የምጅር_ማይ ( የዳመራ_ማቆሚያ_ቀን)

#የምጅር_ማይ ( #የዳመራ_ማቆሚያ_ቀንን ** በሶዶ ክስታኔ ማህበረሰብ እና ዙሪያው ባሉ #የክስታኔኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች በዓመት ውስጥ ከሚከበሩ ሐይማኖታዊ እና ባሀላዊ በዓላት ውስጥ ነሃሴ 13 የሚፈፀመው የምጅር ማይ ወይም ዳመራ የማቆሚያ ቀን አንዱ ሲሆን ይህ በዓል የራሱ የሆነ ሃይማኖታዊ አንድምታ እና ባህላዊ ይዘት ያለው ሲሆን በዚህም ቀን በጠዋቱ አንድ መንደር አቅራቢያ ያሉ ወጣቶች በመስባሰብ ለደመራ የሚሆነውን እንጨት ማለትም በደጋማ አካባቢ የነጭ ዛፍ አጠና እና ገድራ በቆላማው አካባቢ ደግሞ ከቀይ ዛፍ አጠና ወይም ከጫካ እንጨት ቆርጠው እና እንጨቱንም ቶሎ እንዲደርቅ ደመራውም እንዲያምር ተልጦ ይዘጋጃል አዘገጃጀቱም መሃል ላይ እንደምሰሶ የሚያገለግል አንድ ወፍራም አጠና በረዥም የተቆረጠ ጫፋ ላይ ያልተመለመለ አጠና እንዲቆም ይደረጋል በዚያም በክብ ዙሪያውን የተቆረጡትን አጠና እንጨቶች ከማህለኛው እንጨት ጫፍ ጋር በመጨመር በልጥ ወይም በወፊቾ ዙሪያውን በማሰር ደመራው በሰርአት እንዳይወድቅ ይቆማል ።

ይህ የደመራ ማቆም መትከል ሥራ በአጥቢያ ቤተክርስቲያን በእድር ወይም በሸንጎ መቀመጫ ቦታ በመኖሪያ ቤት አካባቢ በቁጥር ሁለት ማለትም የአዋቂ እና የልጆች ተብሎ ይደመራል ወይም ይዘጋጃል ይህንንም ደመራ አዘጋጅተው ለሚመጡ ወጣቶች አባቶች እና እናቶች እንኳን ለዚኛው አመት አደረሰን በማለት በመመረቅና አምላክን ባማመስገን ጠላ ዳቦ ቆሎ ወይም ንፍሮ በማዘጋጀት ይቀበሉቸዋል ይመርቋቸዋል።

ይህ ደመራ ከቆሙበት የመጀመሪያ እሁድ ጀመሮ እና የሰንበት ቀን በመንደር ያሉ ሴት ልጃገረዶች እና ወጣት ወንዶች ፀሐይ ከመጥለቋ ባፊት ተሰባስበው በጋረ ይጫወታሉ ይህ ጊዜ በጉጉት የሚጠበቅ እና የሚናፈቅ ከመሆኑ ጋር ማንም ከዚህ አይቀርም በዚህም ጨወታ ወቅት ዔቶች በአበቤ ዜሜ’ አበቤ አበቤን”በቅላፄ ያዜማሉ ወንዶችም ‘ጎሮ ማጎሮ’፣ አጋት’፣ “ችሌ ከበሌ” “ሴባ’፣” አጋት አበደች”፣ “መጀ አራጆ” የሚባሉ ጫወታዎችን እንደ ዕድሜያቸው መጠን በተናጠል ይጫወታሉ ይህም ጨዋታ እስከ መሰቀል እና አዳብና ጅማሮ ይቀጥል በነዚህን ቀናት የቤተሰብ ባልከላም ይሁን ቁጣ የለም።መልካም በዓል ይሁንላችሁ [||