
ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በሚል መሪ ቃል 4 ሄክታር መሬት በጤፍ ሰብል መሸፈን መቻሉ ተገለፀ።
በዘንድሮ ዓመት ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በሚል ሀሳብ የእርሻ ዝግጅት ከተጠናቀቀለት 8 ሄክታር መሬት ውስጥ በዛሬው እለት 4 ሄክታር መሬት በጤፍ ሰብል መሸፈን መቻሉን የደቡብ ሶዶ ወረዳ ግብርና ፅ/ቤት አስታወቀ።
በዛሬው እለት በኬላ ዙሪያ ቀበሌ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የዘር መዝራት ማስጀመሪያ ፕሮግራም የደቡብ ሶዶ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የትምህርት ቤቶች ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ እንዳለ ቡልቡላ፣ የወረዳው ረዳት የመንግስት ተጠሪና የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት የፖለቲካና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታደለ ብርሃኔ፣ እንዲሁም ረዳት የመንግስት ተጠሪና የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሞገስ አባይ፣ የግብርና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው ማሩና የቀበሌው አስተዳዳሪ አቶ ዳኜ ታደለ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተውበታል።
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ግብርና ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ እንዳልካቸው ማሩ እንደገለፁት መንግስት ባስቀመጠው መሰረት ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በሚል ሀሳብ የሚታረሱ መሬቶች እንደወረዳ ዕቅድ ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱና የተረጂነት አመለካከት አስወግዶ የራስን አቅም አሟጦ በመጠቀም ለማልማት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።
እንደ ክልል ለተግባሩ 25 ሄክታር መሬት መሰጠቱን የጠቁሙት ኃላፊው በዘንድሮ በጀት ዓመት በወረዳ ደረጃ 8 ሄክታር መሬት የእርሻ ዝግጅት ማጠናቀቃቸውና በዛሬው እለት በኬላ ዙሪያ ቀበሌና በአጋም ሰናዶ ቀበሌ 4ሄክታር መሬት በጤፍ ሰብል መሸፈኑን ገልፀዋል።
ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሻገር ሊታረሱ የሚችሉ መሬቶች በማረስ በራስ አቅም ለመሸፈንና ለተጠባባቂነት የእህል ክምችት ለክልሉ በማበርከት ጭምር እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን አቶ እንዳልካቸው ጠቁመዋል።
በመጨረሻም ኃላፊው እንዳሉት በቀጣይ ቀናትም ቀሪ የእርሻ ዝግጅት የተደረገባቸው መሬቶች በተለያዩ ሰብሎች እንደሚሸፈኑ አስፈላጊው ግብአት በመስጠት በበጀት ዓመቱ ከ50 እስከ 60 ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ አመላክተዋል።
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የትምህርት ቤቶች ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ እንዳለ ቡልቡላ በዘር ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው እንዳሉት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራው ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ኢኒሼቲቭ ማህበረሰቡ ከተረጂኑት አስተሳሰብ ወጥቶ እራሱን በምግብ የሚችልበት ሁኔታ ለመፍጠር ሰፊ ንቅናቄ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
እንደወረዳ ያሉ አማራጮችን በመጠቀም በዘንድሮ በጀት ዓመት 8 ሄክታር መሬት ቅድመ ዝግጅት ስራ አጠናቀው መሬቶቹ በተለያዩ ሰብሎች ተሸፍነው እስከ 60 ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
በተጨማሪም አቶ እንዳለ እንዳሉት በዛሬው እለት በሁለት ቀበሌዎች 4 ሄክታር መሬት በጤፍ ሰብል ዘር በመዝራት መሸፈኑን አንስተዋል።
የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት እና በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰቱ አደጋዎች በራስ አቅም ለመሸፈን በቀጣይ በሁሉም ቀበበሌዎች ያሉ ያለሙና ያልታረሱ መሬቶችን የማጥራት ስራ ተሰርቶ በተሟላ አቅም በበጀት ተደግፎ የሚከናወን እንደሆነ አመላክተዋል ሲል የዘገበዉ የደቡብ ሶዶ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

