መላዊ የኢትዮጲያ ህዝቦችና የየአትሌቲክስ አፍቃሪዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ!!!!

በ33ኛው የፓሪስ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

ዛሬ በተካሄደው የወንዶች የማራቶን ውድድር አትሌት ታምራት ቶላ 1ኛ በመውጣት ለሀገሩ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝቷል።

ከ2 ዓመታት በፊት በአሜሪካ ኢዩጂን በተደረገው የዓለም ሻምፒዮና የርቀቱ አሸናፊ የነበረው ታምራት፤ ከ21 ኪሎ ሜትር ጀምሮ ውድድሩን በልዩነት እየመራ በማጠናቀቅ ነው የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት የሆነው።

#EBC

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *