የደቡብ ሶዶ ወረዳ ት/ት ጽ/ቤት

አቶ እንዳለ ቡልቡላ
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ት/ት ጽ/ቤት ሀላፊ
ዋና አላማ
ዝርዝር አላማ
  • በየደረጃው የሚታየውን የአመለካከት፣ የክህሎትና የግብአት አቅርቦት ማነቆዎችን መፍታት፣
  • በሁሉም ት/ቤቶች የተመዘገቡ ህጻናት በየክፍሉ እያንዳንዱ ተማሪ በትምህርት አቀባበል ዝግጅት ያለበት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሁኔታ ተለይቶ መረጃ በመያዝ እንደየችግሩ ሁኔታ ድጋፍና ክትትል የሚደረግበት ስርዓት ይመቻቻል፡፡
  • የትምህርት ሰራዊት የገነቡ ተቋማት ቁጥርን 100% የማድረስ ስራ የሚሰራ ሲሆን ምቹ ሁኔታ ያልፈጠረ ተቋም አይኖርም
  • የመደበኛ ያልሆነ የጎልማሶች ማሰልጠኛ ጣቢያዎች በቀበሌ 6 ጣቢያዎች እንዲኖሩ ማድረግና የተከፈቱትን የመደበኛ ያልሆነ የጎልማሶች ትምህርት ጣቢያዎች በግብዓት የማጠናከር ስራ ይሰራል፡፡
  • በወረዳው ውስጥ ፍትሀዊነትና ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት በማድረስ ለልማትና ለፍትህ ለሰላምና ለዲሞክራሲ ግንባታ የተሰጡና የላቀ ሚና የሚጫወት ሀገሪቱን ሊረከቡ የሚችል ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ ትውልዶች ማፍራት ነው፡፡
  • የሴክተሩ የረጅም ጊዜ ዕቅድ
  • በወረዳው ውስጥ የሚገኙ ሁሉም የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣የቅድመ አንደኛ ክፍል ትምህርት ቤቶች እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እስፈላጊውን ግብዓት ቁሳቁስ እንዲሁም የሰው ኃይል በተገቢው እንዲሟላ በማድረግ ወረዳው ላይ የሚገኙ ኁሉም ት/ቤቶች 70%ቱ ደረጃ 3ላይ እና 30%ቱ ደረጃ 4 ላይ ማድረስ
  • የሴክተሩ የአጭር ጊዜ ተግባራት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት
  • የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ማረጋገጥ
  • የመምህራን አቅም ማጎልበት
  • በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ የመጀመሪያና መካከለኛ እንዲሁም 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ካሉበት ደረጃ 2 በ50% ወደ ደረጃ 3 ማሸጋገር መቻል
  • የተማሪዎች ውጤት ከነበሩበት በ50% ማሻሻል
  • የመረጃ ልውውጥ ስርዓት በቴክኖሎጂ መቀየር
  • እንደ ወረዳ በሴክተሩ ስር የሚገኙ ተቋማት
  • የቅ/አንደኛ ክፍል በመንግስት 47 በግል 3 አድምሩ 50 የቅ/አንደኛ
  • ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል በመንግስት 4 ተቋማት
  • ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል በመንግስት 20 ተቋማት በግል 1 ተቋም በድምሩ 21 ተቋማት
  • ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በመንግስት 3 ተቋማትን በመያዝ እንደ ወረዳ ከማህበረሰቡ ጋር በጋራ በመሆን እንዲሁም የተለያዩ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶችን በማስተባበር የተማሪዎችን ውጤትና ስነ-ምግባር እንዲሻሻል ከመቼውም ጊዜ በላይ እየተሰራ ይገኛል፡፡
  • የትምህርት ጥራቱን፣ሽፋኑን፣ ፍትሀዊነቱንና ብቃቱን ቀጣይነት ባለው መልኩ በማሻሻል በሁለንተናዊ ስብዕናው የታነፀ ትውልድ በመፍጠር ለወረዳው ዘላቂ ልማት ተገቢውን አስተዋፅፆ ማድረግ

ራዕይ(Vission)

በ2020 ዓ.ም በወረዳው ፍትሀዊነቱና ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት በማድረስ በእውቀት፣ በክህሎትና በአመለካከት የተስተካከለና ለልማት፣ ለፍትህ፣ ለሠላምና ለዲሞክራሲ ግንባታ የላቀ ሚና የሚጫወትና በገበያ ላይ ብቁ ተወዳዳሪ የሆነ ትውልድ ተፈጥሮ ማየት፡፡

ተልእኮ (Mission)

ፍትሀዊ፤ አካታች እና ተደራሽ የሆነ ጥራቱና አግባብነቱ የተረጋገጠ በመልካም አስተዳደር ላይ የተገነባ የህይወት ዘመን ትምህርትና ስልጠና አካል የሆነ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ትምህርት ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ለዜጎች ማቅረብ!!

  • አጠቃላይ የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ ተችሏል
  • የመጀመሪያ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ የሚሰሩ መ/ራን፤ ር/መ/ራን እና ሱ/ሮች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት እንዲኖራቸው ተደርጓል
  • የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የተማሪዎች መጠነ ማቋረጥ 0.5 % ዝቅ እንዲል ተደርጓል
  • የሰለጠኑ መምህራን በመጀመሪያ ደረጃ እና በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች 100%  እንዲሸፈን ተደርጓል
  • የተቀናጀ ተግባር ተኮር የጎልማሶች ት/ት በብርሃን ምዘና፤ በመሰረተ ትም/ት እና በክህሎት ስልጠና ትምህርት እንዲወስዱ ተደርጓል
  • ትም/ቤቶች በኢንስቴክሽ ስታንዳርድ መሰረት የደረጃ ምደባ ደረጃቸው ተሸሽሏል
  • በት/ቤቶች የሚማሩ ሴቶች ፆታዊ እኩልነት ተጠብቆ እንዲማሩ ማድረግ ተችሏል
  • የትምህርት ተሳትፎ እና ፍትሃዊነት ማሻሻል ተችሏል
  • በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ሁሉም የትምህርት እርከኖችና የትምህር አይነቶች የተማሪ መፅሀፍ ጥምርታ 1፤1 ማድረስ ተችሏል
  • የ6ኛ፤የ8ኛ እና የ12ኛ ብሄራዊና ክልላዊ ፈተና ውጤት መጠነ ማሳለፍ 100% እንዲል ተሰርቷል
  • ሃገር ወዳድነት
  • የባለቤትነት ስሜት
  • ብቃትና ዉጤታማነት
  • ፍትሃዊነት
  • ግልጸኝነትና ተጠያቂነት
  • የሃይማኖት እኩልነት
  • የህዝብ ጥቅም ማስቀደም/ለህዝብ ጥቅም ቅድሚያ መስጠት
  • መከባበር፣ ሀቀኝነት፣ መቻቻል
  • ሁሌም ለትምህርት ጥራት፣ መስራት
  • የላቀ ተሳትፎአዊነት
  • በጋራመሥራት፣ /በአገራዊ ራዕይ ላይ መግባባትና ከዚያም በየተቋማቱ ራዕይና በሚተገበሩ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎችና ዕቅዶች ላይ የጋራ ስምምነት ላይ መድረስ
  • ለለውጥ ዝግጁ መሆን፣
  • ለተገልጋይ የላቀ አክብሮት መስጠት፣
  • በእውቀትና በእምነት መምራት፣
  • ፈጠራና ችግር ፈቺነት አቅም ማጐልበት፣
  • የሁሉም ዜጎች መብቶችና ጥቅሞች በእኩልነት የሚጠበቁበት የዲሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት፣

ሠራተኞች በየሥራ ሂደቱ የተሠጠውን ዕቅድ መሬት የማስነካት ሚና እንዲጫወቱ እያንዳንዱ ሠራተኛ በቅንጅታዊ አሰራር ማስተሳሰር፡፡

የሴክተሩ አጠቃላይ ገፅታ

የደቡብ ሶዶ ወረዳ በማዕከላዊ ኢትዮጰያ በምስራቅ ጉራጌ ዞን ውስጥ ከሚገኙ ወረዳዎች አንዷ ናት ወረዳዋ በስተሰሜን ሶዶ ወረዳ በስተምስራቅ መስቃን ወረዳ በስተምዕራብ ኦሮሚያ ክልልና ሶዶ ወረዳ በስተምስራቅ በሶዶ ወረዳ ትዋሰናለች የወረዳው ርዕስ ከተማ ኬላ ስትሆን ከአዲስ አበባ በ113 ኪ.ሜ ከዞን ከተማ ቡታጅራ በ23ኪ.ሜ ከክልል ርዕሰ መስተዳደር ሆሳዕና በ113 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገናለች፡፡ወረዳዋ መልካዓ ምድራዊ አቀማመጧ ደጋዋ አካባቢ ወጣ ገባ /ተራራማ/ ቆላማው ክፍል ሜዳማ የበዛበት በ17 የገጠር ቀበሌዎችና በ2 ከተማ የተከፈለች ናት የአየር ንብረቷም 35%ቱ ደጋ 65%ቱ ወይና ደጋ ነው ፡፡የወረዳው አመታዊ የዝናብ መጠን አማካይ ከ801-1200ሚ.ሜትር ሲሆን የሙቀት መጠኑ ከ12.6-20 ዲግሪ ሴንቲግሬድ እንደሚደርስ ይታመናል፡፡የሴክተሩ መገኛ ቦታ፡- ማእከላዊ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን ደቡብ ሶዶ ወረዳ ኬላ ከተማበሴክተሩ ስር የሚከኙ ት/ቤቶች ብዛት፡- 28 ሲሆኑ ( 25 የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት 3 ሁለተኛና መሰናዶ ት/ቤት)የበሴክተሩ የሰው ሀይል፡- ከተፈቀደለት መደብ ወ=6 ሴ=7 ድ=12 ተሸፍኖ ስራዎች እየተሰሩመሆኑ

የደቡብ ሶዶ ወረዳ ት/ት ጽ/ቤትን ለማግኘት