የደቡብ ሶዶ ወረዳ ፕላን ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት

ዋና ዓላማ

የዓስር ዓመቱ መሪ ዕቅድ መነሻ በማድረግ ዓመታዊ የትኩረት መስኮችና ግቦች በመለየት ማቀድና መተግበር የሚችሉበትን መደላድል በመፍጠር የሴክተሩን ውጤታማነት ማረጋገጥ ነው፡፡

ዝርዝር ዓላማ

  • በወረዳው ጠንካራና ደረጃውን የጠበቀ የእቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ስርዓት እንዲዘረጋ ማስቻል!
  • ወረዳው የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ሊቀርፉ የሚችሉ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች እንዲተገበሩ በማድረግ እና በልዩ ልዩ የፖሊሲና ስትራተጂዎች አፈፃፀምን በሚመለከት ጥናት በማካሄድ፣በወረዳው ያለውን የልማት ክፍተት የማሻሻያ ሃሳቦችን በማቅረብ የወረዳው  የኢኮኖሚ ሁኔታ ማሻሻል እና የወረዳው የድህነት ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንስ ማስቻል !
  • በወረዳው ከየአሰተዳደር እርከኑ ጋር የሚያገናኝ የተቀናጀ የመረጃ ሥርዓት በመዘርጋት ወቅታዊ ወጥ ትክክለኛና ተአማኒነት ያላቸውን የተሟላ የማህበራዊና የኢኮኖሚ ሁኔታ አመልካች መረጃዎችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ማድረግ!
  • በማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ምጣኔ ሐብት ልማትና በሕዝብ ቁጥር ዕድገት ምጣኔ መካከል ያለውን ልዩነት በማጥበብ በቀጣይ ጊዜያት የሕዝቡን የኑሮ ሁኔታ ደረጃ በደረጃ  በማሻሻል ዜጎች የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩ ማስቻል፤

ተልዕኮ

በማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች መለስተኛ ጥናቶችን በማካሄድና የፖሊሲ ማሻሻያ ሀሳቦችን በማመንጨት፣ ግልፀኝነትና ተጠያቂነት በሰፈነበት አሰራር ዘመናዊ የልማት ዕቅድና መረጃ በመዘርጋት፣የልማት አጋሮችን በማስተባበርና የሕዝብ ቁጥር ዕድገት ከኢኮኖሚ እድገት ጋር እንዲጣጣም በመስራት በወረዳው ፈጣንና ቀጣይነት ያለው  ልማት እንዲረጋገጥ ማስቻል፡፡

ራዕይ

ፍትሃዊ የሀብት ድልድልና አጠቃቀም በማረጋገጥ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ ዕድገትን በማስፈን የወረዳው ሕዝብ ከድህነት ተላቆ  ማየት፡፡

  • ቆጣቢነት
  • ወቅታዊና አስተማማኝ መረጃ
  • ፍትሃዊነት
  • ውጤታማነት
  • ግልፀኝነትና ተጠያቂነት
  • ተቆርቋሪነት
  • ቀልጣፋ አገልገሎት
  • በእቅድ መመራት
  • ሕጋዊነት

በዳይሬክቶሬት የሚሰጡ ዝርዝር ግብ

  • የወረዳውን የረጅም የመካከለኛና የአጭር ጊዜ ዕቅድ ሰነድ ማዘጋጀት!
  • የወረዳው የረጅም የመካከለኛና የአጭር ጊዜ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ማዘጋጀት! ማሳተም እና ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ማድረግ!
  • በወረዳው የካፒታል ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ሁሉንም ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ የግማሽ ዓመት እና ዓመታዊ ወቅታዊ የሆነ ክትትልና ግምገማ ማካሄድና ሪፖርት በማዘጋጀት ለሚመለከተው አካልማቅረብ፤
  • የዕቅድ ዝግጅት! ክትትልና ግምገማ የአሠራር ማንዋል በማዘጋጀትማቅረብ፤
  • ክልሉ በሚያዘጋጀው አመታዊ የሀብት ማከፋፈያ ቀመር መሰረት ለወረዳዎች በጀት ማከፋፈል፣
  • የወረዳው ሴክተሮዎች የረጅም ጊዜ እቅድ የአጋማሽ ጊዜ፣ዓመታዊ እና የየሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ማዘጋጀት፤
  • የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በማዘጋጀት በየደረጃው የሚገኙ ኃላፊዎችንና የባለሙያዎችን የማስፈፀም አቅም ማጎልበት፤
  • ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በተለያዩ የማክሮ ኢኮኖሚና የማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ልዩ ልዩ ጥናቶች ማካሄድና ባለድርሻ አካልትና በሴክተሩ መካከል የእውቀት ሽግግር በማድረግ የባለሙያዎች የማስፈፀም አቅምና ክህሎትን ማሳደግ!
  • የአስር ዓመቱን ዕቅድ አፈፃፀምን በሚመለከት አግባብነት ካላቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የአጋማሽ ጊዜና የማጠቃለያ ጊዜ ክትትልና ግምገማ በማካሄድና ሪፖርት በማዘጋጀት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ የሚሆኑበት የአፈጻጸም ግምገማ የውይይት መድረክ ማዘጋጀትና ሪፖርቱን በማሳተም ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ማድረግ
  • የወረዳው ስታቲሰቲካዊ መረጃ አቅርቦት በጥራት፤በጊዜ እና በመጠን የተሟላ በማድረግ የተገልጋይ ፍላጎትና እርካታ ማረጋገጥ
  • በወረዳው አስተዳደራዊ ሰታቲስትካል መረጃ አመንጭ ተቋማት የመረጃ አስተዳደር ሂደትና ሥርዓትን ሙሉ በሙሉ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዞ የመረጃ ጥራት ችግር በወሳኝ መልኩ 95 በመቶና በላይ መፍታት
  • የክልሉን CSA መነሻ በማድረግ የወረዳው ሁለንተናዊ ዕድገትና ብልፅግና የሚለካባቸዉ መለክያዎች የሚፈልጋቸዉን መረጃዎች መቶ በመቶ በማመንጨት የመረጃ አቅርቦት ችግርን መቅረፍ!
  • የሰው ሃብት ብቃትና ተነሳሽነትን ማሳደግ፤(የሰዉ ቁጥር ይገለጽ)
  • የወረዳ ስታቲስቲካል ሲስተም የሚመራባቸዉ የአሰራር ሥርዓቶችን መዘርጋትና የተዛቡና ትክክለኛነታቸው ያልተረጋገጡ መረጃዎችን በሚያቅርቡ አካላት የተጠያቂነት አሰራርን ማስፈን
  • የሁሉም ዓይነት መረጃ መሰብሰብያ ዘዴዎች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆኑ ይደረጋል! ለዚህም የሚሆኑ የቴክኖሎጂ ግብዓቶች ሙሉ በሙሉ እንዲሟላ ይደረጋል!( ኮምፒወተር፤ሶፍትዌርናኢንተርኔትአገልግሎተ)
  • ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ግብአት በማሟላትና በመጠቀም የገፀ-ምድርና መረጃዎችን በማሰባሰብ በማደራጀት እንዲሁም በዘመናዊ ጂኦ-ዳታ ቤዝ ማከማቸት መተንተንና በተለያዩ ሰነድ ዓይነቶች (በካርታ፤በቡክሌት ለተጠቃሚዎች ማቅረብ!
  • የወረዳው ማዕከላዊ መረጃ ክፍል ( Zonal data center} ደረጃዉን በጠበቀ መረጃ ማከማቸትና ማሰራጨት፤(ዓመታዊና አብስትራክት) በቁጥር
  • በሥነ-ህዝብና ልማት ዙሪያ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ፤
  • የሕዝብ ቁጥር ዕድገት ምጣኔው ከወረዳው የኢኮኖሚ ልማት ጋር እንዲጣጣም ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ትብብር ማጠናከር
  • የሥነ-ሕዝብ ጉዳዮች በሚመለከታቸው 9 ሴክተርመ/ቤቶች የልማት ዕቅድ ውስጥ አካትተው እንዲተገበሩ ድጋፍ ማድረግ፤
  • ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ልማት ለማረጋገጥ የሚመለከታቸውን የመንግስት ተቋማትን ማስተባበር፤
  • የሴቶችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳታፊነትንና ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የሚደረገውን ትብብር አጠናክሮ ማስቀጠል፤
  • ችግር ፈቺ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን በማካሄድ የሥነ-ህዝብና ልማት ችግሮችን በሳይንሳዊ መንገድ መፍታት
  • የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎችንና የህትመት ውጤቶችን (ብሮሸርና የሬድዮ ስርጭት) በመጠቀም በተከታታይ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ፤

ወ/ሮ አሰፋሽ ቡርቃ በዳሶ

የደቡብ ሶዶ ወረዳ ፕላን ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ መልዕክት

ፕላን ኮሚሽን የወረዳውን አሰፈፃሚ አከላት ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ በቁጥር 180/2012 የተቋቋመ መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም የፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በወረዳው ከተቋቋሙት ሴክተሮች/ጽ/ቤቶች/ አንዱ ሲሆን የተቋቋመበት ዋና ዓላማ የወረዳው የልማት እንቅስቃሴዎች በዕቅድ እንዲመሩ ለማስቻልና በተግባራት አፈጻጸም ረገድ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት አሠራር ይበልጥ እንዲሰፍን በማድረግ፣ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል እንዲረጋገጥና ዘመናዊ የመረጃ አያያዝና ስርጭት ስርዓት በመዘርጋት የወረዳው ትክክለኛና ወቅታዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ገጽታ መረጃዎችን በማሰባሰብ ማደራጀትና ለተጠቃሚዎች በማሰራጨት እና የህዝብ ቁጥር ዕድገት ከኢኮኖሚ ዕድገት ጋር ተጣጥሞ እንዲጓዝ በመሥራት ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ቀጣይ እንዲሆን የሚጠበቅበትን ተልእኮ ለመወጣት ነው፡፡ በአጠቃላይ እንደ ፕላን ልማት ፅ/ቤት ላስተላልፍ የምፈልገው የህዝብ ቁጥር ዕድገት ከኢኮኖሚያችን ጋር ተጣጥሞ እንዲሄድ የባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ትኩረት እንደሚያስፈልግ እየገለፅኩኝ በዚህ ሁኔታ በትኩረት ከሰራን አሁን ላይ እንደ ሀገር የገጠመንን የኑሮ ውድነቱን ልንቋቋመው እንችላለን እላለሁኝ አመሰግናለሁ፡፡

የሴክተሩ አጠቃላይ ገጽታ

ፕላን ፅ/ቤት ቀደም ባሉት ዓመታት በፋ/ኢ/ል/መ ውስጥ  ከነበሩት ል/ዕቅድ  ስነ ህዝብ ሶሽዮ ኢኮኖሚ የስራ ሂደቶችን በመያዝ እዲሁም የሰው ሃብት አስተደደር እና መረጃና ስታትስቲክስ የስራ ሂደትችን በመጨመር በአዲስ መልክ የተቋቋመ   የወረዳውን የረጅምና የመካከለኛ የአጭር ጊዜ ዕቅድ ማዘጋጀት አፈጻጸሙን መከታተልና መገምገም፤ የማክሮ ኢኮኖሚ ፊስካል ማዕቀፍ ማዘጋጀት፤ የመንግስት ካፒታል ፕሮጀክቶች የአዋጭነት ጥናት ማካሄድና መገምገም፤ የማክሮ ኢኮኖሚ ጥናት ማካሄድ ፤ የወረዳውን ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ መልካ ምድራዊ መረጃ ማሰባሰብ፤ መተንተንና ማሰራጨት፤ የስነህዝብ ጉዳይን በልማት ዕቅድ አካቶ ከመተግበር አንጻር መንግስትና መንግስታዊ ያልኑ ድርጅቶችን ማስተባበር፤ በእቅድና ፕሮጀክቶች ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዙሪያ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ተግባራዊ ማድረግ ወዘተ…

የደቡብ ሶዶ ወረዳ ፕላን ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤትን ለማግኝት