የደቡብ ሶዶ ወረዳ ውሃ መስኖ ማዕድንና ኢነርጂ ጽ/ቤት
አቶ ታሪኩ በሬሳ ሞርኬ
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ፅ/ቤት ኃላፊ

ራዕይ

የውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ሀብቶቻችን በተቀናጀ፣ በዘለቄታዊ፣ ፍትሐዊና ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማስተዳደርና ለማልማት የሚያስችሉ ሕጋዊና ተቋማዊ አሰራሮች ጎልብተው በቂና አስተማማኝ ውሃ ለሁሉም ግልጋሎቶች በተፈላጊው ጥራት ደረጃ ቀርበው ፣ የህ/ሰቡ የአማራጭ ኢነርጂ ተጠቃሚነት አድጎና የወረዳው የማዕድን ሀብት በተገቢው ሁኔታ ለምቶ ለፈጣን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ወሳኝ ድርሻ አበርክቶ የወረዳው ህብረተሰብ ተጠቃሚ ሆኖ የተሻለ ሕይወት ሲመራ ማየት

ተልዕኮ

ህብረተሰቡንና ሌሎች የልማት ሀይሎችንና አጋሮችን በማስተባበር የውሃ፣ የማዕድንና የኢነርጂ ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎችንና ኘሮግራሞችን መሠረት ያደረገና ተፈፃሚነት ያለው የልማት መርሃ ግብር በመቅረጽ የተቀናጀ እና ዘለቄታዊ የውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ አስተዳደር ማስፈንና የውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ሀብታችን ለወረዳው ህዝብ ዕድገትና ብልጽግና ወሣኝ ሚና መጫወት በሚችል መልኩ እንዲለማ ማድረግ

  • ለዘላቂና ለተቀናጀ የውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ሀብት ልማት ጠንክረን እንሰራለን፡፡
  • ውሃ ህይወት ነው
  • የውሃ፣ የማዕድንና ኢነርጂ ዘርፍ የመረጃ ባንክ ነን፡፡
  • ሴቶች በውሃ ልማት እኩል ተሣታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ እናደርጋለን፡፡
  • ውሃቁልፍ የልማት መግቢያ / key entry point / ነው
  • የውሃ ልማት በሌሎች የልማት ዘርፎች ላይ ወሳኝ ድርሻ አለው፡፡
  • ውሃ ዋጋ አለው
  • ውሃን በቁጠባ እንጠቀም
  • ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት ጠቀሜታ አለው
  • ማዕድን ዋጋ ያለው ስለሆነ እንከባከበው
  • በማዕድን ሃብታችን ህብረተሰባችን ተጠቃሚ ይሁኑ
  • ኢነርጂ የልማት ሁሉ መሠረት ነው
  • ውሃ ረግጠን አንጠማም

ዓላማ

ዋና ዓላማ

  • ለወረዳ የገጠር ነዋሪ ህዝብ በ1 ኪ/ሜ ክልል ውስጥ በነፍስ ወከፍ በቀን 25 ሊትር ውሃ ማቅረብ
  • ለወረዳው የከተማ ነዋሪ ህዝብ በነፍስ ወከፍ በቀን ደረጃ 40 ሊትር ውሃ በማቅረ
  • በማዕድኑ ዘርፍ ወጣቶችን ማደራጀት
  • የአማራጭ ኢነርጂ አቅርቦት በማሳደግ ከኩራዝ ጭስ ነጻ የሆኑ ቀበሌዎች መፍጠር

ዝርዝር ዓላማ

  • የወረዳውን የውሃ፣ የመስኖ፣ የማዕድንና የኢነርጂ ሀብት በአግባቡ በማጥናት ህጋዊ አጠቃቀምና አስተዳደር ሥርዐት በማስፈን ለተለያዩ ማህበራዊ ዕድገት እንቅስቃሴዎች በተቀናጀ፣ ዘላቂና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ማልማትና መጠቀም ፣
  • የንፁህ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ተቋማት ጥናትና ዲዛይን፣ ቅድመ ብቃት ግምገማና ይሁንታ አሰጣጥና አሰራር ሥርዓቱ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በጥራትና በቅልጥፍና ላይ ተመስርቶ ህብረተሰቡ አስተማማኝና ዘላቂ አገልግሎት እንዲያገኝ በማድረግ የዘርፉን የልማት ግብ ማሳካት፤
  • በሴክተሩ መታየት የጀመሩትን ማነቆዎች በማስወገድና በማቃለል አጠቃላይ የዞኑን የንጹህ መጠጥ ውሃ እና የዘመናዊ የመስኖ ዉሀ አቅርቦት ሽፋንን ማሳደግ፣
  • የንፁህ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አቅርቦቱ ስታንደርዱን ጠብቆ ፍትሃዊነቱ እና ጥራቱ በተረጋገጠ የአሰራር ሥርዓት ላይ የተመሠረተ በማድረግ የወረዳውን ህዝብ ጤና ሁኔታ በማሻሻልና አምራች ዜጋ በማፍራት አጠቃላይ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ብልጽግናን ማዳበር፣
  • የመጠጥ እና የመስኖ ውሃ ተቋማት ጥገናና አስተዳደር ስርዓትን በማዘመን ተቋማት አስተማማኝና ዘላቂ አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ የሴክተሩን የልማት ግብ ማሳካት፣
  • የአማራጭ ኢነርጂ ዘርፍ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ከማረጋገጥ አንጻር የበኩሉን እንዲወጣ ማድረግ

ለኮንስትራክሽን፤ ለግብርና እና ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ግብዓት የሚውሉ ማዕድናት ሀብት አለኝታ በመለየት የምርት አቅርቦት እንዲሻሻል በማድረግ በዘርፉ የስራ ዕድል እንዲፈጠር ማስቻል፤

  • መጠጥ ውሃ ዘርፍ
  • የገጠር መጠጥ ውሃ ተቋማት የብልሥት ምጣኔ መቀነስ
  • የከተማ ውሃ አገልግሎት ድጋፍ ማድረግ
  • የገጠር የውሃ ማህበራት ኦዲት ማድረግ
  • የገጠር መ/ው/ሳኒቴሽንና ማህበራት የሴቶች ተሳትፎ ማሳደግ
  • የህ/ሰብ የጉልበት ተሳትፎ ለመጠጥ ውሃ ግንባታ ማዋል
  • የውሃ ተቋማት በማህበር ማደራጀት
  • ተቋማት በፌድሬሽን ማቋቋም
  • የውሃ ተቋማት አጥር ማሳጠርና ማጠናከር
  • በነባር የገጠር ውሃ ማህበራት ላይ የማህበራት የስራ አስፈፃሚዎችን ማጠናከር
  • የመለስተኛ ጥልቅ ጉድጓድ ጥናትና ዲዛይን
  • አዲስ ጥልቅ ጉድጓድ ከነማከፋፈያ ጥናትና ዲዛይን
  • ምንጭ በቦታው
  • ከነባር ተቋማት ማከፋፈያ ጥናት ማድረግ
  • የእጅ ጉድጓድ ፓምፕ የተገጠመለት
  • ጤና ተቋማት የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረግ
  • የት/ት ተቋማት የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረግ
  • ምንጭ ከነማከፋፈያው
  • የውሃ መገኛ ቦታዎች ጥናት ማድረግ
  • የውሃ ሽፋን መረጃ ማዘጋጀት
  • የውሃ ተቋማት በክሎሪን ማከም
  • የንጹህ መጠጥ ውሃ ሽፋን ማሳደግ
  • የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ እርካታ ማሳደግ
  • የጨረታ ዶክመንት ማውጣትና መገምገም
  • የመለስተኛ ጉድጓድ ቁፋሮና ግንባታ ክትትል ቁጥጥር ማድረግ
  • አዲስ ጥልቅ ጉድጓድ ቁፋሮና ግንባታ ክ/ቁ/ማድረግ
  • ነባር ጥልቅ ጉድጓድ ቁፋሮና ግንባታ ክ/ቁ/ማድረግ
  • ምንጭ በቦታው ማጎልበት
  • መለሰተኛ ምንጭ ግንባታ ከነማስፋፊያ ክ/ቁ/ማድረግ
  • የእጅ ጉድጓድ ቁፋሮና ግንባታ ክትትል ማድረግ
  • ማዕድን ሀብት አስተዳደር
  • በማህበር ለተደራጁ ወጣቶች የማእድን ፈቃድ መስጠት
  • በማእድን ወጣቶችን ማስጠቀም
  • ከነባር ባለፈቃድ ገቢ መሰብሰብ
  • ከአዲስ ባለፈቃድ ገቢ መሰብሰብ
  • ከአዲስ ባለፈቃድ ውል ስምምነት ማድረግ
  • ከቅጣት ገቢ መሰብሰብ
  • የማእድን ቦታዎችን መከለል
  • የተጎዱ የማእድን ማምረቻ ቦታዎች መልሶ ማልማት
  • የተሰጠ የቴክኒክ ድጋፍና የምክር አገልግሎት
  • የስራና የግብር የሽያጭ ካርኒ በወቅቱ ያወራረዱ
  • ህገ-ወጥ የኮ/ማ/ክ/ቁ/ማድረግ
  • የተመረተ የማእድን መጠን በማእድን ዓይነት ለይቶ ማስቀመጥ
  • የማእድን አምራቾች ውል ማቋረጥ
  • አማራጭ ኢነርጂ
  • የአማራጭ ኢነርጂ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ፊላጎት ማሰባሰብ
  • ሶላር ማሾ ማሰራጨት
  • ሶላር በቤተሰብ ማሰራጨት
  • ሶላር በተቋም ማሰራጨት
  • አማራጭ ኢነርጂ ቴክኖሎጂ ውጤቴች እርካታ መለየት
  • ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ ማሰራጨት
  • ትክክል ምድጃ ማሰራጨት
  • አዲስ የተገነባ ባዮጋዝ
  • የተጠገነ ባዮጋዝ
  • የተጠገነ ሶላር
  • ኩራዝ አልባ ቀበሌ ልየታ ማድረግ
  • ህገ ወጥ ሶላር አቅራቢዎች ቁጥጥር ክትትል ማድረግ
  • የኢነርጂ ቴክኖሎጂ ምርት ማስተዋወቅ

የደቡብ ሶዶ ወረዳ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ፅ/ቤት ኃላፊ መልዕክት

በሚቀጥሉት አስር ዓመታት (2013-2022 ዓ/ም) ወደ ትግበራ በሚገባው የዘርፉ መሪ ዕቅድ ከገጠር የመጠጥ ውሃ አቅርቦት አንጻር በ1 ኪ/ሜ ርቀት በነፍስ ወከፍ በቀን 40 ሊትር ውሃ በማቅረብ  ሽፋኑን በዕቅድ ዘመኑ መነሻ 2012 ዓ/ም ከነበረበት 35.42% በዕቅድ ዘመኑ መጨረሻ 2022 ዓ/ም 100% ለማድረስ የሚሰራ ይሆናል፡፡ በተመሳሳይ በከተማ ንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት አንጻር በነፍስ ወከፍ በቀን ደረጃ 40 ሊትር ውሃ በማቅረብ ሽፋኑን በዕቅድ ዘመኑ መነሻ 2012 ዓ/ም ከነበረበት 32% በዕቅድ ዘመኑ መጨረሻ 2022 ዓ/ም 100% ለማድረስ የሚሰራ ይሆናል፡፡ ለከተማው የሚቀርበው የውሃ መጠን ከተማው በተሰጠው ደረጃ የሚወሰን ሲሆን ይህም በከተማው የሚኖረው የህዝብ ብዛትን መነሻ ያደርጋል፡፡ በአጠቃላይ የወረዳውን የገጠርና ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋንን በዕቅድ ዘመኑ መነሻ 2012 ዓ/ም በአማካይ ከነበረበት 35.42% በዕቅድ ዘመኑ መጨረሻ 2022 ዓ/ም 100% ለማድረስ የሚሰራ ይሆናል፡፡ከዘመናዊ መስኖ ልማት አንጻር አስተማማኝ የውሀ አቅርቦት እንዲኖር ደግሞ ከመቼውም በተሸለ መልኩ ተስማሚ አካባቢዎችንና ከፍተኛ የዝናብ መቆራረጥና እጥረት ያለባቸዉ ቦታዎችን በመምረጥ ግድብ ግንባታና የከርሰ ምድር ውሀ ልማት ማከናወን፣ ውሀ ቆጣቢና ዘመናዊ የመስኖ ቴክኖሎጂዎችን ማስፋፋት፣ የአምራቹን ህብረተሰብ እውቀት፣ ግንዛቤና ክህሎት ማሳደግ እና አስፈላጊ መሰረተ ልማቶችን በስፋት መዘርጋት ዋናዋና መሰረታዊ እርምጃዎች ተብለዉ ተለይቷል፡፡ከአማራጭ ኢነርጂ ልማት አንጻር ዘመናዊና የተሻሻሉ ባህላዊ አማራጭ የኢነርጂ ቴክኖሎጂዎች በአይነትና መጠን በሰፊው የህዝቡን ፍላጎት ጋር የተመጣጠነ አቅርቦትና ስርጭት ለማድረግ ታቅዷል። በመሆኑም ህጋዊ እውቅና የተሰጣቸው የቴክኖሎጂ አቅራቢ ማህበራት ቁጥር በመጨመር አቅርቦቱን ማሻሻል እና የአካባቢ አምራች ነባር ማህበራት ነባሩን በቂ ምርት እንዲያመርቱ ማድረግ እና አዲስ ማህበራት በማደራጀት ወደ ስራ እነዲገቡ ይደረጋል።ከማዕድን ሀብት ጋር ተያይዞ በተለይ በወረዳው የሚገኙ የግንባታ ማእድናት በአይነትና ጥራት ክምችቱን በመለየት ለተደራጁ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ እድል እንዲፈጠርላቸው በልዩ ትኩረት የሚሰራ ሲሆን ነባር ማህበራት በወቅቱ እንዲሸጋገሩ በቂ ድጋፍና ክትትል ይደረጋል።በሚቀጥሉት አስር ዓመታት ተፈጻሚ የሚሆኑ የዘርፉ የልማት ሥራዎች ከምን ጊዜውም በተሻለና በላቀ ሁኔታ ጥራታቸው የተጠበቀ እንዲሆን የሚደረግ ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘ ዕቅዱን ተፈጻሚ ለማድረግ ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ የሚጠይቅ ሲሆን በተለይ ለመጠጥ ውሃ ተቋማት ግንባታ ሥራዎች ኢንቨስትመንት ፍላጎት ከፍተኛ ነው፡፡ ስለሆነም ህብረተሰቡን በሰፊው የማነቃነቅና የግሉ ባለሀብት ተሳትፎ ማሳደግ ከፍተኛ ትኩረት ተሠጥቶ ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ ይሆናል፡፡

የደቡብ ሶዶ ወረዳ ውሃ መስኖ ማዕድንና ኢነርጂ ጽ/ቤትን ለማግንኝት