የምስራቅ ጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢንሼቲቭ ( ኢትዮ ኮደርስ) መርሃ ግብርን በድምቀት አስጀምሯል!!

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢንሼቲቭ ( ኢትዮ ኮደርስ) መርሃ ግብርን በድምቀት አስጀምሯል!!

የ5 ሚሊየን ኢትዮጵያ ኮደርስ ኢንሼቲቭ ( ኢትዮ ኮደርስ) ስልጠና መርሃ ግብር በዞኑና በክልሉ መቀመጫ ቡታጅራ ከተማ ውስጥ ከፍተኛ ባለ ድርሻ አካላት በተገኙበት የማስጀመሪያ መድረክ መካሄድ ጀምሯል።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የማዕ/ኢት/ክ/መ/ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ከበደ ሻሜቦ፣ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ደሱ አበጋዝ፣ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘነበ መዱን ጨምሮ የኢትዮ ቴሌኮም ተወካይ፣ የመብራት ሃይል ተወካይ፣ የዞን መምሪያ ኃላፊዎች፣ የየወረዳውና ከተማ አስተዳደር አስተዳዳሪዎችና ከንቲባዎች፣ የየመዋቅሩ የሳኢቴ ጽ/ቤት ኃላፊዎችና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም

ከወጣቶችና ሴቶች ሊግ ጀምሮ ሌሎችም ወጣቶች እየተሳተፉበት ያለ ሲሆን በቀጣይ የበርካታ ኢትዮጵያውያን ስራ አጥነት ችግር የሚፈታ ነው የሚል ተስፋ እንደተጣለበትም ተገልጿል።

በአጠቃላይ ይህ ስልጠና በከፍተኛ ተነሳሽነትና ተግባር ሊከናወን ዝግጅት መጠናቀቁን ተገልፆ፣ በዞኑ ሁሉም የከተማና የወረዳ መዋቅሮች የሚሠጥ መሆኑንም ታውቋል።

ሰልጣኞች በተዘጋጀላቸው ቦታ በአግባቡ ተገኝተው እንዲሠለጥኑ በማሳሰብ፤ ለስኬታማነቱም ቴክኒክና ሙያ ተቋማትን ጨምሮ ሁሉም ተቋማት የበኩላቸውን በማድረግ፣ አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ትውልድ መፍጠር ይገባልም ተብሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *