የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሚሊሻ ፅ/ቤት ኃላፊ

አቶ ዘነበ አረሩ

የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሚሊሻ ፅ/ቤት ኃላፊ

ዓላማ

ዋና ዓላማ

  • በ2016 በጀት አመት በጽ/ቤቱ ተልዕኮ ማሳካት የሚያስችሉ ከትኩረት መስኮች የተቀዱ ግብ እና ዋና ዋና ተግባራትን በአግባቡ በመለየት በማቀድ በየደረጃው የሚገኘው አመራርና ፈፃሚ ቅንጅት በመፍጠር፣ የቀበሌ ሚሊሻን በመመልመል፣ ማሰልጠንና በማደራጀት ከህረተሰብ፣ ባለድርሻ አካላትና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በማቀናጀት የተጠናከረ የአካባቢ ሰላም አጠባበቅ ማድረግ ነው፡፡

ዝርዝር ዓላማ

  • የሚሊሻ ጽ/ቤት በክልል፣ በዞን፣ ወረዳ እና ቀበሌ ደረጃ የሚገኙ አደረጃጀቶች በጋራ ራዕይና ተልዕኮ ትስስር ፈጥሮ ለመስራት፣
  • የሚሊሻ አባላት በአካባቢ ፀጥታ ጥበቃ ላይ የተሻለ አፈፃፀም እንዲመዘገብ በስልጠና የአቅም ግንባታ ማጎልበት ስራ ለመስራት፤
  • በአካባቢ ፀጥታ ጥበቃ ህብረተሰቡ፣ ባለድርሻ አካላትና ተባባሪ ወጎኖችን ተሳታፊ ለማድረግ፤
  • የውጤት ተኮር ዕቅድ ምዘና ስርዓቱ ተጠያቂነትን መሠረት ያደረገና ተመጋጋቢነቱን የጠበቀ እንዲሆን ማስቻል፣
  • በጽ/ቤቱ ራዕይ ስትራቴጂና ተግባራት መካከል ትስስር በመፍጠር ራዕይና ተልዕኮውን ለማሳካት፣ ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች በጋራ ተቀናጅቶ ውጤታማ ተግባር መፈፀም፤
  • በስትራቴጂያዊ አስተሳሰብ ለመምራትና ተቋማዊ ብቃት ለመፍጠር፤

ራዕይ

በ2022 ዓ.ም የአካባቢ ፀጥታና ሠላም የተረጋገጠበትና የህብረተሰቡ ደህንነት የተጠበቀበት ወረዳ ተፈጥሮ ማየት፣

ተልዕኮ

በህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ ብቃት ያለው የሚሊሻ ኃይል  በመመልመል፣ በማሰልጠን፣ በማደራጀት፣ በማሰማራት፣በማጥራትና የሎጅስቲክስ አስተዳደር በማካሄድ የሚሊሻ ኃይል ማፍራትና ተደራሽነቱን በማረጋገጥ የአካባቢ ፀጥታን ማስከበርና የህብረተሰቡን ሠላምና ደህንነት መጠበቅ፣

እሴት

ዕሴቶች የሴክተሩ ሠራተኞችና የሥራ አመራሩ የሚመሩባቸውና ወደፊትም በጋራ ሊከተሏቸው የሚገቡ የግልና የተቋም የአሰራር ፍልስፍናዎች ሲሆኑ ሴክተሩ

  • ለህገ-መንግሥቱ ታማኝ መሆን፣
  • የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማረጋገጥ፣
  • ሀብትን በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም፣
  • የሕዝብ አገልጋይነት፣
  • ብዝኃነት መቀበልና ማክበር፣
  • ፍትሃዊነትና ሰብአዊነትን መላበስ፣
  • ራስን ማብቃት፣ አዳዲስ አሠራሮችን ማወቅና መጠቀም፣
  • ሙያዊ ሥነ-ምግባር መላበስ፣
  • ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ትኩረት መስጠት እና

ኃላፊነትን መወጣት የሚሉት ናቸው፡፡

  • በአካባቢ ሠላምና ፀጥታ አጠባበቅ የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማሳደግ፡፡
  • በአካባቢ ሰላም እሴት ግንባታ የህብረተሰቡን እርካታ ማሳደግ ፡፡
  • የሚሊሻ ኃይልን በመመልመል፣ በማሰልጠን፣ የአከባቢ ፀጥታ ጥበቃ አገልግሎት ሽፋንን ማሳደግ፡፡
  • በሰላም ግንባታ የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ማሳደግ ፡፡
  • የሚሊሻ ኃይልን በማደራጀትና በማሰማራት የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናን ማሳደግ ፡፡
  • የሚሊሻ ኃይልን የአገልግሎት አሰጣጥ ዉጤታማነት ማሳደግ ፡፡
  • የሰላም ግንባታና የአከባቢ ፀጥታ ጥበቃ ዉጤታማነትን ማሳደግ ፡፡
  • የአካባቢ ፀጥታ መረጃ አደረጃጀትና ፍሰት ቅልጥፍናን ማሳደግ ፡፡
  • የሚሊሻ ሀይል ምልመላና አቅም መግንባት
  • ግጭትን መከላከልና ወደ በጎ መለወጥ
  • በአካባቢ ፀጥታ ጥበቃ የህብረተሰብ ተሳትፎ
  • የአካባቢው ሰላምና ፀጥታ ማስከበር
  • የሀይማኖትና እምነት እሴት ግንባታ

ወረዳው ከ2002 ዓ/ም ከፍትህና ፀጥታ ጽ/ቤት ስር እራሱን ችሎ በአዋጅ ከተቋቋመ ወዲህ የወረዳውን ህዝብ ሰላምና ፀጥታ በማስጠበቅ በኩል ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በዚህም የህ/ሰቡን ተሳትፎ ያረጋገጠ የወንጀል መከላከል የግጭት አፈታትና አስተዳደር ከዘመናዊ የግጭት መከላከልና አስተዳደር ስርዓት ጋር በማቀናጀት የወረዳውን ሰላምና ፀጥታ አስተማማኝ ደረጃ ማድረስ ሲሆን ከመዋቅር አደረጃጀት ጀምሮ የፀጥታ ሀይሉን በማደራጀትና በማሰማራት ከአሁን በፊት ግጭት ተከስተው ያልተፈታባቸውን አካባቢዎች በመለየትእንዲሁም አልፎ አልፎ የተከሰቱ ግጭቶችና አለመግባባቶች በራሱ በወረዳውና ከአጎራባች ወረዳዎች ጋር በመቀናጀት ሰላምና ፀጥታ አስተማማኝ ደረጃ ላይ ለማድረስ በሚደረገው እንቅስቃሴ ሂደት ግጭቶችን በብቃት ለመከላከል ህ/ሰቡን ያሳተፈ የግጭት አፈታት ስልት በባህላዊና በዘመናዊ መልኩ ለመፍታት እንዲሁም የሰለጠነ የሰው ሀይልና ቁሳቁስ አደራጅተው መንቀሳቀስ ከጀመረ ወዲህ በርካታ ለውጦች መታየት ጀምሮዋል፡፡

  እነዚህ ስራዎች ከወረዳው ስፋትና ልዩ ባህሪ አንፃር በርካታ ፍላጎቶች የሚንፀባረቅበት ከመሆኑም ጋር ተያይዘው በተለያየ ምክንያት በህዝቦች መካከል የሚከሰቱ አለመግባባቶች ወደ ግጭት ሊያመሩ ስለሚችሉ ቀጣይ በወረዳችን በሁሉም ቀበሌዎች ሰላምና ፀጥታ ለማስፈን ጽ/በቱ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ለመፈፀም አቅዶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡

የተፈቀደለት የሰው ሀይል=20

የተሸፈነ በዋና ስራ ሂደት ወ=3. ሴ=0 ድ=3      ያልተሸፈነ በዋና ስራ ሂደት=7

በደጋፊ ስራ ሂደት ወ=0. ሴ=3 ድ=3          በደጋፊ ስራ ሂደት =4

ያልተሸፈነ የጋራ =3