የደቡብ ሶዶ ወረዳ ፋይናስ ጽ/ቤት

አቶ ተሻለ ደበላ ቁፋ

የደቡብ ሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ፅ/ቤት ኃላፊ

ዓላማ

ዋና ዓላማ

 የተቋሙ አመታዊ ዕቅድ በሀገራችን የተጀመረዉን ፍኖተ ብልፅግና ጉዞ በማፋጠን  በወረዳችንችን በብልፅግና ጉዞ የዜጎችን ቁሳዊ ፍላጎት፣ ዕኩል የልማት ተሳታፊነት፣ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና ነፃነትን ለማረጋገጥ የትኩረት መስኮችና ግቦቻቸዉን አንጥሮ በመለየት በየደረጃው የሚገኙ ፈፃሚ አካላት ከዚህ ተቋማዊ ዕቅድ የየራሳቸውን ድርሻ በመውሰድ ማቀድና መተግበር የሚችሉበትን መደላድል በመፍጠር የሴክተሩን ውጤታማነት ማረጋገጥ ነው፡፡

ዝርዝር ዓላማዎች

ሀ.የፊስካል ፖሊሲ (ገቢ፣ ወጪና በጀት) አተገባበርን በቁርጠኝት በመፈፀም የወረዳውን ሀብት ማሳደግ፣

ለ.የመንግስት ሀብትን ፍትሃዊ፣ ግልፅና ተጠያቂነት ባለዉ መንገድ፣ በቁጠባ፣ በብቃት እና ዉጤትን በላቀ ደረጃ ሊያስገኝ በሚችል አኳኋን መምራት፣ ማስተዳደር እና መቆጣጠር፣

ሐ.ግዥና ንብረት አሰተዳደርን ወጪ ቆጣቢ፣ ወቅታዊ፣ ግልጽ፣ ቀልጣፋ፣ ውጤታማ በሆነ መንገድ መምራት፣ አድሏዊ አሰራርና የሀብት ብክነት እንዲከስም ማድረግ፡

መ.የሴክተሩ የመረጃ አያያዝ ስርዓት በዘመናዊ ተክኖሎጂ በመታገዝ ተጠያቂነትን በሚያሰፍን መንገድ በማሰተዳደርና በመቆጣጠር  ወቅታዊ ተደራሽነትን በጥራት ማረጋገጥ፣

ራዕይ

 በወረዳችን በብልፅግና ጉዞ የዜጎችን ቁሳዊ ፍላጎት፣ ዕኩል የልማት ተሳታፊነት፣ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና ነፃነትን ለማረጋገጥ የወረዳው ሀብት በብቃት በማሰተዳደርና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ልማት በማረጋገጥ መሰረታዊ የኢኮኖሚ ለውጥ መጥቶ ማየት፣ በወረዳችን ፐብሊክ ሰርቪስ ዉስጥ በልህቀቱና በውጤቱ መሪ ተቋም መሆን፤

ተልዕኮ

 በቁጠባ ላይ የተመሰረተ የሀብት አጠቃቀም እንዲሰፍን ፣ ዘመናዊ የመንግስት ሃብት አስተዳደርና ቁጥጥር ስርዓትን በመዘርጋት፣ የፊስካል ፖሊሲ፣ሲቪክና ትብብር ሀብት በማስተባበርና በመምራት፣ የመንግስት ልማት ድርጅቶችን በማስተባበር፣ አሰራሩን የጠበቀ ግዥ ሥራዓት በመዘርጋት እና የንብረት ማስወገድ አገልግሎት፣ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት በሰፈነበት አኳኋን በወረዳው ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ፍትሃዊ የሀብት አሰተዳደር  ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ

የሕዝብ አገልጋይነት፣

ዉጤታማነት፣

የስራ ትጋትና ቁርጠኝነት፣

ህጋዊነት፣

የሙያ ልቀት፣

የመማርና የለውጥ ተነሳሽነት፣

ተጋግዞ በቡድን መሥራት፤

የበለፀገ ኢኮኖሚ መገንባት፣

  • ለሴክተሮች በጀት ክፍፍል የሚሆን ትክክለኛ መረጃ ማደራጀት
  • ለሴ/መ/ቤቶች ፍትሃዊ የሆነ የበጀት ክፍፍል ማድረና በካቢኒ በማስተቸት አንዲፀድቅ ማድረግ
  • የፀደቀውን ጥቅል በጀት በሴክተር፤በፕሮግራምና በበጀት ዓይነት በየስራ ሂደቱ በመዘርዘር ማደራጀትና ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ተገቢው ክትትል ማድረግ፤
  • ከሴ/መ/ቤቶች የተጠቃለለ የድርጊት መርሃ ግብር የጥሬ ገንዘብ አጠቃቀም ድርጊት መርሃ ግብር መቀበልና በመርሃ ግብሩ መሰረት መምራት፤
  • ከወረዳው ሴ/መቤቶች በየሩብ ዓመቱ የተግባር አፈፃፀም ሪፖርት መቀበልና አፈፃፀማቸውን መሰረት በማድረግ ግ-መልስ መስጠት የግ-መልስ ምላሽ መቀበል፤
  • በ2016 በጀት ዓመት በጠቅላላው ከመንግስት ግምጃ ቤትና ከወረዳው ገቢ ብር ሙሉ (የ12 ወር ለደመወዝ)ና አስገዳጅ ወጪዎች ፤ለካፒታልና ስራ ማስኬጃ በመደልደልና በተገቢው በማደራጀት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ማድረግ፤
  • የእርዳታ ብድር ፕሮግራሞች /ፕሮጀክት አፈፃፀም  4 ዙር በመስክ በመደገፍና በመከታተል ሪፖርትና ግ-መልስ ማዘጋጀት
  • በ2016 በጀት ዓመት ትርፍ የተሰበሰበ ገቢ (የማዘጋጃ ቤት፣የት/ቤቶችና ጤና ጣቢያዎች ) መረጃ በማድራጀትና በማጥራት አፀድቆ ስራ ላይ እንዲውል ማድረግ፤
  • ገላጭ የሆነና ጠንካራ ሁሉም ተግባርና ሴክተሮች ያቀፈ የጠቅላላ ግዥ ዕቅድ ማዘጋጀት፤ወጪ ቆጣቢ ግዢ መፈፀም፤
  • የደመወዝ፣ የተራድኦ በጀት ፣የግዥ የአገልግሎትና ሌሎች ክፍያዎች በወቅቱ ትክክለኛ ነታቸው በማረጋገጥ ክፍያ መፈፀም፤
  • የአፈፃፀም ወቅታዊ ሪፖርት ለሚመለከተው አካል ማስተላለፍ(ማለትም ወርሃዊ የሂሳብ ሪፖርት ለዞን እና ወርሃዊ የበጀት አፈፃፀም ሪፖርት ለሴክተሮች ተደራሽ ማድረግ)
  • የቋሚና አላቂ ንብረቶች በተገቢው ገቢና ወጪ ማድረግ በቋሚና አላቂ መዝገብ መመዝገብ በተገቢው መያዝ፤
  • የ2016 የተጠቃለለ የወረዳው የህትመት ፍላጎት ለዞን ማቅረብ፣ ከዞን የቀረበው ህትመት ወደ ወረዳ በማምጣት በተገቢውና በወቅቱ ስርጭት ማድረግ መከታተል፣
  • የሴ/መ/ቤቶች በጀት በተገቢው የሌጀር ቁጥጥር ማድረግ፣ ጥሬ ገንዘብ በጥሬ ገንዘብ መዝገብ መቆጣጠር እና ወርሃዊ ባንክ የማስታረቅ ስራ መስራ፤
  • ዓመታዊ የጥሬ ገንዘብ የድርጊት መርሃ ግብር ከሴክተሮች ማሰባሰብ ማደራጀት እና ለዞን ማስተላለፍ እና ሴክተሮች ባቀረቡት የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት የዲርጊት መርሃ ግብር መሰረት መምራት፤
  • በፋይናንስና ፋይናንስ በሚያስተዳድራቸው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የማይሰጡ ንብረቶችን ሰብስቦ የማስወገድ ስራ መስራት
  • የተሰብሳቢና ተከፋይ ሂሳቦች በተገቢው መረጃ ማደራጀት ተሰብሳቢዎችን በወቅቱ መሰብሰብ፣ተከፋዮችን በወቅቱ መክፍል
  • የካፒታል ፕሮጀክት በወቅቱ ጨረታ በማውጣት ግዢ እንዲፈፀሙ ማድረግና መከታተል፣
  • የመንግስት መመሪያዎች ደንቦች ተፈፃሚ እንዲሆን ማድረግ የተገልጋይ አመኔታ በተሻለ መልኩ ማሳደግ፣
  • በተዘረጋዉ የጥቆማና የቅሬታ አቀራረብ ስርዓት አማካኝነት የሚመጡ ጥቆማዎች፣ቅሬታዎችንና የስነ-ምግባር ጥሰቶችን በመለየት 100% ተግባራዊ ማድረግ፡፡
  • ማንኛውም የመንግስት ገቢ የተሰበሰበበት የገቢ ደረሰኝ አያያዝ ስርጭትና አመላለስ ምርመራ በማድረግ ለሚመለከተው አካላት ማቅረብ፣
  • ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ለማስፈን የአስተዳደራዊ ስራዎች ምርመራና ኦዲት ማድረግ፣
  • የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት መዘርጋት ፣የስጋት ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች ልዩ ትኩረት መስጠትና ምርመራ ማድረግ፣
  • የተቋሙ የውስጥ ኦዲት ስራ የመደበኛ በጀት ክፍያዎች፣ የግዢ፣የተራድኦ በጀቶች የንብረትና የአስተዳደራዊ ስራዎች ኦዲት በወቅቱ ማድረግና ሪፖርት በወቅቱ ለሚመለከተው ማስተላለፍ፣
  • ከተቋሙ ውጪ ያሉ የአፈር ማዳበሪያ፣ ጤና ጣቢያዎች፣ኦሞ ኤጀንቶች፣ ኦሞ ተቋም፣ ፍ/ቤት፣ት/ቤቶች፣እንስሳት ጤና ክሊኒኮች እና የገበሬ ማሰልጠኛ ተቋት በወቅቱ ኦዲት ማድረግና ወቅታዊ ሪፖርት ለሚመለከተው አካላት ማስተላለፍ
  • በልዩ ትዕዛዝ የሚጠየቁ የኦዲት ጥያቄዎች ወቅታዊ ምላሽ መስጠት፣
  • ከፑል ውጪ ያሉ ተቋማት የምክር አገልግሎት መስጠት ወቅታዊና ተገቢ ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣
  • የተቋሙ የሰው ሃይል አሰራሩን ተከትሎ በደረጃ እድገት፣በዝውውርና በቅጥር የሟሟላት ስራ መስራት፣
  • የተቋሙ የሪፎርም ስራዎችና አደረጃጀቶች በተቀመጠላቸው አግባብና ውጤት ሊያመጡ በሚችሉበት አግባብ መፈፀምና መምራት፣

በዚህ አመታዊ ዕቅድ ዘመን ይህ ትኩረት መስክ የወረዳውን ሀብት በማስተዳደር የማይተካ አሰተዋጽኦ የሚያደርግ የሴክተሩ ዋና የስራ ሂደት ሆኖ ይቀጥላል፡፡ ከዚህ አኳያ በቀጣይ በየዘርፉ በሴክተር መ/ቤቶች የሚታቀዱ የወረዳው ልማት ሥራዎችን ለማስፈጸም የሚመደበዉ ዉስን መደበኛና ካፒታል በጀት ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ ለመምራት የሚያስችል አሰራር ስርዓት በመዘርጋት ፣ በወረዳው በባለበጀት መ/ቤቶች የሚደለደለዉ ከተለያዩ ምንጮች የተገኘዉን ሀብት ፍትሃዊ እንዲሆን ልዩ ትኩረት ይሠጣል፡፡ በዚህም መሠረት በበጀት ዝግጅትና አሰተዳደርና፣  በፊስካል ፖሊሲ (ማዕቀፍ) ገቢ አሰባሰብ ስርዓት በመዘርጋት፣ በሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች የፕሮጀክቶች ጉዳይ ማስተባበርና በፕሮጀክት ድጋፍ የሚፈሰዉ ሀብት ስርጭቱ ፍትሃዊ እንዲሆን ማስቻል እና በባለበጀት መ/ቤቶች በኩል የሚፈሰዉ ሀብት ፍሰት ክትትልና የቁጥጥር ሥራዎችን ዉጤታማና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ በማሰተዳደርና በመምራት ላይ ልዩ ትኩረት ይሠጣል፡፡ በትግበራ ሂደት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ማነቆዎችን በመለየትና አሰራር ስርዓትን በመዘርጋት በአሰተማማኝ ሁኔታ ለመፍታት ልዩ ትኩረት የሚሰጠዉ ይሆናል፡፡

በክልሉ የወጡ የመንግስት ፋይናንስ አሰተዳደር የህግ ማዕቀፎችን መነሻ በማድረግ ጠቅላላ በወረዳው መንግስት ፍላጎትና አቅርቦት መካከል ለሚታየዉ ክፍተት ከተለያዩ የገቢ ምንጮች በገንዘብ ወይም በዓይነት ሀብትን በመሰበሰብ ለመንግሥት መ/ቤቶች ለመደበኛና ለካፒታል ሥራዎች የሚመደብላቸዉን ዉስን ሀብት ለተገቢና አግባብ ባለዉ የመንግስት አካል ለፀደቀ ዓላማ ብቻ በቁጠባ፣ በብቃት እና ዉጤትን በከፍተኛ ደረጃ ሊያስገኝ በሚችል መንገድ እንዲዉል በማድረግ፣ የመረጃ አያያዝ ሥራዓቱን በማዘመንና በማደረጃት የፋይናንሻል ሪፖርቶችንና ልዩ ልዩ መግለጫዎች በተቀመጠዉ ስታንዳርድ መሠረት በማዘጋጀት፣ በመተንተን፣ ተደራሽ በማድረግና በመቆጣጠር የማይተካ ሚና ያለዉ በመሆኑ የሴክተሩ ትኩረት መስክ ሆኖ ይቀጥላል፡፡ ከዚህም አኳያ ከወረዳ እስከ ቀበሌ ድረስ የተፈቀደዉን በጀት መነሻ በማድረግ ተዘጋጅቶ በሚቀርበዉ በጥሬ ገንዘብ ፍላጎት መርሃ ግብር መሠረት ገቢ መሰብስብ፣ ጥሬ ገንዘብ ማሰተላለፍ፣ ክፍያ መፈጸም፣ መረጃ ማደራጀት፣ መተንተን፣ ሪፖርቶችንና መግለጫዎችን ማዘጋጀትና ማቅረብ፣ ኦዲት ማሰደረግና ግብረ መልስ መሥጠትና የባከኑ ሀብቶች እንዲመለሱ የማስደረግ ስራ ትኩረት የሚሰጠዉ ጉዳይ ይሆናል፡፡ በዘመናዊ ተክኖሎጂ የመረጃ አያያዝ ስርዓትን በማዘመን፣ በመረጃ ጥራት ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በመለየት የሚሰራ ሲሆን ለዉስጥ ቁጥጥር ስርዓትን ልዩ ትኩረት በመስጠት በሚታዩ ኦዲት ግንኝቶች ላይ እርምጃ የሚወሰድበትን አሰራር ስርዓትን አጠናክሮ መቀጠል ልዩ ትኩረት የሚሰጠዉ ይሆናል፡፡

በአመታዊ ዕቅድ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር መዋቅሩን የሰው ኃይል በአመለካከትና በሙያ አቅም በማጠናከር፣ ግዥዎች ወጪ ቀጣቢ፣ ግልጽ፣ ከብክነት የፀዳ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ እንዲሆን ማስቻል እንዲሁም ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችለውን ከፍተኛ ፋይዳ (Value for money) ማስገኘቱን ማረጋገጥ እና ሁሉም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ፍላጎት በማሰባሰብና ግልጽ ጨረታ በማዉጣት ሕትመቶች፣ የተለያዩ ቁሳቁሶችና ማሽነሪዎች የሚገዙበት አሰራር መዘርጋት፣ በወቅቱ የንብረት ማስወገድ ሥራ በማከናወን የመንግሰት ንብረቶችን ከብክነት ማዳን፣ ክትትልና ድጋፍ በሁሉም መስክ ማጠናከር፣ የግዥና የንብረት አስተዳደር አፈጻጸም ኦዲት ተደርጎ ሪፖርቱን ተደራሽ ማድረግና የማስተካከያ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን መከታተል፣ በግዥ አፈጻጸምና ንብረት አወጋገድ ሂደት ላይ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ለመፍታት የሚያስችሉ ዉሳኔዎችን መስጠት፣ግዥና ንብረት አስተዳደር ስርዓቱን በጥብቅ ድስፕሊን መምራት እና የመንግስት ግዥዎች በጥራትና በወቅቱ የሚፈጸምበት አሰራር ስርዓት ማጠናከር እንዲሁም የመንግስት ግዥ ኮንትራት አስተዳደር ሥርዓት ላይ የሚስተዋለዉን ክፍተት አሰራርን በማጠናከር መፍታት ልዩ ትኩረት የሚሰጠዉ ይሆናል፡፡ በወረዳው ከፍተኛ የመንግስት ሀብት በሚፈስበት በመንግስት ግዥ ሂደት ውስጥ ገንዘብ ሊያስገኝ የሚገባውን ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዲያስገኝና የግዥ ሥርዓቱ ፍትሃዊ፣ ግልፅ፣ ውጤታማና ተጠያቂነት የሰፈነበት ሆኖ እንዲፈጸም እና የንብረት አሰተዳደር ሥርዓቱን በማዘመን የአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት ለመጨመርና ለመቆጣጠር የተዘረጋዉ አሠራር በመሪ ዕቅዱ በይበልጥ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ 

የተቋሙ አጠቃላይ ገፅታ

የደ/////ቤት በወረዳው ከተቋቋሙት ሴክተሮች ውስጥ አንዱ ሲሆን የተቋቋመበት ዋና ዓላማ የወረዳው የልማት እንቅስቃሴዎች በዕቅድ እንዲመሩ ለማስቻልና በተግባራት አፈፃፀም ረገድ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት አሰራር ይበልጥ እንዲሰፍን በማድረግ፣ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል እንዲረጋገጥና በቁጠባ ላይ የተመሰረት የሀብት አጠቃቀም ባህል በማዳበር ሴክተሩ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣንና ተግባር መሠረት በጀት ማዘጋጀትና ማስተዳደር፣ በተፈቀደው በጀት መሠረት ክፍያ መፈጸም፣ የበጀቱን አፈጻጸም መከታተል፣ መገምገምና መቆጣጠር፤ የበጀት፣ የሂሳብ፣ የክፍያና ጥሬ ገንዘብ እና የውስጥ ኦዲት ሥርዓት መዘርጋትና በስራ ላይ እንዲውል ማድረግ፣ ገንዘብና ንብረቶች መያዝና ማስተዳደር፣የወረዳው መንግስት የብድርና እርዳታ ስምምነቶችን መፈራረምና ከአጋር ድርጅቶች የሚገኘውን ሀብት ውጤታማ አንዲሆን በተቀላጠፈ አኳኋን ማስተዳደርና አፈጻጸሙን መከታተል፣ እንዲሁም ከክፍላተ ኢኮኖሚ ጋር ያለዉ ትስስር መገምገም፣ የወረዳውን የፋይናንስና ንብረት ኢንስፔክሽን ማከናወን፣እርምጃ መውሰድና እንዲወሰድ ማድረግ፣

ዘመናዊ የበጀት አስተዳደር፤ የሂሳብ አያያዝ፣ የግዥና የንብረት አስተዳደር፣ በኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት ዘርፍ የተሰማሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ማስተባበርና መቆጣጠር፤ ፕሮጀክቶችን የማበልጸግ፣ የማጽደቅና የመፈራረም ሂደትን የመምራትና የማስተባበር፤ አተገባበራቸውንም በመስክ የመከታታልና የመገምገም እንዲሁም የሀብት ፍሰትና ስርጭት ፍትሃዊነት እንዲረጋገጥ ማስቻል፣ የመንግስትና የግል አጋርነት እንዲጎልብት አሰራር ሥርዓት መዘርጋት፣ የመንግሥት ሀብትና ዕዳን የማስተዳደር እና በበላይነት የመምራት ዋና ኃላፊነት አለበት፡፡

 ስለሆነም አጠቃላይ የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት እንዲያስችል በተዘረጋው የስራ ሂደት ለውጥ ጥናቱን ተግባራዊ ለማድረግ ከሙከራ ወደ ሙሉ ትግበራ በመግባት አበረታች ውጤት በማስመዝገብ ላይ ይገኛል፡፡በዚህም መሰረት ሴክተሩ በ4 ዋና እና በ 2 ደጋፊ የስራ ሂደቶች የተደራጀ ነው፡፡

የደቡብ ሶዶ ወረዳ ፋይናስ ጽ/ቤትን ለማግኝት