እንኳን ወደ ደቡብ ሶዶ ወረዳ ዌብሳይት በሰላም መጣቹ
ክስታኔዎች ከጥንት ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ጠንካራ የስራ ባህል ያለው ማህበረሰብ ነው፡፡ በገጠር የሚኖረው የክስታኔ ማህበረሰብ ቆጮ ለማዘጋጀት፤እርሻ ለማረስ፤ከብት በማርባት እና በተለያዩ የስራ መስኮች ተሰማርቶ የሚኖር ማህበረሰብ ሲሆን በአጠቃላይ የክስታኔ ማህበረሰብ ማሃበራዊ ኑሮ ብቻ ሳይሆን ስራን አብሮና ተበብሮ የመስራት ባህሉ እጅግ አስደማሚና ትምሳሌት የሆነ ተግባር መሆኑን ነው የሚያሳየው፡፡ ከነዚህም ተባብሮና አብሮ የመስራት ባህል መካከል ለአብነት ያህል፡-
ውሣቻ ማለት በማህበረሠባችን እሴቶች ዘንድ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ በስፋት የሚተገበር ባህላዊ የመረዳጃ እሴት ሲሆን ወንዶችም ቢሆኑ ለቆጮ የደረሰውን እንሰት በጊዜ በመንቀል በተግባሩ ላይ የድርሻቸውን ይወጣሉ፡፡ የአካባቢውም ሴቶች በጋራ በመሆን በወንዶች የተነቀለውን እንሰት ለቀጣይ ለቆጮ አገልግሎት እንዲውል የማዘጋጀቱን ሙሉ ሀላፊነት ይወጣሉ፡፡ ስለዚህ ውሣቻ ማለት በአንድ መንደር የሚኖሩ ሴቶች ተደራጅተው በየተራ እየዞሩ ቆጮ የሚያዘጋጅበት/ የሚፍቁበት ስርዓት ነው፡፡
የደቡብ ሶዶ ወረዳ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጉራጌ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች አንዱ ሲሆን ወረዳውን






Views This Year : 47የባለቤትነት መብት @2016 የደቡብ ሶዶ ወረዳ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው
