
መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚገኙ አቅሞች በመጠቀም ወጣቱ ወደ ስራ ለማስገባት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ተገለፀ።


በደቡብ ሶዶ ወረዳ በጎልቤ ቀበሌ በንብ ማነብ የተደራጁ የእድገት በአንድነት ማህበር በኤሶ ኤስ ሳህል ድጋፍ የተደረገላቸው ንቦች ሊመገቡት የሚችል የአበባ ተክል በዛሬው ዕለት መትከል ችለዋል።
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሰራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ባሳዝን ይፋ በቦታው ተገኝተው እንደገለፁት በተያዘው በጀት ዓመት ከተደራጁ ኢንተርፕራይዞች መካከል የጎልቤ ቀበሌ እድገት በአንድነት የንብ ማነብ ማህበር በኤሶ ኤስ ሳህል ድጋፍ ወደ ስራ ለማሳገባት ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ገልፀዋል።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ግብረሰናይ ድርጅቱ በተለያዩ ቀበሌዎች ለተደራጁ ወጣቶች በተለያዩ የስራ መስኮች ላይ አሰማርቶ እየደገፈ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው በዘንድሮ በጀት ዓመትም እድገት በአንድነት የንብ ማነብ ማህበርን በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ለማስገባት 10 የንብ ቀፎዎች በማስገባትና ንቦች ሊመገቡት የሚችል የአበባ ችግኞች በማስገባት እየተተከለ መሆኑንና በቀጣይ የማር መጭመቂያና ማጣሪያ ማሽን መዘጋጀቱን አብራርተዋል።
ፅ/ቤቱ በ2017በጀት ዓመት በገጠርና በከተማ 4ሺ 4መቶ84 ስራ አጦች ለመለየት አቅዶ 4ሺ 2መቶ 92ወጣቶች መለየት መቻሉንና በቀጣይ የቅድመ ዝግጅት ስራና የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ በነሃሴ ወር ውስጥ እንደሚሰጥ ኃላፊው ጠቁመውናል።
እንደ ወረዳ ያሉትን ፀጋዎችን ተለይተው ለወጣቶች የስራ እድል እየተፈጠረ መሆኑን ያነሱት አቶ ባሳዝን ከግብርና ሚኒስቴር በተገኘ ድጋፍ ለ30 ወጣቶች የስራ እድል የሚፈጥርና በመንግስት ስራ ለማሰማራት የልየታና የምዝገባ ስራ እየተከናወነ መሆኑንና ከወረዳው ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ጋር በመሆን ወጣቶች በኢትዮ ኢኮደርስ ስልጠና ላይ ተሳታፊ ለማድረግ ስራ መሰራቱን አመላክተዋል።
የእድገት በአንድነት የንብ ማነብ ማህበር ሰብሳቢ የሆኑት ወጣት ታምራት ሲሳይ እንደገለፁት 1ለ5 ተደራጅተው ንቦች ወደ ውስጥ ለማስገባት የቅድመ ዝግጅት ስራ እየሰሩ እንደሆነ ገልፀዋል።
በዛሬው እለትም በኤሶ ኤስ ሳህል ግብረሰናይ ድርጅት ድጋፍ የተዘጋጀላቸው ለንቦች ምግብነት የሚውል የአበባ ችግኝ በመትከል ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
በቀጣይ ንቦቹ ወደ ውስጥ በማስገባት ስራ በመስራት በማስፋፋት ውጤታማ ሆነው ለሌሎች ጭምር የስራ እድል ለመፍጠር እቅድ አቅደው እየሰሩ መሆኑን አቶ ታምራት አመላክተዋልሲል የዘገበዉ የደቡብ ሶዶ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።