የደቡብ ሶዶ ወረዳ ምክር ቤት

አቶ ጌታቸው ጋሹ
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ
ዓላማ
ዋና ዓላማ
የም/ቤቱ ተቋማዊ አደረጃጀት በማጠናከር እንደ ሀገር የተጣሉትን የብልጽግና ፍኖተ ካርታ በወረዳ ደረጃ በማሳካት የህዝቡን ቁሳዊ ፍላጎት፣ክብር፣የእኩልነትና ነጻነት ማረጋገጥ የዲሞክራሲ ባህል እንዲዳብር በማድረግ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚነት እና የስልጣን ባለቤትነት ወደ ላቀ ደረጃ እንዲሻገር ማድረግ ነው
ዝርዝር ዓላማ
- የሁሉም ዜጎች ቁሳዊ ፍላጎቶችን ፍትሀዊና እኩልነት በሰፈነበት መንገድ መተግበራቸው ማረጋገጥ
- የህዝቦች የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መቅረፍ
- የም/ቤቶች ተቋማዊ አደረጃጀት የተሟላ ማድረግ
- የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታው የላቀ ደረጃ ማድረስ
ተልዕኮ
የም/ቤቱ አሰራር በማሻሻል በህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ ለወረዳው ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዕድገት መፍጠር ፋይዳ ያላቸውን ህጎች በማውጣት አፈጻጸማቸው በመከታተልና በመቆጣጠር እና ቁርጠኛ የመንግስት አደረጃጀት የህዝብ የስልጣን ባለቤትነት እንዲረጋገጥ የግልጸኝነትና የተጠያቂነት ስርዓት እንዲሰፍን እና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲጎለብት ማድረግ ነው፡፡
- ረቂቅ ህጎችን መመርመርና ሙያዊ አስተያየት መስጠት
- አሳታፊነት ያረጋገጠ ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ያለው አገልግሎት ማሳደግና የህዝብ አመኔታ ማሳደግ
- መደበኛ ጉባኤ በዓመት 4ጊዜ እንዲሳካ ማድረግ
- በወጡ ህጎች ላይ ጥናት ማድረግ
- ቋ/ኮሚቴውን መደገፍና ማጠናከር ስኬታማ የክትትል ቁጥጥር ስራ መስራት
- ቀበሌ ም/ቤቶችን በተለያየ መንገድ የማጠናከር ስራ መስራት
- በዓመት 4 ጊዜ የምክክር መድረክ ማካሄድ
- ቃለ ጉባኤ በጥራት ማዘጋጀትና ማሰራጨት
- የም/ቤቱ ስራ በሚዲያ ለህዝብ ማስተላለፍ ናቸው
- ህግ ማውጣት
- ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ
- ውክልና ማረጋገጥ ናቸው
አቶ ጌታቸው ጋሹ
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ መልዕክት
ም/ቤቶች በሁሉም የእርከን ደረጃ ልዋላዊ የስልጣን ባለቤት በመሆናቸው የተጣለባቸው ሁላፊነት አንዱ የሌላኛውን ውሳኔ በማይሽር መንገድ እየ. ተገበሩ የሚሄዱ በመሆናቸው በየእርከኑ ተመሳሳይ ተልዕኮ ይዘው የሚሰሩ ናቸው ዋነኛ ተልዕኮአቸው፡ 1ኛ/ ውክል ና ማረ ጋገጥ 2 ኛ / ህግ ማውጣት እና 3 ኛ / ክትትልና ቁጥጥር :ማድረግ ናቸው። ስለዚህ: በየደረጃው ያሉ ምር ቤቶች የተጣለባቸው ኃላፊነት በተገቢው የመወጣት ግዴታቸው መሆኑ አውቀው ያልተቆራረጠ ህገ መንግስታዊ ጉባኤ በማካሄድ የወከላቸው ህዝብ ሊጠቅሙ የሚችሉ በላይኛው እርከን ከወጣ ዉ ፡ ህግ ጋር የማይጣረዙ ህግ በማውጣትና የወጣው ህግ ስራ ላይ ስለ መዋሉ ክትትልና ቁጥጥር አጠናክሮ፡ ማስቀጠል ይኖርባቸዋል ።በተጨማሪ የወረዳው ም/ቤት በማ/ኢትዮጵያ ክልል በምስረቅ፡ ጉራጌ ዞን በደ/ ሶዶ ወረዳ የሚገኝ በ4 ስራ ሂደት የተደራጀና በክትትልና ቁጥጥር ስራ የተቀላጠፈ እንዲሆን በ3ቱም ዘርፍ ቋ/ኮሚቴ ተደረጀቶ በተለያየ ስልት የክትትልና ቁጥጥር ስራ እየሠራ ይገኛል።
የሴክተሩ አጠቃላይ ገፅታ
ተቋሙ በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን በደቡብ ሶዶ ወረዳ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የራሱ የሆነ 5 የስራ ክፍል ያሉት በአሁኑ ሰዓት ከተፈቀደለት የሰው ሀይል 10 ይህሉን የያዘ በህዝብ ውክልና የተሰጣቸው 46 የተጣራ የም/ቤት አባላት ያሉት ሲሆን ከህነዚህ የተወጣጡ 3 ዘርፍ ቋ/ኮሚቴ በውስጣቸው አምስት አምስት አባላት በድምሩ 15 አባላት የያዘ ሲሆን 2ቱ ዘርፎች በቋሚነት ቋ/ኮሚቴ ሰብሳቢ በሹመት የተቀመጠለት ሲሆን 1 ዘርፍ በውክልና አገልግሎት የሚሰጥ ነው፡፡
phone Number
0463328811