ባህላዊ የሰላም መድረክ ነው ኬርታ
ኬርታ በክስታኔ ቤተ_ጉራጌ የተለየ ቦታ የሚሰጠው ባህላዊ የሰላም መድረክ ነው።
ኬርታ ከስሙ ጀምሮ ሰላም የሚሰብክ የተለየ ባህላዊ የእርቀሰላም ማውረጃና በማህበረሰብ፣በጎሳና በቤተሰብ የተሰሩ ለቀድሞ በደሎች ይቅርታ የሚጠየቅበት ለሚመጣውም ዘመን ሰላም የሚመኙበት መድረክ ነው።ይህ እጅግ ጥልቅ የሆነው ቱባ ባህል አባትና እናቶቻችን ለዘመናት ሲቀባበሉ ኖረው ለዚህኛው ትውልድ ያስረከቡት የተጣሉ የሚታረቁበት፣የበደሉ የሚክሱበት፣ተራርቀው የኖሩ የሚገናኙበትና በርካታ ባህላዊ ስርዓቶች የሚከወኑበት የሰላም መድረክ ነው።
የኬርታ ስነ-ስርዓት በኢትዮጵያ ጉራጌ ዞን #ሶዶ ክስታኔ ትልቅ ክብር የሚሰጠው ስነ-ስርዓት ሲሆን ትርጓሜውም በዚህ ማህበረሰብ የኑሮ ዘይቤ ውጣ ውረድ የተፈጠሩ ስህተቶችን በግልፅ በማውጣት የተጣሉ፤ በተለያዩ መንገዶችና ምክንያቶች እርስ በእርስ የተጎዳዱ፣ የተጋደሉና አጠቃላይ በምድራዊ ህይወት አላግባብ ግፍ የሰሩ ሰዎች ፈጣሪያቸውን በመለመን የተሰራው ግፍ ተገርስሶ የአካባቢው ሰላም እንዲሰፍን፤ ጀግና እንዲፈጠርና በሁሉም ዘርፍ አዎንታዊ ለውጥ እንዲታይ ይቅርታን አግኝተው ለቀጣይ ህይወታቸው መልካም አጋጣሚ የሚፈጥሩበት ሆኖ በሌላ በኩል ደግሞ #ኬርታ በማህበረሰቡ ዘንድ ጥፋት ባይኖር እንኳን ከቤተሰብና አካባቢው ጀምሮ ለሀገሪቱ ብሎም ለአለም ሰላምና ለውጥ በንፁህ ልብ የሰው ልጅ ከፉ አይንካው እንስሳው ሳሩ ቅጠሉ ይለምልም #ደህና ይሁንልን ይደረግልን በማለት በተመረጡ አባቶችና እናቶች በቤተሰብ፣ በዘመድ፣ በጎጥና አጠቃላይ ማህበረሰቡ ደረጃ ፈጣሪያቸውን ይማፀናሉ።

አባቶች ለመጀመርያ ጊዜ ኬር ብለው የማህበረሰቡ ኢኮኖሚያዊ ፓለቲካዊና ማህበራዊ አዎንታዊና አሉታዊ ክስተቶችን መዝነው ውጤቱንም ይረዱታል። ፈጣሪ ከሰማቸው እያመሰገኑ በሰው ልጅና እንስሳም ጭምር ግፍና በደል ከመስራት እየተቆጠቡ ይቀጥላሉ። #በዚህ ማህበረሰብ የሚታሰበው ጥሩ የህይወት ከባቢ ለማየት ሶስት ጊዜ ኬርታ ይደረጋል። በመጀመርያው ኬርታ እንዳልሰማቸው ሲገምቱ ደግሞ የጎደሉ ነገሮች አሟልተው ጥፋቶችን በመቀነስ ለሁለተኛ ጊዜ #ኬር ፈጣሪ ጥፋታችንን አትቁጠርብን ይቅር በለን ሰላም አብዛልን ከክፉ ጠብቀን እያሉ ማር ቅቤና የተለያዩ ግብዓቶች በማዘጋጀት ኬር ይላሉ። በዚህም ካልተሳካና የቀሩ የፈጣሪ ቁጣ ምልክቶች ከታዩ ለሶስተኛ ጊዜ #ኬር ብለው አምላካቸውን በመለመን ማለትም መልካም ምኞታቸውን ከፈጣሪያቸው ተነጋግረው ተግባራዊ ለውጥም ያያሉ።



#ኬርታ:- የሰው ልጆች ሰላም፣ ለውጥ፣ አንድነት፣ ፍቅር፣ እኩልነት፣ መከባበርና ጠቃሚ ነገሮች ሁሉ ከፈጣሪ ደጅ የሚቀዳበት መሰረታዊና ብዙዎች ያልተረዱት ስነ-ስርዓት ነው። እናም በዚህ ሰዓት አጠቃላይ የሶዶ ክስታኔ ማህበረሰብ ኬርታ እጅጉን የሚያስፈልገው በመሆኑ ለአካባቢው ኬር እንዲባል ለሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ የባህልና ቱሪዝም ተቋማት መልዕክቴን ለማስተላለፍ እወዳለሁ ምክንያቱም በርካታ ችግሮች ይስተዋላ። በጥቂቱም ቢሆን ያነሳሁት ርዕሰ ጉዳይ በማንበብ ሃሳቡን ስለተካፈልከኝ/ሽኝ አመሰግናለሁ።❗️ #ኬርታ በራሱ ከባዕድ አምልኳዊ አካሄድ የፀዳ #ይቅርታ ነው። ትልቁ የፈጣሪ ዋጋ ደግሞ ይቅርታ ነው። በቅዱስ መፅሃፉ የበደላችሁን እንኳን እኔን ዋስ አድርጋችሁ ይቅር በትሉት መልካም ዋጋችሁ እኔ ጋር ነው ብሏል።
#ኬር ለጉባኛ❗️
#ኬር ላገርኛ❗️
#ኬር ላለምኛ❗️