ሐምሌ 18/2016 ዓ.ም(ኬላ)

የደቡብ ሶዶ ወረዳ ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ የዲጂታል ፕላትፎርም ሆኖ የሚያገለግለውን ወረዳዊ ድህረገጽ በማበልፀግ አየር ላይ መዋል መቻሉን ተገለፀ።

የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ከምስራቅ ጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ጋር በመተባበር የደቡብ ሶዶ ወረዳ ወረዳዊ ድህረገጽ ልማት የእውቅና ፕሮግራም መድረክ አካሄደ።
 
 
 
በመድረኩ ማስጀመሪያ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዴ ቀበሌ በመሬት መንሸራተት ሳቢያ ህይወታቸው ላጡ ወገኖች የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ መድረኩ ተጀምሯል።
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መስፍን አድማሱ በመድሩኩ መክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት የወረዳዊ ድህረገጽ ልማት ማልማት ላይ ሁሉም የሴክተር አመራሮችና ባለሙያዎች የእንኳን ደስ አላቹ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የድረገጽ ዋነኛ ፋይዳ የሆነው ወረዳውን እንዲሁም አካባቢውን የምናስተዋውቅበትና ወረዳው ላይ ያሉ ፀጋዎች በተገቢው የምንሸጥበትና መረጃዎች የምንለዋወጥበት መሆኑን አቶ መስፍን ጠቁመዋል።
እንደሀገር የተያዘው የዲጂታል አገልግሎት ውጤታማ ለማድረግ የለሙ ድህረገጾች ተግባራዊ በማድረግ ስትራቴጂውን ከወረቀት ነፃ የሆነ አገልግሎት መስጠትና መረጃዎች አብዴት በማድረግ ወደ ዲጂታል አለሙ መቀላቀል ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
ድህረገጹ በወረዳ ደረጃ እውን ማድረጉ እንደ ትልቅ እድል መያዝ እንደሚገባ የገለፁት አቶ መስፍን ባለሙያዎች በሚሰጡት ሃሳብ በመያዝና ለቴክኖሎጂው የምንሰጠው ትኩረት በማሻሻል የወረዳውን ፀጋዎች ማስተዋወቅና መሸጥ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ደመላሽ ውዴ ንግግር ባደረጉበት ወቅት እንደገለፁት የወረዳው ፕላትፎርም ከብዙ ውጣ ውረድ በኃላ በልፅጎ አየር ላይ ለማዋል በመብቃቱ የእንኳን ደስ አላቹ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ድህረገጽ ለየት የሚያደርገው እንደ ሀገር ከዕዳ ወደ ምንዳ የስልጠና መርሃ-ግብር ላይ ከተቀመጠው የዲጂታል ኢኮኖሚ ልማት ግንባታ እስትራቴጂ አንድ ማሳያ መሆኑን እንደሆነ አቶ ደመላሽ ተናግረዋል።
የወረዳው ድህረገጽ ከሌሎች ያለሙና እያለሙ ያሉ መዋቅሮች ድህረገጾች ጥሩ ተሞክሮ ሊሆን የሚችል ድረገጽ መሆኑን በዞንና ከክልል ከፍተኛ ባለሙያዎችና አመራሮች ዕውቅና መሰጠቱ ለየት እንደሚያደርገው አንስተዋል።
ድህረገጽ በማበልፀግ ሂደቱ ላይ መረጃ ከመስጠት ጀምሮ ሲያግዙ የነበሩ ተቋማት፣ የዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ፣ እንዲሁም የፅ/ቤቱ የማኔጅመንት አካላት በፅ/ቤቱ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ባለሙያ የሆኑት አቶ ናትናኤል ይልማሸዋና አሸናፊ ሃይሉ ድህረገፁ ውስጡ ላይ የያዘው ሃሳብና እንዴት መጠቀም ይቻላል የሚል ሃሳብ በዝርዝር አቅርበዋል።
ተሳታፊዎች በሰጡት ሃሳብ እንደገለፁት በወረዳው በበጀት ዓመቱ ከተሰሩ ስራዎች ውስጥ ዋነኛው ስራ በመሆኑ ከወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት እስከ ዞን መምሪያ ድረስ ወረዳዊ ድህረገጽ ማበልፀግ ላይ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
የበለፀገው ድህረገጽ ትኩረት ተሰጥቶት መሰራቱን ያነሱት ተሳታፊዎች በቀጣይ ድህረገጽ ሁሉም ሃላፊነት ወስዶ ማስተዋወቅ እንደሚገባ አንስተዋል።
በመጨረሻም ፅ/ቤቱ የሞባይል መተግበሪያ አፕልኬሽንና በተዘጋጀው ወረዳዊ ድህረገጽ ገፁ እንዲለማ ትልቅ ድጋፍ ሲያደርጉ ለነበሩ አካላት የምስጋናና የምስክር ወረቀት አበርክቷል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *