ገና በ ክስታኔ ቤተ-ጉራጌ
ገና በ ክስታኔ ቤተ-ጉራጌ ውስጥ ሐይማኖታዊና ባህላዊ ይዘት ኖሮት ይከበራል።በዓሉ ከገና ወይም ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል ከአንድ ወር በፊት በከብት እረኞች እና በአካባቢ ለአቅመ አዳም በደረሱ ጎረምሶች በገና ጭዋታ ይጀመራል ለዚህም መነሻ የሚሆነው ሐይማኖታዊ አንድምታ “ከመፅሐፍ ቅዱስ ከማቴዎስ ወንጌል ምዕ 2፥8-20 የሚገኙትን የጌታን መወለድ ከመልአኩ የሰሙትን እረኞችን ይወክላል” በማለት የሐይማኖት መሪዎችና ታላላቅ የሀገር ሽማግሌዎች ይናገራሉ። ይህ ባህላዊ ጨዋታ የራሱ የሆነ ህግ እና የራሱ የሆነ የመጫዎቻ እቃዎች አሉት እነዚህም፦
1ኛ/የገና ዱለ(ጉማ ወይም ፋርጉጌ)ጫፉ ወፈራም እና ቆልማማ የሆነ ከባህርዛፍ ወይም ከወይራ ዛፍ በሥርዓት ተጠርቦ የሚዘጋጅ ነው።
2ኛ/ሩር(አንቃት)ከእንጨት ዛፍ ስር ወይም ተፈልፍሎ እንደ ኳስ ድቡልቡል ተደርጉ አንደይሰነጠቅ በእሳት ተለብልቦ የሚዘጋጅ ሲሆን ፤ለጫወታው ምቹ እና ለጥ ባለ ሰፊ በሆነ ሜዳ ላይ ዳኛ(ያኖግ)በመሰየም ጫወታው ይካሄዳል።

ይህም ባህላዊ ጫወታ መንደር ከመንደር ቀበሌ ከቀበሌ በግጥሚያ ወይም በውድድር መልክ ተዘጋጅቶ ይቀርባል በዚህም ጫወታ ቂም በቀል ጌታና ሎሌ ታናሽና ታላቅ ተብሎ የሚበላለጥ እና በቅሬታ የሚያዝ ቂም ቁርሾ ፀብ አይኖርም። እንዲህ እንዲህ እያለ ጫወታው እሰከ ገና በዓል ይቀጥላል በመጨረሻም በዘመነ ዮሐንስ ከሆነ በታህሳስ 27በሌላው ጊዜ ደግሞ በታህሳስ 28ማታ ወይም በገና ዋዜም ሆያሆዬ(እንዞሪቴ)ጭፈራ ይጀመራል ጭፈራውም በእድሜ አቻ የሆኑ ወንድ ወጣቶች ቤት ለቤት በመዞር ይጨፍራሉ ለዚህም ብር እና በአይነት የእህል ስጦታን ከአባወራው ወይም ከእማወራዋ ይቀበላሉ ከዚህም በተጨማሪ ልጅ ያልወለደች ሴት ቤት በመሄድ ስለት ምርቃትን ይቀበላሉ ሰለቱም እንዲሰምር ምስጋና ያቀርባሉ እንዲህም ብለው ያዜማሉ፦


