የደቡብ ሶዶ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት


አቶ ደሳለኝ ለገሰ ከበደ

ዋና ዓላማ

:-ፍትሃዊ የንግድ አሰራርና ዘመናዊ የግብይት ስርዓትን በመዘርጋትና መልካም አስተዳደርን በማስፈን የንግዱ ማህበረሰብና ሸማቹን ህብረተሰብ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ እርካታ ደረጃውን ከፍ ማድረግ ነው፡፡

ዝርዝር ዓላማ

  • በሥራ ሂደቱ ፈፃሚዎችና የሥራ ሂደቱ አስተባባሪ እንዲሁም በበላይ ሥራ አመራር መካከል የሚገባ የውል ስምምነት ሠነድ በመሆን እንዲያገለግል፣
  • የሥራ ሂደቱና የሴክተሩ የጋራ ዓላማና ፍላጎት ለጋራ ስኬት መሆኑን ለማሳየት፣
  • የሥራ ሂደቱና ፈፃሚዎች የተቀመጠላቸውን የሴክተሩን ፕሮግራምና የስራ ሂደቱን ተልዕኮ ለማሳካት አኳያ አፈፃፀማቸውን የሴክተሩን ፕሮግራምና የስራ ሂደቱን ተልዕኮ ከማሳካት አኳያ አፈጻጸማቸውን በግልጽ ለማሳየት፣
  • የሥራ ሂደቱ የጣለውን ግብ በተቀመጠው ስታንዳርድ መሠረት እየፈፀመ መሆኑን ወይም አለመሆኑን ለመከታተል፣
  • የሥራ ሂደቱ የግቦችን አፈፃፀም ወሰንና ኃላፊነቱን በግልጽ እንዲያወቅና እንዲረዳ፡፡
  • የሥራ ሂደቱ ፈጻሚዎች ስራቸውን በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሠረት እየፈጸሙ መሆኑን ወይም አለመሆኑን ለማሳየት፣
  • ፈጻሚዎች የየድርሻቸውን የአፈጻጸም ወሰንና ኃላፊነታቸውን በግልጽ እንዲያውቁ ለማገዝ፡፡
  • በዕቅድ እንመራለን፣
  • ፍትሃዊ አሳታፊና ዲሞክራሲያዊ አመራር መለያችን ነው፣
  • በማያቋርጥ ለውጥና መሻሻል እናምናለን!
  • ጊዜ እና የሰው ኃይል ካሉን ሀብቶች ሁሉ ቁልፍ ሀብቶቻችን ናቸው፣
  • ኪራይ ሰብሳቢነትን እንፀየፋለን፣
  • መረጃን ለልማት እናውላለን፣
  • ውጤት ያሸልማል፣
  • ተገልጋዮቻችን የሕልውናችን መሠረት ናቸው!
  • ቅሬታ አቅራቢዎች መካሪዎቻችን ናቸው!

ራዕይ

ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶች በዓይነት፣ በመጠንና በጥራት አድገው፣ በቀጣይ ዕድገት ላይ የተመሰረተና በዓለም ተወዳዳሪ የሆነ ዘመናዊ፣ ህጋዊና ፍትሃዊ የንግድና ግብይት ዘርፍ በ2023 ዓ.ም ተፈጥሮ ማየት፡፡

ተልኮ

በወረዳው የነጻ ገበያ መርህ የተከተለ ንግድና ግብይት በማዘመን፣ በማስፋፋት፣ ህጋዊነትና ፍትሃዊነት በማስፈን የሸማቹን ህብረተሰብና የንግዱን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፡፡

  • አዲስ የንግድ ምዝገባ አገልግሎት መስጠት
  • አዲስ የንግድ ፍቃድ አገልግሎት መስጠት
  • የንግድ ፍቃድና ዕድሳት አገልግሎት መስጠት
  • የምክር አገልግሎት መስጠት
  • የስነ-ልኬት ምርመራ ማድረግ
  • የተመደበ የፍጆታ ምርት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ
  • ወቅታዊ የገበያ መረጃዎችን በዘመናዊ መንገድ በመሰብሰብ፣ በማጠናከርና በመተንተን ለአምራቱ፣ ለአርቢው፣ ለነጋዴዎቹና ለሸማቹ ተደራሽ ማድረግ
  • ማንኛውም ነጋዴ ሸማቹን ለመጉዳት የሚፈፀሙ ተገቢ ያልሆኑ ተግባራትን መከታተልና መከላከል
  • በሸማች ጤንነትና ደህንነት ላይ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ምርቶች /ሸቀጦች/ አገልግሎቶች ላይ ስለሚገኙ ጉድለቶች  ክትትል ማድረግ
  • የገበያ ትስስር የሚፈጠርለት የአገዳ ሠብል ምርት
  • የገበያ ትስስር የሚፈጠርለት የብርዕ ሰብል ምርት

ቆዳና ሌጦ በግል ተዋናይ ለማዕከላዊ ለገበያበደረሰኝ መሸኘት 

አቶ ደሳለኝ ለገሰ ከበደ

የደቡብ ሶዶ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ መልዕክት

በወረዳችን ፈጣንና ቀጣይነት ያለውን ልማት ለማረጋገጥ በሚደረገው ርብርብ የበኩሉን ለመወጣት የለውጥ ሠራዊት ግንባታ ላይ የነጋዴ ሴቶች ማህበር፣ የእህል ነጋዴዎች እና የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በማቋቋም መብትና ግዴታቸውን እንዲወጡና ኢኮኖሚያቸው እንዲያሳድጉ ከሌሎች አካባቢ ከሚገኙ የንግዱ ህብረተሰብ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የግንዛቤ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና የኪራይ ሰብሳቢነት ምንጭ የሚሆኑ በሮችን በመዝጋት አገልግሎት ተቀባዩ ህብረተሰብ ከሴክተሩ የሚፈልገውን አገልግሎት በላቀ ደረጃ ለማበርከት  እንዲያስችል ለልማታዊ ባለሀብቱ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት፣ለህገ-ወጥ ንግድ መስፋፋት የማይመች አካባቢ በመፍጠር፣ የሸማቹን ግንዛቤ በመፍጠርና የመደራደር አቅም በማሳደግ፣ ከንግዱ ማህበረሰብ አደረጃጀቶች ጋር ተቀናጅቶ በመስራት የንግድ እና ግብይት ሥርዓትን ከማዘመን አንፃር የዳታ መቆራረጥ ችግር በኦን ላይን አገልግሎት ለመስጠት ስለተቸገርን ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ በትኩረት ጥረት እያደረግን መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

የደቡብ ሶዶ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤትን ለማግኝት