የደቡብ ሶዶ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት

አቶ እንዳልካቸው ማሩ
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ግብርና ፅ/ቤት ሀላፊ
ዓላማ
ዋና ዓላማ-የተፈጥሮ ሀብትና ውስን ካፒታልን በአግባቡ በመጠቀምና በማስፋት መላዉ አ/አደር ጋር እንዲደርስ በማስፋፋት ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ አገር ተወዳዳሪ የሆኑ ምርቶችን በጥራትና በብዛት በማምረት ሕዝቡን ምግብ ዋስትና በማረጋገጥ የገጠሩ ህ/ሰብ የኑሮ ደረጃውን እንዲሻሻል ለማድረግ በተለይም የሴቶችና የወጣቶች የልማት ተሳትፎ በማሳደግ በልማቱ ፈጣንና ቀጣይነት ያለዉ እድገት እንዲመዘገብ ማድረግ ነዉ፡፡
ራዕይ
በ2020 ዓ/ም የምግብ ዋስትና በዘላቂነት የተረጋገጠበትና የግብርና ኢኮኖሚ አድጎ በገጠር ኢንዱስትሪዎች የተስፋፋበት ወረዳ ሆኖ ማየት፡፡
- ቅድሚያ አርሶ አደሩ
- ሀብቱን በአግባቡ በቁጠባ መጠቀም
- ፍትአዊነት
- ህ/ሰብን ያሣተፈ ልማት ማካሄድ
- ቅንነት
- ታማኝነት- ተጠያቂነት ማስፈን
- የምርት አሰባሰብ በጥራት ማከናወን መቻል
- የበጋ መስኖ ስንዴና የመደበኛ መስኖ ማሳደግ
- የእንስሳት ዝሪያ ማሻሻል፤የእንቁላል፤የወተት፤የማር ምርት ማሳደግ
- 30*40*30 የፍራፍሬ መንደር ማሳደግ
- የተፈጥሮ ሀብት ስራ ማሳደግና የአረንጓዴ አሻራ ቅድመ ዝግጅት ማጠናከር
- የቡናና ቅ/ቅመማ ልማት ማጠናከር
- የህብረት ስራ ልማትና የግብዓት አቅርቦትና ግብይት ማጠናከር



የሴክተሩ አጠቃላይ ገፅታ
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ግብርና ፅ/ቤት የሰው ሀይል ማሟላት የተፈቀደ ተግባር ተኮር 96ሲሆን የተሸፈነ 40 የወል የተፈቀደ 15 የተሸፈነ 4 የጋራ አገልግሎት የተፈቀደ 7 የተሸፈነ 4 በአጠቃላይ የሰው ሀይል ማሟላት የተፈቀደ 119 የተሸፈነ 48 አፈፃፀም 40% ነው፡፡
አቶ እንዳልካቸው ማሩ
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ግብርና ፅ/ቤት ሀላፊ መልዕክት
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ግብርና ፅ/ቤት በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን የሚገኝ ሲሆን ፅ/ቤቱ በአምስት ዋናዋና ዘርፍማለትም በእርሻ ዘርፍ በተፈጥሮ ዘርፍ በእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ በአደጋ ስጋት መከላከልና ቅድመ ማስጠንቀቂያ በመሬት አስተዳደር አጠቃቀም ዘርፍ የተዋቀረ ሲሆን በዋናነት ተቋሙ የኢንደስትሪሽግግር ለምናደርገው ጉዞ አጋዥ የሆኑ ስራዎች በመስራት ላይ ይገኛል ከዚህ አኳያ ትላልቅ የመደበኛ መስኖ ስራዎች በአትክልትና ፍራፍሬ ስራዎች በእንስሳት ዘርፍ የዝርያ ማሻሻልና የንብ ማነብ ስራዎች በስፋት እየተሰራ ይገኛል፡፡ለዚህ የበርካታ ዜጎች የስራ ዕድልና የኢንቨስትመንት ማዕከል በመሆን ለኢኮኖሚ ዕድገት የጎላ አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል፡፡