የደቡብ ሶዶ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስ ፅ/ቤት

አቶ ታምራት መገርሳ
የደቡብ ሶዶወረዳ ፐብሊክ ሰርቨስ ፅ/ቤት ዋና ኃላፊ

ዓላማ

ዋና ዓላማ

የደ/ሰ/ወ/ፐብሊክ ሰርቪስ ና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት በተሰጠው ኃላፊነት መሠረት የተቋማትንየለውጥ ሥራዎች ፣ የሰው ሀብት ስራ አመራር ስርዓቶች፣የመልካም አስተዳደርን ያካተተ ዕቅድ ተዘጋጅቶ የተቋማትን የማስፈጸምአቅም በማጎልበት ተገልጋዩ ኅብረተሰብ የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኝ ስልቶችን በመቀየስ የመልካም አስተዳደርን  ለማስፈን እና ለዚህም በሶስቱም የትኩረት መስኮች የተቋማትየማስፈፀም አቅምመገንባትና ማብቃት ላይ የተለያዩ የክህሎት ማሳደግያ ስልጠናዎች በመስጠት የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ ማድረግ ነው

ዝርዝር ዓላማ

  • ፐብሊክ ሰርቪስ ውስጥ ውጤታማነት በማረጋገጥ ተቋማዊ ለውጥ ማምጣት
  • መልካም አስተዳደርን በማስፈን የተገልጋይ ህዝብ ማርካትን ማረጋገጥ
  • በተቋማት የኪራይ ሰብሳቢነት ምንጮች በማድረቅ ልማታዊና ዲምክራሲያዊ ፐብሊክ ሰርቪስ መገንባት

ተልዕኮ

  • በወረዳ የመንግስትን ፖሊሲዎችና ስትራቴጀዎች በብቃት ለመፈጸም የሚያስችሉ አዳዲስ አሰራሮችንና አደረጃጀቶችን በመዘርጋት፣ የአመራሩንና የሰራተኛዉን አመለካከት በመለወጥና ብቃቱን በማሳደግ፣ ህዝብን በቅንነትና በታማኝነት የሚያገለግል ጠንካራና ዉጤታማ የመንግሥት አገልግሎት መፍጠርነው፡፡
  • ችግር ፈቺነት፣
  • ቅድሚያ ለብቃትና ለልህቀት፣
  • ለለውጥ መስራት፣
  • ክብር ለተገልጋይ፣
  • ፍትሃዊነትና አለማዳላት
  • ቅልጣፌና ውጤታማነት
  • ቅንነት፣ ታማኝነትና አካታችነት፣
  • ሁሌም መማር፣
  • ሁሉ አቀፍ የአመራር ስብእና መላበስ
  • ጥራት ያለው፤ ቀልጣፋና ውጤታማ የሆነ አገልግሎት መስጠት
  • የሪፎርም ስራዎች ማጠናከር
  • የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመለየት እንዲፈቱ ማድረግ
  • ተቋማት የማስፈፀም አቅም መገንባት
  • የመልካም አስተዳደር ችግር መቅረፍ
  • የሰው ሀብት ስራ አመራርና ልማት

ተቋሙ በማዕከላዊ እትዮጵያ ከልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን በደቡብ ሶዶ ወረዳ ውስጥ  የሚገኝ  ሲሆን የራሱ የሆነ 5ዋና  የስራ ሂደት እና 2ደጋፊ የስራ ሂደት የጋራ አገልግሎት 2  ያሉት ሲሆን በአሁን ሰዓት የተፈቀደለት የሰው ሀይል 21 የተሸፈነ 9 በአጠቃላይ ኃላፊ ጨምሮ 11 ሰራተኛ እየሰራ  ይገኛል

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን በደቡብ ሶዶ ወረዳ ውስጥ 28 ሴክተር መ/ቤቶች   የሚገኝ ሲሆን

  • በዋና ስራ ሂደት የሚያስፈልግ 669 የተሸፈነ 233 አፈጻጸም 34 ፐርሰንት
  • በደጋፊ ስራ ሂደት የሚያስፈልግ 279 የተሸፈነ 90 አፈጻጸም 32 ፐርሰንት
  • የጋራ አገልግሎት የሚያስፈልግ 79 የተሸፈነ 37 አፈጻጸም 42 ፐርሰንት

   በድምሩ የሚያስፈልግ 1042 የተሸፈነ 379 አፈጻጸም 37 ፐርሰንት ላይ ይገኛል

ተቋማቶች የአገልግሎት አሰጣጥ እና የለውጥ ስራዎች ማሳለጫ ናቸው፡፡ የሰብአዊነት መጠበቂያና ፍትሃዊነት የህዝብ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተቋማት ናቸው ፡፡

  • ባሳለፍናቸው አመታት በርካታ ስኬቶቻችን ከላይ እስከታችኛው ተቋማቶች ሲመዘገቡ ቢቆዩም የተግባር አፈፃጸም ልዩነቶች ይስተውሉ ነበር ፡፡እነዚህም መንጠባጠቦች ከተወሰኑ አመታት በኋላ በተቀየሰው ጥረት ቀበሌዎቻችን እና ሴክተር መ/ቤቶች ከፍተኛ ለውጥ በማምጣት በዞን ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን በቅተዋል ፡፡
  • እንዲሁም በያዝነው በጀት አመት የተቋማት የማስፈጸም አቅም ግንባታ ፤የሰው ሀብት ስራ አመራር ስርዓት ማሻሻል ፡አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻል እና መልካም አስተዳደር ማስፈን 4ቱ የትኩረት መስክ ተግባራዊ በማድረግ ድንቅ ዉጤቶች ማየት ችለናል ፡፡ ዉስን ጉድለት ከነበረበት የተቋማችን አገልግሎት አሰጣጥ አፈጻጸም 92 ፐርሰንት ከፍ ማድረግ ተችሏል ፡፡ የክትትል ድጋፍ ስራዎች በተጠናከረ መንገድ በማስቀጠል በ 27 ሴክተር መ/ቤቶች እና 17 የገጠር ቀበሌዎች ላይ የለውጥ አደረጃጀት በማጠናከር በየ 3 ወሩ ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ በአፈጻጸም ወስንነት የተስተዋለባቸው  ሴክተሮች በልዩ ድጋፍ ማጠናከር የተቻለ ሲሆን ቀበሌዎችም  በቋሚነት በየወሩ የክላስተር ውይይት በማጠናከር የአገልግሎት አሰጣጥ ውስንነቱን በማረም ና ግብረ መልሰ በማውረድ ከነበረበት ከፍ ለማድረግ ተችሏል፡፡
  • በተመሳሳይ ደረጃ የተቋሙ የህዝብ ክንፍ እና ባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት ችግሮች እንዲቀረፉ ተደርጓል፡፡
  • ከአደረጃት አንጻር – በሴክተሮች 71 ቲም እና በቀበሌ ደረጃ 30 ቲም  የተደራጀ ሲሆን 450 አባላት ሳምንታዊ ተግባራቸውን በቲም እየገመገሙ ይገኛሉ፡፡
  • የጋራ የምክክር መድረክ የጽ/ቤቱ ውጤታማነት ማሳያ እንደመሆኑ መጠን ልምድ ሊሰጥ በሚችል መልኩ የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ቀበሌያት ; ሴክተሮች እና ፈጻሚዎችን በመለየት ከ 150’000 ብር በላይ ሽልማት በማበርከት በተቋማት በካከልና በፈፃሚዎች መካከል የውድድር መንፈስ ተፈጥሮ ተገልጋይ ተኮር አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጓ ፡፡ በአጠቃላይ ተቋማቶች የተጣለባቸው ሃላፊነት ለመወጣት በተቀመጠላቸው የትኩረት መስኮች መነሻበማረግ ተቋማዊ አሰራር በማስፈን  የመልካም አስተዳደር ችግሮች በፍጥነት በመቅረፍ ከባለድርሻ አካላት እና የህዝብ ክንፍን  የበለጠ በማሳተፍ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ አደራዬን ማስተላለፍ እወዳለሁ፡፡

የደቡብ ሶዶ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስ ፅ/ቤትን ለማግኘት