ሐምሌ 24/2016 ዓ.ም ኬላ
የደቡብ ሶዶ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲያካሄድ የነበረው የአመራር ምዘና ተጠናቀቀ።
የፓርቲ እና የመንግስት ስራዎች የዕቅድ አፈፃፀምን መነሻ በማድረግ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው የአመራር ምዘና በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።የደቡብ ሶዶ ወረዳ ዋና የመንግስት ተጠሪና ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ጋሻው ተረፈ በመድረኩ ማጠቃለያ እንዳሉት ምዘናው የተግባርና የአስተሳሰብ አንድነት የምንፈጥርበት እንደሆነ በመረዳት አመራሩ በቀጣይ በተግባር ተቀራራቢ ውጤት ማምጣት የሚችልበት እድል የሚፈጥር እንደሆነ ገልፀዋል።: ሐምሌ 24/2016 ዓ.ም ኬላ



አመራሩ ተቋማዊ አሰራር ተክሎ ጊዜ ሰጥቶ የመንግስትና የፓርቲ አደረጃጀት በእግሩ እንዲቆም ስራ መስራት ይጠበቅበታል ያሉት ኃላፊው አመራሩ ከችግር ሊወጣ የሚችልበት ግምገማ እንደሆነ በመገንዘብ ከእቅድ ዝግጅት ጀምሮ ሀገራዊ ግቦችን ሊያሳካ የሚችልና ጥራቱን የጠበቀ እቅድ አቅዶ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
በመንግስትና በፓርቲ የተጀመሩ የኢኒሼቲቭ ስራዎች ተግባራዊ ለማድረግ እንደወረዳ የተጀመሩ ስራዎች በውስን መንደሮች ብቻ ሳይሆን በቀጣይ ሁሉ አቀፍ ተደራሽነት የማስቀጠል ስራ ላይ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
በመጣንበት ዓመት በርካታ ስራዎች ሲሰራ እንደነበር በተለይም ከገቢ ስራ፣ ከትምህርት ስራ፣ በግብርናው፣ በመንገድ ዘርፍ በሁሉም ስራዎቻችን ውጤታማ እንደነበረ በመግለፅ በቀጣይ ጉድለቶቻችን ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል።
በመጨረሻም አቶ ጋሻው እንዳሉት ከሚዲያ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ፌክ አካውንትች በመታገል የመንግስት ሚዲያ አጉልተን በማውጣት የተሰሩ ስራዎች ለህዝብ የማድረስ ስራ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መስፍን አድማሱ በማጠቃለያቸው እንደገለፁት የምዘናው ዋና አላማ የአመራሩ የተግባር፣ የአመለካከትና የአስተሳሰብ አንድነት ሊፈጥር የሚችል እንደሆነ በመረዳት ከግለሰብ ፍላጎት በመውጣት የማህበረሰባችን ተጠቃሚነት ሊያስቀጥል የሚችልና የፓርቲው ቅቡልነት ሊያረጋግጥ የሚችል እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል ብለዋል።
ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ በሁሉም ተቋማት ላይ የሚታዩ ጉድለቶች በቀጣይ መታገል እንደሚያስፈልግ በመግለፅ ከብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘ እንደወረዳችን ጎልቶ የሚታይ እንደሆነና ትልቅ ስራ የሚፈልግ እንደሆነ በመረዳት አገልግሎት በገንዘብ እየተሰጠ እንደሆነ በርካታ ማሳያዎች መኖራቸውን የገለፁት አቶ መስፍን በቀጣይ ቅንጅታዊ አሰራር በመከተል የህዝብ ተጠቃሚነት ሊረጋገጥ ይገባል ብለዋል።
የፓርቲያችን ትልቁ ተልዕኮ ተቋም መገንባት ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው አመራሩ ተግባር ቆጥሮ ሰጥቶ ቆጥሮ ከመቀበል አንፃር ጉድለት መኖሩን አመራሩ በተገቢው ተገንዝቦ ስራ መስራት ይጠበቃል ብለዋል።
የመንግስትና የፓርቲ አደረጃጀቶች በማጠናከር እስከታችኛው መዋቅር በመውረድ ከአስተሳሰብ ጀምሮ ስራ መስራት እንደሚያስፈልግ በመግለፅ በተለይም የወጣትና የሴቶች አደረጃጀት በማጠናከር በተለይም ህዋስና መሰረታዊ ድርጅት አሰራር ተክሎ እንዲሄድ በማድረግ ሰፊ ስራ መሰራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።
ከሚዲያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ አመራሩ መሰረታዊ ጉድለት እንዳለበት በመግለፅ በቀጣይ የመንግስትና የፓርቲ ሚዲያ የሚለቀቁ መረጃዎች ለህዝብ ከማድረስ አንፃር ውስንነት እንዳለ በመረዳት በቀጣይ አመራሩ ሊያግዝ ይገባል ብለዋል።
በመጨረሻም የምዘናው ዋና አላማ አመራሩ ከመጠራጠር ወጥቶ ሙሉ ጊዜውን ስራ ላይ ሊያውል እንደሚገባና የስራ ተነሳሽነት የሚፈጥር እንደሆነ መረዳት ይገባል ያሉት አቶ መስፍን በቀጣይ ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ሀገራዊና ክልላዊ ኢኒሼቲቮች ፣ የገቢ ስራችን ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል በማለት አፅዕኖት ሰጥተዋል ሲል የዘገበው የወረዳው መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።
ፈጣን መረጃ እንዲደርሶ የፔጃችን ተከታይ ይሁኑ!!





Views This Year : 50