
ታዋቂ አትሌቶች፣ አርቲስቶችና ጋዜጠኞች በእጦጦ እፀዋት ማዕከል ችግኝ ተከሉ
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በአዘጋጀው የችግኝ ተከላ መርሐግብር በፓሪስ ኦሎምፒክ የድል ባለቤት የሆኑ አትሌቶችን ጨምሮ ታዋቂ አርቲስቶች ፣ጋዜጠኞችና ቲክቶከሮች በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ዛሬ ችግኝ ተክለዋል።



የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ብልለኔ ስዩም እንደገለፁት፣ ሁላችንም የአየር ንብረት ለውጥ አደጋ ስጋትን ለመከላከል ችግኝ መትከል አለብን። በአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር በመሳተፍ የአካባቢያችን ስነምህዳር መጠበቅ ይኖርብናል ብለዋል።

አትሌት ታምራት በበኩሉ ችግኝ ህይወት ነው። ለድል የበቃውትም በደን በተሸፈነው እንጦጦ ተራራ ተለማምጀ ነው። ሁሉም ዜጋ ችግኝ መትከልን ባህል ማድረግ እንደሚገባ ገልጿል።
(ኢ ፕ ድ)