የደቡብ ሶዶ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ፅ/ቤት

አቶ ተሾመ በጋሻው
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ፅ/ቤት ኃላፊ
ራዕይ
የወረዳው ህ/ሰብ ወደ ኢኮኖሚያዊና አስተዳዳራዊ ማዕከላትና የአገልግሎት ተቋማት የሚያደርስ በቂ ፣ምቹና አስተማማኝ የመንገድ አውታርና የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚ ሆኖ ማየት
ተልዕኮ
ለወረዳው ህ/ሰብ የተቀናጀ ልማት ለማምጣት የሚያስችሉ የተለያዩ ደረጃ ያላቸው መንገዶችን በማስጠናት በመገንባት እንዲሁም በመጠገንና በማስተዳደር የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም በማስፋፋትና በማጠናከር ፣የአሽከርካሪዎችንና የተሸከርካሪዎችን ብቃት በማረጋገጥና የህ/ሰቡን የመንገድ አጠቃቀምና ትራፊክ ደህንነት ግንዛቤ በማሳደግ የትራንስፖርት ተጠቃሚነትንና ደህንነትን እውን ማድረግና መላው ህዝብ በማደራጀትና በማነቃነቅ በሴክተሩ እቅዶች ዝግጅት አፈፃፀምና ውጤት ላይ ማሳተፍ መቻል
- ቀልጣፋ አገልግሎትና ውጤታማነት ማረጋገጥ ተግባራችን ስኬት ዋና መለኪያ ናቸው
- ጥራት፣ ግልጽነት፣ ተጠያቂነትና ፍትሃዊነት ጥምር የጽ/ቤታችን ሀብቶች እናደርጋቸዋለን፡፡
- ህ/ሰቡን ያሳተፈ ልማት ላይ እናተኩራለን ስኬቱም ውድቀቱም የጋራችን ነው
- ሀብትን በአግባቡና በቁጠባ እንጠቀማለን
- ለደንበኞቻችን እርካታ ቅድሚያ እንሰጣለን
በዳይሬክቶሬት የሚሰጡ
- በየደረጃው ያሉ የስራ ክፍሎች ለተገልጋዮች ውጤታማ አገልግሎት ይሰጣሉ
- የስብሰባ ፕሮግራሞች ለተገልጋየጰች የአገልግሎት መስጪያ ጊዜ በማይነካ መልኩ በማድረግ የስራ ሰዓትን ለተገልጋዮች ምቹ ያደርጋል
- ተገልጋዮችን በአገልጋይነት ስሜት ማስተናገድ የስራ ክፍሎችና የፈጻሚዎች መለያ /ባጅ በአግባቡ መጠቀም
- የአገልግሎት አሰጣጥን ስታንዳርድን ለተገልጋይ የማሳወቅ ስራ ይሰራል
- በየደረጃው የተዘጋጁ እቅዶችን በተቀመጠው ጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይፈጽማሉ



የትኩረት መስክ
- የመንገድ ልማትና አስተዳደር
- የትራንስፖርት አገልግሎት
አቶ ተሾመ በጋሻው
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ፅ/ቤት ኃላፊ መልዕክት
የመንገድ ልማት አስተዳደርና የትራንስፖርት አገልግሎት ቁልፍ የትከረት መስኮች ሲሆኑ በዚህ ዘርፍ መንግስት እምርታዊ ለውጥ ለማምጣት በስፋት እየተቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ በሌላ በኩል የአገልግሎት አሰጣጥ በማሻሻል የሚጠበቅ ውጤት ነው፡፡ በዚህ መሰረት ተቋሙ በመንገድ ልማት አስተዳደር ዘርፍ እንደዚሁም ደግሞ በትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ በአጠቃላይ የተቋሙ አፈፃፀም ወደ ተሻለ በማድረስ መንግስት በ GTP2 እቅዱ ያለመውን ቦታ ለማድረስ ጥረት ማድረግ ነው፡፡ ለወረዳው ህ/ሰብ የተቀናጀ ልማት ለማምጣት የሚያስችሉ የተለያዩ ደረጃ ያላቸው መንገዶችን በማስጠናት በመገንባት እንዲሁም በመጠገንና በማስተዳደር የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም በማስፋፋትና በማጠናከር ፣ የአሽከርካሪዎችንና የተሸከርካሪዎችን ብቃት በማረጋገጥና የህ/ሰቡን የመንገድ አጠቃቀምና ትራፊክ ደህንነት ግንዛቤ በማሳደግ የት/ርት ተጠቃሚነትንና ደህንነትን እውን ለማድረግ መላው ህዝብ በማደራጀትና በማነቃነቅ የሴክተሩ እቅድ ዝግጅትና አፈፃፀም ውጤት ከፍ ማድረግ ነው፡፡