በዳሙ ገነት ደብረ ሳማ ጂገና ቅ/ጎርጊስ

ይህ ደብር በዳሙ ገነት ደብረ-ሳማ ጂገና ቅ/ጎርጊስ በቅድመ አያቶቻችን ዘመን እንደተተከለ ከአባቶቻችን እንደሰማነዉ ከዚህ በታች በቅደም ተከተል እንገልጻለን፡፡በመጀመሪያ ደረጃ ደብሩ በ1110ዓ/ም (በአስራአንድአስር ዓ/ም) እንደተመሰረተ ይነገራል፡፡ ደብሩ 905ዓመታት ያስቆጠረ የጥንት ቤተ-ክርስቲያን መሆኑን አባቶች ያብራራሉ፡፡ ደብሩን የተከሉት አባቶች አቶ ቶበቱ ቀልቡ፣አቶ መነቁ ንጉስ፣ገመሮ ንጉስ አልፈም፣ስልጢ ላንካሱ፣ነመጦ አርቢቶ፣ንጉስ ስበቶ እንዲሁም ሰራጋ የሚባሉ አባቶች ቀስቃሾች የቀ/ጊዮርጊስ ጽላተ ህግ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ከነበሩት አቡነ ፔጥሮስ አቤቱታ አቅርበዉ በዳሙ አከባቢና ዙሪያዉ አከባቢ አንድም ቤተክርስቲያ አለመኖሩን አስመስክረዉ ተፈቀደላቸዉ ታቦተ ህጉ በካህናት እጅ ጅገና ተብሎ በሚጠራዉ ስፍራ በትንሽ መቃኞ ቤት አርፎ በየወሩ እየተቀደሰ ለብዙ ዓመታት እንደቆየ ከአዋቂዎች ተረድተናል፡፡

ቀጥሎ ዘመንን እና ዓመት ምህረትን የሳር ክዳን ቤተ መቅደስ ከላይ ስማቸዉ የተጠቀሱት አባቶች የዳሙ ህዝብን በማስተባበር አሰርተዉ ከጨረሱ በኁላ ከነበሩበት ደሳሳ መቃኞ ወደ ተሻለ ዉቤት መቅደስ ዉስጥ አሳርፈዉና ቄስ አሉ ከሚባለዉ ጎሳፊት አዉራሪ ፈረደች አማካኘነት ከጎርደና ክፍለ ሃገር አስመጥተዉ ለመጡት ካህናት የሚያርፉበትና ለልማት የሚሆን የእርሻ ቦታ ተሰጥቶቸዉ በየሳምንቱ እየቀደሱ መቀደሻ የሚሆን መብዓ የዳሙን ህዝብ በአጠቃላይ ቅደም ተከተሉን ጠብቆ ለቄሰ ገበዙ ገቢ በማድረግ ለብዙ ዓመታት እንደቆየ የሚታወቅ ነዉ፡፡

ቀጥሎ የሳሩ ቤተ መቅደስ እያፈሰሰ በማስቸገሩ የአቶ ጨነቆ ችባ ልጅ የሆኑት አቶ አዋሽ ችባ የተባሉት የሃገሩ ተወላጅ ቆርቆሮ ገዝተዉ አና ጺአዘጋጅተዉ አሰርተዉ የተሻለ ሂወት እንዲረዉ 1979ዓ/ም ድረስ ቆይቶ አሁን የሚታየዉ ቤተመቅድስ 1979ዓ/ም  ግንባታዉ ተጀምሮ 1985ዓ/ም ስራዉ ተጠናቆ ሚያዚያ 23/08/1985ዓ/ም የአባታችን ተክለ ሃይማኖት ተቦተ ህጉ ተደርቦ በደመቀ ሁኔታ ተከብሩ አሁን ባለዉ መንበር ይገኛል፡፡