የደቡብ ሶዶ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት

አቶ ሽመልስ ፈቀደ ወርሳ
የደ/ሶ/ወ/ጤ/ፅ/ቤት ዋና ኃላፊ
ራዕይ (Vision)
ጤናማ፣ምርታማና የበለፀገ ሕብረተሰብ ተፈጥሮ ማየት
ተልዕኮ (Mission)
ጥራቱን የጠበቀ፤ ፍትሐዊና ተደራሽ የሆነ የጤና ማበልጸግ፣ በሽታ መከላከል፣ የፈውስ ህክምናና የተሃድሶ ጤና አገልግሎት በመስጠትና በመቆጣጠር የወረዳውን ህብረተሰብ ጤናና ደህንነት ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ ነው፡፡
- የማሕበረሰብ ጥቅሞች ማስቀደም
- ቅንነት
- ታማኝነትና ሐቀኝነት
- ግልፅነትና ተጠያቂነት
- ምስጢር መጠበቅ
- ሕጋዊ በሆነ ስልጣን መጠበቅ
- አድልዎ አለመፈፀም
- ሕግን ማክበር
- አርአያ መሆን
- መደጋገፍ
- ሙያዊ ሥነ-ምግባር
- ተከታታይ ሙያዊ ዕድገት
- ለለውጥ ዝግጁነት
- ርህራሄ
- የእናቶች እና የጨቅላህፃናት ጤና ማሻሻል
- የስነምግብ ሁኔታን ማሻሻል
- የዋናዋና በሽታዎችን ክስተት እና በኽብረተሰቡ ውስጥ የሚኖረው ጫና መቀነስ
- የህክምና እና ተሀድሶ አገልግሎት ማሻሻል
- የህብረተሰቡን የጤና ባለቤትነት ማሻሻል
- የፋይናንስ ተገቢነት እና ውጤታማነት ማሻሻል
- የአደጋ ክስተቶች ለሚያስከትሏቸው አደጋዎች ምላሽ የመስጠት አቅምን ማሳደግ
- የግባት አቅርቦት እና አስተዳደር ስርዓትን ማሻሻል
- የመልካም አስተዳደር ስርዓትን ማሻሻል
- ቴክኖሎጂዎች እናአዲስ የፈጠራ ውጤቶችን ማሻሻል
የህብረተሰብ ተሳትፎ ውክልናነ ባለቤትነት ማሻሻል
- ፍትሃዊ እና ጥራቱነ የጠበቀ አጠቃላይ የጤና አገልግሎትአሰጣጥ ማሻሻል
- የጤና ድንገተኛ እና አደጋ ስጋት አስተዳደርን ማሻሻል
- የማህበረሰቡን ጤናና ባለቤትነት ተሳትፎን ማሳደግ
- የቁጥጥር ስርዓቶችን ማሻሻል
- የሰው ሃብት ልማትና አስተዳደርን አሰጣጥን ማሻሻል
- መረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ አሰጣጥን ማሻሻል
- ዲጂታል ጤናን እና ፈጠራዎችን ማሻሻል
- የጤና አመራር እና መልካም አስተዳደርን ማናከር
- የጤና ፋይናንስን ማሻሻል
- የግሉን ዘርፍ የጤና ተሳትፎ ማሻሻል
- የባህል ህክምና ማሻሻል
- ወረዳ ደቡብ ሶዶ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት
- ዞን ምስራቅ ጉራጌ ዞን ጤና ፅ/ቤት
- ክልል ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
- የስራ ክፍሎች ብዛት 11
የደ/ሶ/ወ/ጤ/ፅ/ቤት ዋና ኃላፊ መልዕክት
ወረዳችን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን የምትገኝ ወረዳ ስትሆን ከክልላችን በ120 ኪሎ ሜትር ከዞናችን በ25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ስትገኝ ወረዳችን በጤናው ዘርፍ በርካታ ስራዎች የተሰሩ ሲሆን ለአብነት ያህል ከዚህ በፊት ከጤና ተደራሽነት አንፃር ጉድለት የነበረብን ሲሆን አሁን ላይ 100% ደርሳል ከዚያ ውስጥ አንዱ የዳሙ ጤና ጣብያ ግንባታን ስናስብ ከዚህ በፊት የዳሙ እናቶች በወሊድ ወቅት ሌላ ሩቅ ቦታ ነበር የሚጓዙት አሁን በአቅራቢያቸው ማግኛታቸው እንዲሁም ቢታመሙም በቅርበት መታከም መቻላቸው ሌላው እንደ ጤና ሚንስተር ከተቀመጠው ፕላን መሰረት በዋናነት በሽታን መከላከልና እንዲሁም የታመመን በህክምና አክሞ ማዳን መሰረት የታለመውን እቅድ ለማሳካት እየተሰራ ሲሆን ለዚህ በወረዳችን 4 ጤና ጣቢያ እንዲሁም 17ጤና ኬላዎች አሉን ሌላው ከባለሙያ ስብጥር ጋር ተያይዞ በ4ቱም ጤና ጣቢያ የተሟሉ ባለሙያ ያለ ሲሆን በሽታን ከመከላከል አንፃር በሁሉም ቀበሌዎቻችን ጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ሲኖሩ 18ቱን ፓኬጆች መሰረት ያደረገ ስራዎች በመሰራት ላይ እንገኛለን።