እንዲተገበር ማድረግ
የሰው ሃይል መረጃ አደረጃጀትና አያያዝ ወቅታዊነትን ማሳደገግና ሳምንታዊ የስራ እንቅስቃሴ ላይ ከየስራ ሂደቱ መወያየት
- ለኑሮ ተስማሚና ከሌሎች ከተሞች ጋር ተወዳደሪ የሆኑ ከተሞችን መገንባት
- የደቡብ ሶዶ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ፅ/ቤት በስሩ የሚገኙ ሁለት ማዘጋጃ ቤቶች (ማለትም የኬላ ከተማ ማ/ቤትና የአለም ገና ታዳጊ ማ/ቤት) ሲኖሩት ሌሎች ማዘጋጃ ቤቶችን ለመጨመር በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡አሁን ላይ የደቡብ ሶዶ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ፅ/ቤት አንድ ዋና የቢሮ ኃላፊ ሶስት ምክትል ሃለፊና የዘርፍ አስተባባሪዎች እንዲሁም ስምንት ባለሙያዎች አሉት ፡፡
አቶ በላይ ወርቁ
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ኃላፊ መልዕክት
በወረዳችን በሚገኙ ከተምች ጊዚውን የሚመጥን፣የህዝብ ፍላጎት ምንም እንኳን አዳጊ ቢሆንም እሱን ለመልስ የሚችል ስራ እየተሰራ እንገኛልን። ከተሞቻችን ምቹ ፣ውብና ለንሮ ተስማሚ ለማድር ታቅዶ እየተሰራ ነው። ከተሞቻችን የነዋሪዎች እንዲሆኑ በርካታ የግንዛቤ መድረክ ፈጥረናል። ከተሞች ያለቸወን እምቅ የኢኮኖሚ አቅም በመጠቀም የከተማው ነዋሪ የበለፀግ እንዲሆን አይተስራ ነው። በከተማ ባልተለመደ መንገድ የንሮ ወድነት ጫና እየፈጠረ ነው፣ይህን ለመቋቋም የከተማ ግብርና አጠናክረን የያዝን ሲሆን በዶሮ፣በበግና ፍየል እርባታና ማምኮት በወተት ላም፣በማድለብ እንዲሁ በጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ የከተማው ማህረሰብ እንዲሳተፍ ጥረት ተደርጎ ወጤት መገምገም ተጀምረናል።በከተማ የንግድ እንቅስቃሴው ጤናማ ሆኖ እንዲሆዲ፣ወድድር ላይ እንዲመሰረት ከባለድርሻ አካላት በከተምች ከነጋዴው ማህበረሰብ የወይይት መደረክ እያደረግን እንገኛለን። ከተሞቻችን በመሰረተ ልማት የተምሉ እንዲሆን አቅደን እሰራን ሲሆን በዚህ ዘርፍ በርካታ መሻሻሎች ገምግመናል።የውሃ ችግር ሙሉ በሙሉ መቅረፍ ችለናል፣የማብራት መቆራርጥ እንዳይኖር ከተቋሙ ጋር በትብብር እየሰራን ሲሆን፣የመንገድ ለማት ነበሩን በማደስና በማሻሻል የተሻለ የጠጠረ መንገድ ግንባታ እንዲሆን አድርገናል፣አዲስ መንገድ ከፈታና ጠር ጋ በተሻለ መንገድ መከውን ፣የጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍና የውሃ መወረጃ ዲች ግንባታና ጥገና አጠናክረን በመቀጠል የከተሚውን የመኖራያ ሰፈር ደረጃ ማሻሻል አስፈላጊ በመሆኑ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ይገኛል።ከመሬት አቅርቦት ጋር ያሉ መሰናክሎች ቆጥሮ በመፍታት የመሬት ከቅርቦትና ትልልፍ በማዘመን የማህበረሰቡብ ችግር መቅረፍ ላይ እየሰራን ነው፣ለንግድ ፣ለመኖርያ ለኢንቨስትመንት እና ለተለያዩ አገልግሎት የሚውል መሬት በተገቢው መንገድ እያቀረብን ለልማት እያስተላለፍን ።መበጨረሺያም በወረዳችን ደቡብ ሶዶ የሚገኙ ከተም ች ለኢንቨስትመንት ተመራጭ የሚያድረጋቸው በርካቷ ሁኔታዎች በኖራቸው በተለይም ፍፁም ሰላማዊ ከተምች በመሆናቸው ከተኛውም አካባቢ መጥታችሁ እንቨስት እንድታደርጉ የደቡብ ሶዶ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ጥሪዉን ያስተላልፋል።





Views This Year : 47