የጉራጌ ሙዚቃ ፈር ቀዳጅ የሶዶ ክስታኔ ቋንቋ አቀንቃኝ የባህል አምባሳደር የኢትዮጲያ ባህላዊ ሙዚቃ ንጉስ። ጋሽ አርጋው በዳሶ። የጉራጊኛ ሙዚቃ ጀማሪ የጉራጌን ባህልና ቋንቋ ከኢትዮጲያ አልፎ ለአለም ያስተዋወቀ ጀግና ሙዚቀኛ። አርጋው በዳሶን የማያውቅ ኢትዮጲያዊ የለም ለማለት እስክደፍር ድረስ እናገራለው። አርጋው በዳሶ በ1920ዎቹ በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን በደቡብ ሶዶ ወረዳ በዳሙ ገነት ተወለደ። አርጋ በዳሶ በልጅነት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ- ክርስትያን ዲያቆን የነበረ። በአንድ ወቅት ከኢትዮጲያ ራዲዮ ጋር ባደረገው ቆይታ ጠፍቶ አዲስ አበባ እንደሄደ ሲናገር ሰምቼ ነበር። አርጋ በዳሶ አዲስ አበባ ከመጣ በኋላ በፍራሽ ስራ ላይ ተሰማርቶ እየሰራ የነበረ ሲሆን ሁሌም በድምፅና በፉጨት ሲያጎራጉር የሰሙት ሰዎች ሙዚቃ ቡድን እንዲቀላቀል ገፋፍተውት እንደተቀላቀለ አውርቷል። አርጋ በዳሶ በጣም የታወቀበት ዘፈኑ አለም በሬ ነይ ነይ ሲሆን በተጨማሪም የጉራጊኛ ጭፈራ ጎበዝ የነበረ ሲሆን በጭቅላቱ ቆሞ እግሩን ወደላይ እያወዛወዘ የሚጨፍረው ጭፈራ የብዙ ተመልካች ቀልብ የሳበ ሆኖ አይረሴም እንዲሆን አድርጎታ።

ከ1949 እስከ 1952 ዓ.ም በሀገር ፍቅር ከሰኔ 1954 ጡረታ እስከ ተገለለበት 1976 ዓ.ም በፖሊስ ኦርኬስትራ አገልግሏል፡፡ ጡረታ ከወጣ በኋላም በትርፍ ጊዜው ከአክሱማይት ባንድ፣ከኤክስፕረስ ባንድና ከሌሎችም ታዋቂ ባንዶች አብሮ ይሠራ ነበር፡፡

አርቲስቱ ከዓይን ህመም በስተቀር ጠንካራ አቋም የነበረውና መድረክ ላይ ታዳሚዎቹን የመያዝ ችሎታ የነበረው የ70ዎቹ አዛውንት የነበረ ቢሆንም ወደ ዕለት ሞቱ በታቃረበበት ጊዜ ግን መናገር ተስኖት እንደነበር ከቅርብ ወዳጆቹ ይነገራል፡፡ ለመሆኑ ይህ አርቲስት ማን ነው? አርቲስት አርጋው በዳሶ በቀድሞ ሸዋ ክ/ሀገር በአሁኑ የደቡብ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መስተዳድር በምስራቅ ጉራጌ ዞን በደቡብ ሶዶ ወረዳ ውስጥ ዳሙ ገነት ቀበሌ ገበሬ ማህበር መጋቢት 27ቀን 1926 ዓ.ም ተወለደ፡፡ አርጋው በለጋነት ዕድሜው እንደማንኛቸውም የአካባቢው ልጆች ከብቶች በማገድ፣ የማገዶ እንጨት በማዘጋጀት፣ ውኃ በመቅዳትና የተለያዩ ሥራዎችን በመርዳት ቤተሰቦቹን ሲያገለግል ቆይቷል፡፡

ምንም እንኳ መማር ባለበት ዕድሜ ወደ ትምህርት ዓለም ያልገባ ቢሆንም በአካባቢው የዘመናዊ ትምህርት ያልነበረ በመሆኑ በወቅቱ በአካባቢው ሲያስተምሩ በነበሩ መሪጌታ ምክንያት ዲያቆን ለመሆን በቅቶ ነበር፡፡ ነገር ግን በድቁናው ስራ ሊረካ ባለመቻሉ እንደሌሎች ጓደኞቹ እራሱን ለማሻሻል ባለው ጉጉት በ1938.ም ነበር ወደ አ/አበባ የመጣው፡፡አርጋው አ/አበባ እንደመጣ ነዋሪነታቸው አ/አበባ በነበሩት አያቱ አማካይነት ንጉሥ ወ/አረጋይ የቄስ ት/ቤት ገብቶ የድቁና ትምህርት ወስዶ ነበር፡፡ በቤተ ክህነት ተክህኖ ቀድሞ ወደ ነበረበት ሙያ እንደተመለሰ አባቱ መልሰው ወደ አገር ቤት ወሰዱት:: የአገር ቤት ቆይታው ብዙ ያልጣመው አርጋው ግብርናውንና ድቁናውን ተያያዘው ይሁን እንጂ አልሞላልህ አለው፡፡

በተለይ አ/አበባ ያሉት ጓደኞቹ እራሳቸውን ለውጠው ወደ አገር ቤት ሲገቡ ሲያይ ይበልጥ በመጓጓቱ ምክንያት ወደ አ/አበባ መምጣቱ ይነገራል፡፡

ከብዙ መንከራተት በኋላ ድንጋይ በመሽከም የቀን ሥራ የጀመረው አርቲስት አርጋው ስራው አድካሚና አሰልቺ የነበረ ቢሆንም ኑሮን ለመጋፈጥ ወጥቷልና አድካሚ የሆነውን ሥራ ተያያዘው፡፡ ሆኖም የሥራውን ክብደት ሊቋቋመው ባለመቻሉ ሰውነቱ ይቆሳስል ገባ ‹‹ግን በዚህ አልተደናገጥኩም ነበር›› ሲል ቀደም ብሎ ስለ ግል ህይወቱ ለተሠራው ፕሮፋይል የሰጠው ቃል ያመለክታል፡፡ የአርጋውን የስራ ሁኔታ በቅርብ ርቀት ሲከታተል የነበረው ያጎቱ ልጅ ግን ‹‹በፍፁም አትሠራም›› ሲል ተቃወመው፡፡ ለተወሰኑ ጊዜያት አብሮት እንዲኖር ካደረገ በኋላ የአካባቢያቸው ተወላጅ ከነበረ እንድ ፍራሽ ሰፊ ጋር ተነጋግሮ ምግቡን ችሎ በዓመት ስድስት ብር እንዲከፈለው ተስማምቶ አስቀጥሮት ነበር፡፡ አሰሪዎቼ ሙስሊሞች በመሆናቸው በምግብ አጠቃቀም በኩል ክርስቲያን ሰለሆንኩ ችግር አንደገጠመኝ ለአሰሪዬ ነገርኩት አሠሪዬም በቀን 0.25ሣ እንደሚያስብልኝ ቃል ገብቶ ተግባራዊ አደረገው እስከ ምሳ ምንም ሳልበላ እየቆየሁ በ0.10 ሣንቲም ቆሎ ገዝቼ ምሳ እበላና ማታ ደግሞ የ0.5 ሣንቲም ቆሎ ገዝቼ አለቃዬ በሚጋብዘኝ እንድ ጣሳ ጠላ አወራርደዋለሁ፡፡ ማደሪያ የሌለኝ በመሆኑ ሥራ ቦታ ሄጄ ተሰፍቶ ቃጫ ያልገባበት ማዳበሪያ ውስጥ ገብቼ ከውስጥ ሸምቀቆውን እስበዋለሁ፡፡ ጧት ስነሳ የት ንደተኛሁ ሳላውቀው እነቃለሁ፡፡›› ሲል ለግለ ታሪኩ ፀሐፊ ተርኮለታል፡፡

አርጋው እንዲህ እንዲህ እያለ ሥራውን ለመደው በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ኑሮውን መግፋት አልፈለገም፡፡ በቀን ከሚሰጠው 0.25ሣ ውስጥ 0.10 ሣ ያተርፋል፡፡ ፍራሽ ተዘጋጅቶ ስድስት ብር ሽጥ ተብሎ ከሆነ 10 ብር ይሸጥና ትርፋን ለራሱ ይይዛል:: ደመወዙንም ጨምሮ በእንዲዚህ ዓይነት ሁኔታ ገንዘብ ማግኘት ቻለ፡፡ ያገኘውን ሣንቲም በአደራ ሲያስቀምጥለት የነበረው ሰው ለብቻው እንዲሠራና የገንዘብ ዕጥረት ከገጠመውም በቁሳቁስም ሆነ በገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርግለት ይመክረዋል፡፡ከዚያ በኋላ በራሱ ቃጫ፣ ክርና ሌሎችም አስፈላጊ ነገሮች አሟልቶ በመሥራት እራሱን ችሎ ጠፍቶ አ/አበባ በመምጣቱ ተቀይመው የነበሩት አባቱ ጥሩ ደረጃ ላይ መድረሱን ሲሰሙ ሊጠይቁት ከአገር ቤት አ/አበባ መጡ፡፡ ይዘውት ወደ አገር ቤት ሄደውም ‹‹ሚስት ካላገባህ›› አሉት፡፡ ‹‹አላገባም›› ብሎ ጠፍቶ ሊመጣ ሲል በግድ ተይዞ እንዲያገባ ሆነ፡፡ ይሁንና ብዙም ሳይቆይ ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ሥራውን

መቀጠል ችሎ ነበር፡፡ አርጋው ዲያቆን በነበረበት ወቅት የድምፁን ማማር የሰሙ የደብር አለቆች ሁሉ‹‹እኛጋ እኛጋ›› እያሉ ይወዛገቡበት እንደነበር ይነገራል፡፡ አርጋው ድቁና ብቻ ሣይሆን ዘፈንም ነፍሱ ነበር፡፡ ‹‹ከበሮ ሲደለቅ ከሰማሁ የትም ቢሆን አልቀርም›› ሲል መናገሩ ግለ ታሪኩ ላይ ያለው ጽሑፍ ያስረዳል፡፡ በአንድ ወቅት አ/አበባ ከመጣ በኋላ ጦር ኃይሎች አካባቢ ኤግዚቪሽን ነበር፡፡ በዚህ ኤግዚቪሽን ላይ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች የየራሳቸውን የባህል ጨዋታ ይጫወቱ ነበር፡፡ አርቲስቱ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም የዘፈን ጥሙን ለማርካት ጉራጊኛ ሲጨፍር ዋለ፡፡ ይህ ቀን ግን

በሀገር ፍቅሮች ዓይን እንዲገባ ያስቻለው ቀን ነበር፡፡ በማግስቱ የተለመደው የዕለት ሰራውን ለማከናወን ለሽያጭ ያዘጋጀቸውን ፍራሽና ትራሶች ይዞ ሲወጣ፡፡ ‹‹የሆኑ ሰዎች ኩምቢ ቮልስ መኪና አቁመው ‹‹ግባ›› አሉኝ በወቅቱ ለአዶላ ወርቅ ቁፋሮ ይታፈስ ስለነበር አልገባም እኔ እንደምታዩት ሥራ አለኝ ስለምንስ ትወስዱኛላችሁ? አልኳቸው:: ግባ ትራሱንም አኛ አንገዛሃለን ብለው ልመና ይሁን ግዴታ ባልለየ የከረረ ድምፅ ቮልሷ ውስጥ አስገብተው ወሰዱኝ›› ሲል መናገሩን ይኸው ግለ ታሪኩ ያስረዳል፡፡ ቮልሷ ሀገር ፍቅር እንደደረሰች ለሥራ እንደሚፈልጉት ነግረውት ሊያወዳድሯቸው እንደሆነም ገለፁለት፡፡ ውድድሩ ተካሂዶ እንዳለቀ በዘፈንም በጭፈራም አንደኛ እንደወጣ ነገሩት በዚሁ መሠረት የቅጥሩ ሁኔታ ተከናወነ፡፡ ደመወዙ በወር 40 ብር በመሆኑ የተሻለ

ኑሮ መኖር ጀመረ፡፡ ሀገር ፍቅር የነበሩ ኃላፊዎች የተለያየ የጉልበት ሥራ ሲኖራቸው እየጠሩና እያሰሩ ሲያሰለቹት እምቢታ አመጣ፡፡ ‹‹የተቀጠርኩት ለዘፈን እንጂ ለሽክም አይደለም›› ሲል ተቃወማቸው፡፡

በዚህ አጋጣሚ በ1954 ዓ.ም የሠራተኛ ቅነሣ ሲመጣ በመጀመሪያ ከተቀነሱት 41 ሰዎች አንዱ ለመሆን በቃ፡፡ ከሥራ እንደተቀነሰ 500 ካሬ ሜትር የከተማ ቦታና የሶስት ወር ደመወዝ 120 ብር ተፈቅዶለት ከሥራ ተሰናበተ፡፡ ሰኔ 1954ዓ.ም ፖሊስ ኦርኬስትራ ማስታወቂያ አወጣ፡፡ ለፈተና እንደቀረበ ፈታኝ የነበሩት የፖሊስ ኦርኬስትራ ኃላፊ ኮ/ል ረታ እና ምክትል ኃላፊው ሻለቃ ወርቅነህ ነበሩ፡፡ ኮሎኔሉ አርጋው በጭንቅላቱ ቆሞ ሲጨፍር በማየታቸው በጣም ተገርመውበት ሻለቃው ቶሎ እንዲቀጥረው ትዕዛዝ አስተላለፉ፡፡

አርጋው በፖሊስ ኦርኬስትራ ሳለ ሀገር ፍቅር ከነበረበት በበለጠ ሁኔታ ብዙ ሥራዎችን ሠርቷል፡፡ በሥራዎቹም ተደማጭነትን እና መስህብ በማግኘቱ ከሀገር ውጪ ሱዳን፣ ምሥራቅ ምሥራቅ ጀርመን፣ ራሺያ የሄደ ሲሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ክፍለ አገራት ሁሉንም ለማዳረስ ችሎነበር፡፡ በአንድ ወቅት ወደ ሱዳን ሄደው ሲመለሱ በአስመራ በኩል ነበር የገቡት አግረ መንገዳቸውን ጎንደር አሣይተው ጎጃም ደብረ ማርቆስ ከተማ ማሳየት ይፈልጋሉ፡፡ ማዘጋጃ ቤት ስቴጅ የሌለው በመሆኑ ሕዝቡ ታች ሆኖ እንዲያይ ተደረገ፡፡ ‹‹ታዲያ በዚህ ጊዜ ቆጥ መሰል መድረክ ሰርተው የሳሙና ማሸጊያ ስስ ጣውላ ይሁን ኮምፔልሳቶ ደርድረው ግቡ አሉን፡፡ ዘፈን ተጀምሮ ጨፍሬ ጨፍሬ በጭንቅላቴ ሰቆም ጣውላው ተደርምሶ ጭንቅላቴ ወደ ውስጥ ገባ ነገሩ ምን እንደሆነ የገባቸው ተወዛዋዦች ከፊትና ከኋላ ከበው የተወሰኑ ሰዎች ወደላይ ይጎትቱኝ ገቡ፡፡ ምን እንደሆነ ያልገባቸውና ሌላ ትርዒት የማሳይ የመሰላቸው ተመልካቾች ግን ‹‹ቢስቢስ›› ይሉ ነበር ሲል ለግል ታሪክ ፀሐፊው ገጠመኙን ተናግሮ ነበር፡፡ እንዲህ እንዲህ እያለ ከፖሊስ ጋር ለ27 ዓመታት ያህል ቆይታ ሲያደርግ ከሃምሳ ብር እስከ 213 ብር የደመወዝ ዕድገት ማግኘት

ችሎ ነበር፡፡ አርጋው በ1976 ዓ.ም ነበር በጡረታ የተገለለው፡፡

አልበሞቹ ሲደመጡ ክስታኒኛ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም የጉራጊኛ ዘፈኖች ይደመጣሉ፡፡ እነዚህን ሌሎች ቋንቋዎች ከመስማት ያለፈ ችሎታ ባይኖረውም ግጥምና ዜማ ግን ያዘጋጅላቸዋል፡፡

የሶዶ ክስታኔ ልማት ማኅበር የበላይ ጠባቂ የነበሩትና የብሔሩ ተወላጅ የነበሩት ብ/ጄኔራል ይልማ ሺበሺ በግላቸው የጉራጌው ማኅበረሰብ እንዲሁም የሌላ ብሔር ተወላጅ የሆኑ ግለሰቦችም ጭምር ለሥራው መሣካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አንዳደረጉለት ማውሳቱን ግለታሪኩ ያስረዳል፡፡ አርጋው ሦስት የባህል ዘፈኖችን በግሉ ያሳተመ ሲሆን በጋራ ደግሞ እንዲሁ ሦስት አሳትሟል፡፡ ‹‹የአርጋው ዘፈኖች አድማጮች በመሳብና በመሳብና በመቆጣጠር ረገድ እንከን የማይወጣላቸው ናቸው፡፡ ‹‹ለምሳሌ የወራሽ ሰመሌ የሚለውንዘፈን የትም ዝግጅት ሲኖረን ወይም ሰንስባሰብ እንጨፍርበት እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡›› ሲል የአምባሰል ሙዚቃ ቤት ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍቃዱ ዋሬ በወቅቱ ለግለታሪክ ፀሐፊው ነግረውታል፡፡

መ/ር ግዛው ተሰማ የተባሉት በወቅቱ የአዲስ ከተማ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት መምህር ለግለ ታሪክ ፀሐፊው ‹‹አርጋው አይናችን ነው፡፡ ባህላችንን ከማስተዋወቅ አንፃር የተጫወተው ሚና ቀላል አይደለም፡፡ በአያንዳንዱ የጉራጌ ማህበረሰብ ልቦና ውስጥ እንደታተመ በአርግጠኝነት ልነግርህ አችላለሁ፡፡›› ብለውት ነበር፡፡ እነሆ አርቲስቱ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየን ሰባት ዓመት ሞላው አርቲስት አርጋው ማዘር እያለ የሚጠራቸውና ‹‹ባለቤቴም እናቴም›› የሚላቸው የ14 ልጆቹ እናት ወ/ሮ ጽጌ ከአርቲስቱ አንድ ዓመት ከስድስት ወር በኋላ ተከትለዋቸዋል፡፡በአጠቀላይ በሶዶ ክስታኔ ማህበረሰብ ውስጥ በረካታ አርአያ(ተምሳሌት) የሆኑ ሰዎች አሉ አነኚህም አሁን ላይ ላለው ትውልድ መሰረት የሆኑ ናቸው ስለዚህ አርቲስት አርጋው በዳሶ አሁን ላለው  ላለው ትውልድ ብዙ አስተምረውናልና የእነዚህን ምሳሌነት መጠቀም ግድ ይለናል፡፡

በቀለ የ16 ስድስት አመት ልጅ ሳሉ  እናታቸዉ ከአጎታቸዉ ገ/ማሪያም  ጋሪ ዘንድ አኖራቸዉ በቀለም እንዳደጉ የአጎታቸዉ እልፍኝ አስከልካይ ሆኑ ደጅ አዝማች ገ/ማሪያም ከ1923-1926  አመተ ምህረት ድረስ የሀረርጌ ጠቅላይ ግዛት እንደራሴ ሳሉ በቀለ ወያ ሻቃ የሚባል የማዕረግ ስም ተሰጣቸዉ በዚህም በረዳት ወታደርነት በአስተዳደር ስራ ላያ ተሰማርተዉ ቆይተዋል በ1927 አ/ምህረት ደጅአዝማች ገ/ማሪያም የሀገር አስተዳደር ሚኒስተር ተብለዉ ሲሹሙ አብረዋቸዉ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የታንክ መስበሪያ መሳሪያ አጠቃቀም ለማጥናት በቁ፡፡1928 ዓ/ም ፋሽስት ኢትዮጲያን ለመወረር ሲመጣ በመጀመሪያ ወደ ሰሜን ቀጥሎ ደግሞ በንጉሰ ነገስቱ ታዘዉ ወደ ሲዳሞ በመሄድ  በአጎታቸዉ ስር ያለዉን ጦር በመምራት ከፍተኛ ጀብድ ፈጽመዋል፡፡ስለዚህ ሁኔታ ታደሰ ዘወልዴ ቀሪን ገረመዉ በተባለዉ መጸሃፋቸዉ  እነዲ ይከትበዋል፡-‹‹የተላት ታንክ ወገንን በማጥቃቱ ደጅ አዝማች ገ/ማሪያም ጋሪ  በጣም ያዝኑ ነበር፡፡አንድ ቀን አምስት ታንኮች በመደዳ ሆነዉ ጦሩን እያጠቁ ሲመጡ ‹‹በቀለ ያንተ ብልሃት ለመቼ ሊሆነን ነዉ !አትለዉም ወይ !ወይኔ !›› እያለዉ ደጅአዝማች ጋሪ ሲያዝኑ  በቀለ ዝም ብሎ ይመለከተ ነበር፡፡ ታንኮቹ ጠጋ ብሎ በደንብ ሲያዉ  በመድፍ የመጀመሪያዉን አኮማትረዉ ፣ደግሚ የኁለኛዉን ደገመዉ  እንደዚህ በ5ደቂቃ አምስቱንም ታንክ አቃጥሎ ሲነድዱ‹‹ደጅ አዝማች !ሄደዉ እሳት ይሙቁ አላቸዉ›› ፡፡ ሻቃ በቀለ ደጅ አዝማች ገ/መሪያም ጋሪ ጦር የመድፍ ክፍል ሃላፊ ሆነዉ በማገልገልና በሲዳሞ ጦር ገንባር ገጥመዉ  በመደምሰስ

የጠላትን ጦር  መሳሪያ ማከማቻ አዉድመዋል በዚህ ጥረታቸዉ ከአጎታቸዉ ገብረ ማሪያምና ከባልደረቦቻቸዉ ምስጋና ሲቸራቸዉ ፤በጦርነቱ ደሞ ስምንት ባለ ዉሃ ከባድ መትረየስና  አስራ አራት ቀላል ድግን አልቤን መትረየስ ሲማርኩ ፤30የጣሊያን መኮንኖች  በቁጥራቸዉ የበዙ የጠላት ወታደሮች ተደባይተዋል፡፡ከዚህ በኃላ ከሰኔ 1 ቀን 1928 ዓ/ም አስከ መስከረም 23 ቀን 1929 ዓ/ም ብዙ ጦርነት ሲካሄድ ከእነዚህ ዋነኛዉ የደባ ስሬ ጠርነት ነበር ፡፡በዚህ ጦር ደጅአዝማች ገ/ማርያም ጋሪ ጋር ቢቆስሉም ሻቃ በቀለ ደግሞ ከ12 በላይ ታንኮችን በመድፋቸዉ በማዉደም የማይረሳ ታሪክ ሰርተዋል፡፡ በህዳር ወር (ከ13-19) ቀን 1929 ዓ/ም ድረስ በአለታወንዶ አካባቢ ተፈሪ ኬላ በተባለዉ ቦታ ጥር 12 1929 ዓ/ም ደግሞ አርቤጎና ላይ ጠር 15 ቀን1929ዓ/ም በዴላ ጭሪ ጥር 19 ቀን 1929 ዓ/ም በሂበኖ አሩሲ የካቲት አምስት፤10 እና  121 ቀን 1929 ዓ/ም በላቂ ደንበል የፈፀሙት ድል ከቶዉኑ አይረሳም፡፡አጎታቸዉ ደጅአዝማች ገብረ ማርያም በየካቲት 13 ፤1929 ዓ/ም ጎጌቲ ከነበረዉ ከባድ ጦርነት ህይወታቸዉ አለፈ፡፡

በዚህም ሻቃ በቀለ በጣም አዘኑ፡፡ ሙሉዉን ጠር  በመረከብ ከአክስታቸዉ የወ/ሮ ቡኔ በዳኔ ልጅ ከነበሩት በዳኔ ጉደታና ከሌሎች አረበኞች በመነጋገር ወታደራዊ ትጥቃቸዉን አጥብቀዉ በትዉልድ ሐገራቸዉ ሶዶ ጠላትን ተቋቁመዋል፡፡ በዚህ መሠረት ጦራቸዉን በማደራጀት በየካቲት ወር1930 ዓ/ም በሶዶና ሜጫ ወሠን ላይ ሁለት በአታላዩን የጠላት ጦር ገጥመዉ በድል ደምስሰዋል፡፡ በዚያዉ ጊዜ በአገመጃ ያካሄዱት ጦርነት ከጠዋቱ 12 ሰዓት 9 ሰዓት ድረስለ 10 ሰዓታት ያህል በአዉሮፕላን በመድፍ የመጣዉን ጠላት ገጠሙ፡፡ በጦርነቱ ብዙ የሶዶ ጀግኖች ተረፈረፉ ፡፡ሆኖም ድሉ የራሳቸዉ ነበር፡፡ይህንን ጀግንነታቸዉ የሰማ የሶዶ ህዝብ በጅምላ ይጎርፍ ጀመር፡፡በሶዶ ቶሎኔና በረጲ ጦርነትም የሻቃ በቀለ ጦር የጠላትን ጦር ድል እየመታ ስለቀጠለ ጣሊያን ፈርቶ ለ6ወር ያህል ርቆ ሎቆይ ተገደደ፡፡ በሶዶ አጨበር ፤ቁሻትና ኢትኒ ለ8 ሰዓት ያህል ተፈፈመ ጦርነት ተካሄዶ ድሉ የሻቃ በቀለ ሰራዊት ነበር፡፡ በተጨማሪ በሶዶ ጨከ ደራራ አገምጃ በሶዶና ወለኔ ወሠን ላይ የሲ፤ኦሞ፤ ጎደ፤ በተባሉ ቦታዎች አንፀባራቂ ድል ተጎናፅፈዋ፡፡ በወርሃ መስከረም 10 ቀን 1932 ዓ/ም ሶዶ ባንቱ በተባለዉ ቦታ ለ 7 ሰዓታት ያህል ተዋግተዉ ድል በማድረጋቸዉ  ሶዶ ህዝብ በኩራት እንዲመካባቸዉ አስችሏል፡፡ አጎታቸዉ ከሞቱ ወዲ ሻቃ በቀለ ከጎረቤት አርበኞች ጋር ህብረት መፍጠር ጀመሩ ፡፡ በተለይም ከዘመዳቸዉ ገረሲ ዱኪ ጋር ተባብረዉ ጠላትን የመደምሰስ ዕቅድ በማዉጣት ብዙ መክረዋል፡፡ በጋራም የጠላትን ጦር ይደመስሱ ነበር፡፡ ከገረሱ ዱኪ ጋር በበዳናሠ አቄሮና ሶዶ ከፍተኛ ጦር ዉስጥ  ተዋግተዋል፡፡ ለዚህ ጦርነት ምክንያቱ ሙሴ ቀስተኛ የተባለ የጣሊያን መልዕክተኛ ነበር፡፡ ሙሴ ቀስተኛ ገረሱን ለማጥመድ የተላከ ስለነበር  በገረሱ ተነቅቶበት የሞት ዉሳኔ ተበይኖበታል፡፡ ይህን አስመልክቶ ጠላት የሙሴ ቀስተኛን  ደም ለመቀበል ከጅማ፣ከሲዳሞ ከአርሲና ከሸዋ ጦር አሰባስቦ የገረሱን ጦር በመዉጋት ከፍተኛ  እልቂት አስከተለባቸዉ፡፡ገረሱ ሸሽተዉ ከሳቃ በቀለ ጋር በመገናኘት ለ3 ቀንና ሌሊት አርባ አራት ባታሊዮንይገመት ከነበረ ጦር ጋር በጣም ዘግናኘኝ የሆነ ጦር ተፋልመዋል፡፡ በአዉሮፕላንና መድፍ ብዙ ሰራዊት አለቀባቸዉ ፡፤ መሳሪያቸዉን በምርኮ ተወሰደ ፡፡ ሻቃ ቀኝ እጃቸዉ ስለቆሰለ መድፍ እንደልብ ባለመተኮሳቸዉ ጦርነቱ ለጊዜዉ ቆመ፡፡ በዚህ ምክንያት ጦሩ ተበተነ፡፡ በቀለ እስኪያገግም ድረስ ሻዋ ቡልጋ ሄደዉ ከአበበ አረጋይ ተነጋግረዉ የጦር ስልት ነድፈዋል፡፡መክረዉም ወደ ሶዶ ተመልሰዋል፡፡ በጋቢት 17 ቀን 1932 ዓ/ም ሻቃ በቀለ ከቀኝ አዝማች በየነ ጉደታ ጋር ሳሉ ከጠላት ወገን ደብዳቤ ደረሳቸዉ፡፡ የደብዳቤዉ መንፈስ እጅ ብትሰጡ ይሻላችኃልና አስቡበት የሚል ነበር፡፡ እነርሱም በደብዳቤዉ ድፍረት በሽቀዉ ትግላቸዉ የነፃነት መሆኑ በመድፍ መልስ ላኩላቸዉ፡፡ ስለዚህ መስከረም 22 1932 ዓ/ም ጦር ተከፈተ ፡፤ ሶዶ ዉስጥ ረጲ የተባለዉ ቦታ ከቀኑ 2 ሰዓት ጀምሮ ከባድ ጦርነት ተፋፋመ ብዙ የሻቃ  በቀለ ጦር እየፎከረ በጀግንነነት አለቀ፡፡ ቀኝ አዝማች በየነ ጉደታ ቆስለዉ ወዲያዉኑ እናታቸዉ ሐገር ሶዶ አገምጃ እንዲሄዱ ተደረገ፡፡ አዚያም ሳሉ የመግደል ሙከራ ገጠማቸዉ ሸሽተዉም ገረሱ ዱኪ ጋር መጡ፡፡ቁስላቸውም ሲድን ወደ በቀለ ወያ ለመሄድ መንገድ ሳሉ ጠላት ከበባቸዉ በዚህም ከጠላት ወገን 20 መኮንኖችንና ከ30 በላይ ወታደር መስዋዕትነትሆነዉ አለፉ፡፡ አብሯቸዉ የነበሩ ስድስት አርበኞችም አለቁ፡፡ሻቃ በቀለ ልባቸዉ ክፉኛ አዘነ ልባቸዉ ቂም አርግዞና ዉስጣቸዉ በበቀለ ሲናጥ ዉሎ ሚያዚያ 23 ቀን 1932 ዓ.ም ዝቋላ ላይ በልዩ ጦርነት ስልት የጠላትን እሬሳ አነባብረዉ  የወንድሞቻቸዉን ደም ተቀበሉ ግንቦት 27 ቀን 1932ዓ.ም ደግሞ ዝቋል ወንበራ ሌላ ጦርነት አድርገዉ ድልን ተቀዳጅተዋል፡፡በኮሌኔሉ አቡ የተባለዉን ከባድ የተባለ ጦረነት ገጠመዉ 26 የፋሽስት መኮንኖችና 60 ወታደሮች ገድለዋል፡፡ ታደሰ ዘዉዴ ጦርነቱን እንዲ ሲሉ መስክርነታቸዉን ሰጥተዋል፡፡‹‹18 ካሚዉን የነበሩትን ፋሽስቶች አንድ ሰዓት በማልሞላ ጊዜ ዉስጥ ጨረሰዋቸዉ ወዲዉኑ አስከሬናቸዉ በፍጥነት ወደ ነበረበት ካሚዉን እነዲሰ ከተደረገ በሁላ ናፍጣ አርከፍክፈዉና በእሳት አቀጣጥለዉ ለለቱን እንደ ጦፍ ሲነድ አደረ ››ይህን የሰሙ ፋሽስቶች ላብ አስመጣቸዉ ፡፡በጎጃ በላይ ዘለቀ የተፈራዉን ያህል በሶዶ ደግሞ በቀለ ወያ  በጠላት ወገን እጅግ ተፈሩ ፡፡ ጣሊያንም የሻቀ በቀለን ሰራዊት ለአንዴ ሊደመስስ በዙ የባንዳ ሰራዊትና ነጭ ወታደሮችን ከጅማ !ከሲዳሞ !ከናዝሪት! ከወሊሶ! ከአዲስ አበባ! ከአርሲ! አሰባስቦ ቶሌ በተባለ ቦታ 12፡ሠዓት የፈጃ ጦርነት ገጠሙ በሁለቱም ወገን አለ የማይባል ጦር አለቀ  የጠላት ወገን ግን እንዳለመዉ አልተሳካለትም ይልቁኑ የበቀለ ወያ ጦር  ከገረሱ ዱኬ በመተባበር አሳዶ  እየወጋዉ ብዝዎችን ማረከበት ሻቃ በቀለ አምስቱንም አመት ሙሉ ለኢትጶያ ቆስለዋል፤ተንከራተዋል በጀግንነትም የጠላትን ጦር ደምስሰዋል፡፡ንጉሰ ነገስቱ ከስደት እንደተመለሱ እንዘህም መአረጎች አግኝተዋል፡፡

1.በ1933ዓ.ም በፊት አዉራሪነት ማዕረግ የሲዳሞ ጥብቅ አስተዳዳሪና የክብረ መንግስት የወርቅ ማዕድን ኃላፊ

21933ዓ.ም የሁለተኛ ሬዥ ማን አዛዥ

3.1934ዓ.ም በወለጋ የሶዩ አዉራጃ ገዥ

4.1935ዓ.ም በጀጅ አዝማችነት ማዕረጋ የጨቦና ጉራጌ አዉራጃ ገዥ

5.1936ዓ.ም የወላይታ ገዥ

6.1938ዓ.ም በሐረር የጨርጨርና ኢሳ አዉራጃ ገዥ በመሆን ሰርተዋል

ደጅ አዝማች በቀለ ወያ በስራ ላይ እያሉ በአደረባቸዉ ፅኑ ህመም ምክንያት ለህክምና ወደ ሲዉዘር ላንድ በጉዞ ላይ ሳሉ ሚያዚያ 6/1946ዓ.ም አርፈዋል፡፡አስከሬናቸዉ ሚያዚያ10ቀን 1946ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ መጥቶ በዙ ዘመድና አዝማድ የመንግስት ባለ ስልጣናት የአርበኞች ማህበር አባላት በግልና በዝና የሚያዉቃቸዉ የአዲስ አበባ ህዝብ በተገኘበት በስላሴ ቤተክርስቲያን በደማቅ ስነ-ስርዓት ታጅበዉ የቀብር ስነ ስርዓታቸዉ ተፈጽሟል፡፡፡ ሻቀ በቀለ ወያ መቼም የማይረሱ ጀግና በመሆናቸዉ ይህ ግጥም ማስታወሻቸዉ ሆኖ ይኖራል፡፡

     ‹‹ አላስኬድም አለኘኝ ጣሊያን በመንገዱ ፤

      ያሻቃ በቀለናአ ወንዱና ወንዱ

አርቲስት ጸጋዬ ስሜ

አርስት ጸጋዬ ስሜ ድምጻዊ የግጥምና ዜማ ደረሲነት ደግም የተሰጠዉ መክሊቶቹና መተዳደሪያዉ ናቸዉ ፡፡የተወሰደዉ በማዕከላዊ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ደቡብ ሶዶ ወረዳ ኑረና ቀበሌ ልዩ ሰሙ ጊዩርጊስ ተብሎ የሚጠራ አካባቢ  ተወለደ፡፡የአምስት ዓመት ልጅ ስለ መኖሪያዉን ከተወለደበት አካባቢ ወደ አዲስ አበባ በመቀየር በቄስ ት/ቤት የፊደል ጉዞዉን ሀ ብሎ ጀመረ፡፡ ገሊላ ት/ቤት ፣ቅዱስ ጰዉሎስ፣እቴጌ መነን ት/ቤት እስከ 8ኛ ክፍል ተማረ፡፡ በመቀጠልም የ2ኛ ደረጃ ት/ቱን በአዲስ ከተማ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት  እስከ  12ኛ ክፍል ተምሯል፡፡በጄነራል ዊንጌት ለአራት ዓመታት የጂኤም ትምህርቱን ተከታትሎ ዲፕሎማ አግኝቷል፡፡ግን በዚህ ሁሉ የት/ቤት ቆይታ ፀጋዬና የክበባት ተሳትፎ ጭራሽ አይታወቁም፡፡

የእሱ ዋና አላማ ትምህርት ተምሮ በተማረዉ ት/ት ሀገሩን ማገልገል ነበር፡፡በሰፈርም በትምህርት ቤት አካባቢም ትርፍ ሰዓት ሲያገኝ እግር ኳስ መጫወት ያስደስተዋል፡፡ ሰፈር ዉስጥ በሚደረጉ ሠርግና መሰል ዝግጅት ልቡ እስኪጠፋ ይጨፍራል፡፡ዘፍን ለመዝፈን አስቦም አልሞም አያዉቅም፡፡ በቃ ድግስ ካለ እሡ በጭፈራ አድማቂ ነዉ፡፡ከአምስት ዓመቱ ጀምሮ የአዲስ አበባ ነዋሪ ቢሆንም በየክረምቱ ወደ ትዉልድ አካባቢዉ መሄድ የዓመት ዓመት ልምድ ሆነ፡፡ በጋ በአ/አበባ ትም/ቱን  ሲከታቲል ይቆያል ክርምት ላይ በመደበኛነት ሀገር ቤት ይገባል፡፡ አዲስ አበባ ሲመለስም በተደጋጋሚ ቋንቋዉ የሚችሊ ሰዎች  እየፈለገ ስለሚያወራ መለያ ስሙ ፀጋዬ ክስታኔዉ ሆነ በ1982 ዓ.ም  ከዊንጌታ መመረቀን ተክትሎ ከቤተሰብ ጫና በመዉጣት የራሱ ገቢ ለማመንጨት ጓጉታል፡፡ በሀገሪቱ ለዉጥ ወቅት አይሩን ተቆጣጥሮ ታል፡፡እሡ ግን እራሱን ሊችል ስለሆነ ሃሳቡ በሙሉ እራስ መቻል ላይ ነበረ፡፡

ከተማረበት ት/ቤት ስም ዝርዝራቸዉ ተወስዶ በአምቦ የጦር መሳሪያ መገጣጠሚያ ፋብሪካ ስራ እንደሚጀምር ተነግሯቸዉ ልቡ ጮቤ ረግጧል፡፡ለቤተሰብ  የመጀመሪያ  ልጅ እንደመሆኑ የቤተሰብ ደጀን ሆኖ የታናናሾቹን መከታ ሊሆን ተዘጋጅቷል፡፡ እሱን  ያዩ ታናናሾቹ በሱ ፈለግ እንደሚከተሉ በማሰብ ተደስቷል፡፡ ግን ይህ ሁሉ ጮቤ መርገጥ ሳይሰምር ቀር የዚህ ምክንያቱም ሹፌር የነበሩት ወላጅ አባቱ በዚህ ቀወጡ ሰዓት  ምን ሲያደርግ  መሳሪያ   ፋብሪካ ተቀጥረሃል አይሆንም አሉ፡፡

 

ክስታኒኛ በደንብ መቻሉ ጠቅሞት የክስታኔ ልማት ማህበረ በክስታንኛ  ቋንቋ በሚያዘጋጀዉ ጋዜጣ ላይ በጋዜጠኝነት መስረት ጀመረ ፡፡ ታዲያ ያኔ የማህበሩ አካል የነበሩትና በዘርፉ የዳበረ ልምድ ያላቸዉ ተክሎ ታኮር በጋዜጠኝነት ለመሰማራት  እንዲያስችለዉ ለአንድ ሳምንት የጋዜጠኝነት  መስራት  ጀመረ ታዲያ የኔ የማህበሩ  አካል  የነበሩትና በዘርፉ የዳበረ ልምድ ያላቸዉ  ተክሉ ታኮር በጋዜጠኝነት  ለመሰማራት እንዲያስችለዉ ለአንድ  ሳምንት የጋዜጠኝነት ስልጠና ሰጥተዉታል፡፡ፀጋዬም በክስታኒኛ  ግጥም ይፃፋል ዘፈኖችን ያንጎራጉራል  ግን  አንድም ቀን ዘፋኝ  እሆናለሁ ብዬ አስቤ አላዉቅም ነበር ይላል፡፡

 

በ1988 ዓ/ም  የዋለዉ የፋሲካ  ዋዜማ ከሌሎች ይለያል፡፡ከጓደኞቹ ጋር ሰብሰብ ብለዉ ለመዝናናት  በማሰብ አብነት አካባቢ የሚገኘዉ ምሽት ክበብ ይገባሉ፡፡ቤቱም ሰዎች ተሞልቷል፡፡ በቤቱ የሙዚቃ ባንድ መኖሩ ተመችቶታል በሙዚቃዉም በመጠጡም እየተዝናኑ ነዉ፡፡ በዚህ መሀል የጉራጊኛ ዘፈን ሊዘፍን  አንድ ልጅ ይመጣል፡፡ ልጁ ቋንቋን ባለማወቁ  በትክክል እየዘፈነ  አይደለም ፡፡ በዚህ የተናደደዉ ፀጋዬ  ከመድረክ ሲወርድ ጠብቆ የዘፈነዉ  ቋንቋ ትክክል አለመሆኑን  ይነግረዋል ከፈለገ ትክክለኛ ግጥም እንደሚጽፍለት ቃል ይገባለታል፡፡ በመሃል ለምን እኔ አስተካክዬ አልዘፍንም በሚል  ወኔ ይገባለታል፡፡በመሃል ለምን እኔ አስተካክዬ አልዘፍነዉም በሚል ወኔ መድረክ ላይ ይወጣል ከታዳሚነት ወደ ዘፋኝነት ተሻጋግሮ እራሱን መድረክ ላይ ተበላሸ ያለዉን  ዘፈን ሲያስተካክል ያገኘዋል፡፡ አንድም ቀን ሳይለማመድ ለልምምድ ለባለሙያ ሳይዘፍን በመሳሪያ ተጫዋቾች ታጅቦ ለታዳሚዎች ሙዚቃን አቀረበ ምንም እንኳን ‹‹ፒች›› የሚባሉ የሙዚቃ ፅንስ ሀሳቦች ለሡ እሩቅ ቢሆኑም አርጋዉ በዳሶን ዘፍን በሙዚቃ መሳሪያ ታጅቦ ዘፈነ  ቤቱን የሞላዉ ታዳሚዉ ፀጋዬን በሽልማት አጥለቀለቀዉ ከሽልማቱ ለዘላለም ሁሉም ታዳሚ ብላልኝ ጠጣልኝ ባዩ በማግስቱም ‹‹የኔ ጌታ እባክህ  እንዳትቀር ››ሲሉ የተማፀኑትን የቤቱ ባለቤትን ልመናና ሽልማት አስታወሱ በዕለቱ ፋሲካ ማምሻዉን ሄደ በማግስቱም የታዳሚዉ አቀባበል ለየት ያለ ቢሆንበት በህይወቱ  ለመጀመሪያ ጊዜ ይሄ ነገር እንጀራዬ ይሆን አንዴ  ሲል አሰበ ሆኖም የዘፈን ጥናት ልምድ የለዉምና ይደገም ቀርቶ ይሰልስ ቢባልም የሚያዉቀዉ ሆነ  የሚዘፍነዉ ብቸኛ ዘፈን የአርጋዉ በዳሶ  አለምብሬን ብቻ ነበር በልማት ማህበሩ  የቢሮ ሠራተኛ  ሆኖ ተቀጥሮ እየሠራ ነዉ ፡፡

 

በልማት ማህበሩ አማካኝነት የክስታኔ ባንድ ሲቋቋም ከመስራች አባሎች  አንድ ሆነ ባንድ ከፀጋዬ ሲሜ ባሻገር  ጎሳዬ ተስፋዬ አብነት አጎናፍርና ሌሎችም በርካታ ሙዚቀኞችን አቅፎ ስራ ጀመረ፡፡ ፀጋዬ የጉራጊኛ ዘፋኝ በመሆን ባንዱን ተቀላቀለ  ለሡ የኪነ-ጥበብ መንገድ ተጀመረ እንሾሽላ ሠርግ መልስ ሲባል አብዛኛዉን ቀን  የስራ ቀናቸዉ እንደነበርና በሳምንት ረዕቡ ብቻ ያረፍ እንደነበር ያስታዉሳል፡፡ፀጋዬ ችላ ካላት መክሊቱ ብሎ ብዙም ዋጋ ከልከፈለላት ሙዚቃ ጋር በባንድ አማካኝነት በደንብ ተግብብቷል፡፤ መድርክና ዝግጅት ላይ ከመሰረት በዘለለም ክስታኔ ሲሉ የሰየሙትን  የመጀመሪያ አልበማቸዉን  በባንድ አማካኝነት ሶስት  ድምጻዉን ተጣምረዉ  ለአድማጭ አንካቹ አሉ አልበሙ  ሙሉ የሙዚቃ መሳሪያ ገብቶላት የተቀረጻ ሲሆን  የአልበሙ በአብዛኛዉ ክፍል የተቀናበረዉ የባንድ ኪቦርዲስት በነበረዉ ድምጻዊ አብነት አጎናፍ ነበር፡፡

 

 

ፀጋዬ  ክስታኔ ባንድ እየሠራ ነጠላ ብሎ ለብቻዉ ሁለተኛ አልበሙን  አወጣ የህዝቡን ተቀባይነት እየጎላ ሲመጣና በየቦታ ፈላጊዉ ሲበዛ ከባንድ ተቀጣሪነት ወደ ባንድ ባለቤትነት ተሻጋገረ የራሱን ባንድ ስኛት ባንድ ሲል መሰረቱ ያም ቢሆንም የመጀመሪያዉን ባለዉለታዉን  የማይረሳዉ ድምጻዊ ክስታኔ ባንድ  ዛሬ ባይኖርም ከህዝብም ጋር ያስተዋወቀኝ ባለዉለታዬ በማለት ያስታዉሳል፡፡

 

በ1996 ዓ.ም ጳግሜ አራት የወጣዉ የፀጋዬ ሶስተኛ አልበም የሙዚቃዉንም ሆነ የህይወት ማርሽ ቀያሪ አልበም ነዉ፡፡ የአልበሙ መጠሪያ እንሾሽላ ሲሰኝ የድምጻዊዉ መጠሪያ እስኪሆን የታወቀበት ኦሴ ባሳ የተሰኘዉ ሙዚቃ የተካተተበት ነዉ ፡፡ ድምጻዊዉ ‹‹ኦሴ ባሳ›› ከጉራጌ ማህበረሰብ አልፎ በመላዉ ኢ/ያን እንድታወቅ ያደረገኝ ዘፈን ነዉ ይላል፡፡ድምጻዊ በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ ሴት ልጅ ሳታገባ ካረገዘች ፣ስርቆት ካጋጠመ ፣በአጠቃላይ መሆን ያልነበረበት ነገር ሲሆን ከታየ ትልልቅ  ሰዎች‹‹ይሄ ሆሴ ባሳ ነዉ›› እንደሚሉና የማዋገዣ ቃል መሆኑን ያነሳል፡፡ በዘፈኑ ጆሮዬ ወጥፎ ነገር አትስማ  ሲል መክሮበታል፡፡ ኦሴ ባሳ መወጣቱን ተከትሎ ፀጋዬ በርካታ የስራ አማራጭ የተሻለ ገቢ እንዲሁም የህዝብ ፍቅርና እዉቅና ያገኘበት ስራዉ ነዉ፡፡ስራዉን የሕይወቴ ለዉጥ ይለዋል፡፡ስራዉ 20 ዓመት ቢጠጋዉም አሁንም መድረክ ላይ በወጣ ቁጥሮ ሁሴ ባሳን ኦሴ ባሳን ይላል፡፡ፀጋዬን ያየ ታዳሚዉ  ኦሴ ባሳን  ሳይዘፍን መዉርድ የማይታሰብ  መሆኑን ይነገራል፡፡ ታዳሚዉ ቀድሞ ኦሴ ባሳን  እንደሚሰማ እርግጠኛ ይሆናል፡፡

ዬሻለ የተሰኘዉ አራተኛ አልበሙን  በ2000 ዓ/ም ለአድማጭ አድርሷል በ2005 ዓ/ም የወጣዉ ‹‹ጥም ቢሳሳ›› አምሰተኛ አልበሙ ሲሆን የመጨረሻዉ  አልበሙ ሲሆን የመጨረሻዉ አልበሙ ‹‹ሱታና›› ይሰኛል፡፡ድምጻዊዉ በሀገር ዉስጥ በበርካታ ከተሞች ተዛዋዉሮ ስራዎችን አቅርቧል፡፡ ባህሬን ፣ኳታር ፣ዱባይ፣ኤርትራ ታዳሚዎቹን አዝናንቷል፡፡በቡታጅራ መስመር በምትገኘዉ ቡኤ ከተማ የገነባዉ ኦሴ ባሳ ሄቴል ተመርቆ ስራ ከጀመረ አንድ አመት ተሸግሯል፡፡ በቀጣይነት ለኑሮ መደጎሚያ ከሡ የሙዚቃ ስራና ከባለቤቱ መደበኛ  ስራ ተጨማሪ ደጓሚ እንደሚሆናቸዉ ተስፋ አድርጓል፡፡ ድሮ ክትፎ ዋነኛ ምግብ ምርጫዉ ነበረ ፡፡ዕድሜ ጨመር እያለ መሄዱን ተከትሎ የምግብ ምርጫዉ  በጎመን ክትፎ በአይብ ተተክቷል፡፡ሁሉንም ስራዎችን እወዳለሁ የሚለዉ ድምጻዊዉ አጥብቄ ስጠይቀዉ ግን ‹‹አዲስ ባላአገር ነዉን››የተለየ እንደሚወደዉ ምስጥር ያወጣል፡፡ አዲስ ባላገር ነዉ(እኔስ ባላገር) ኦሴ ባሳ የሚገኘበት  ሶስተኛ አልበሙ ላይ የተካተተ ስራዉ ሲሆን አስተዳደጉን የሚገለፅበትና አሁንም ባላገር ነኝ የሚልበት ተወዳጅ ዘፈኑ ነዊ፡፡ በተጨማሪም በተለያየ ጊዜያት የወጡ የሰጣቸዉ ሲሆን  ከቡዙ በጥቂቱ በአመልማል አባት ፣አብነት አጎናፍር ፣ሻምበል በላይነህ ፣ምናሉሽ ረታ፣ደርብ ዘነበ እና እንዳሻዉ ጥላሁን እና ሌሎቹም የግጥምና ዜማ ስራ አበርክቷል፡፡ በጋራ በህብረት‹‹ናልማነ››የጉራጊኛ ስራዉ ለህዝብ  አቅርቧል፡፡

የጋዜጠኛ ሶዶ ለማ ጋሻው

ተወልዶ ያደገው በቀድሞ ደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ጎሴ ሳለን ቀበሌ ነው። አባቱ አቶ ለማ ጋሻው ከሶዶ ወረዳ ደጋ ኑረና ”ቡኒ ገብርኤል” አካባቢ፤ እናቱ ወይዘሮ ኩሪ ሀይሌ ሻይ ደግሞ ከምድረ-ከብድ ”አረትጌ” ነው ተወልደው ያደጉት።

ጋዜጠኛ ሶዶ ለማ ወላጆቹ ካፈሯቸው 11 ልጆች(1ዐ ወንዶችና 1 ሴት) 10ኛው ሲሆን በ1981 ዓ.ም ነው የተወለደው። የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን ከሴት አያቱ(የእናቱ እናት) ጋር በመሆን በአዴሌ ቦሮቦር 1ኛ ደረጃ ት/ቤት በማጠናቀቅ የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በኑረና ኬላ ተምሯል። ጋዜጠኛ ሶዶ ለማ ለዛሬ የጋዜጠኝነት ሕይወቱ የመጀመሪያውን ጡብ ማስቀመጥ የጀመረው በነዚሁ ጊዜያት በትምህርት ቤቶች በሚደረጉ የጥበብ እንቅስቃሴዎች ነበር። በአዴሌ ቦሮቦር ትምህርት ቤት በነበረበት ወቅት እድሜውም ሆነ አካላዊ ቁመናው ትንሽ የነበረ በመሆኑ በተማሪዎች ሰልፍ ላይ ከፊት የመጀመሪያው ቋሚ እንደነበረ ብዙዎች ያስታውሳሉ። በዚሁ ጊዜ ከእድሜው አንፃር የማይጠበቁ ተግባራትን በማከናወን የትምህርቱን ማሕበረሰብ ያስገርም ነበር። ከጥበብ አልፎ በስፖርቱ ዘርፍ በተለይ በመረብ ኳስ ብቃቱ ትምህርት ቤቱ በወረዳው ከአቻ ትምህርት ቤቶች ያደርገው ለነበረው ግጥሚያ ሁነኛ ተሰላፊ ነበር።

 

ሶዶ በዚያ ወቅት በጥበቡ ዓለም የሚያደርገው እንቅስቃሴ የነገ እንጀራውን በብዙው ይወስን እንደነበረ ብዙዎች ምስክር ናቸው። ፈጣንና ፈጣሪ ነበር። በተማሪዎች ሰልፍና የሰንደቅዓላማ ሥነሥርዓት ወቅት የተለያዩ አዝናኝ የኪነጥበብ ውጤቶችን በድፍረትና በብቃት በማቅረብ አስተማሪዎቹን ጭምር ያስደምም ነበር። በአንድ ወቅት በየአመቱ ሰኔ 30 ይከበር በነበረው የወላጆች በዓል ቀን በቀረበ ድራማ እንዲጫወት የተሰጠውን የሟች ገፀባህርይ እጅግ መስሎ በመጫወቱ ሊታደሙ የመጡ አባቱን በድንጋጤ ቁጭ ብድግ በማስደረግ ”ልጄ ተገደለ” ብለው በትክክል እስከማዘን የደረሱበት ቅፅበት ዛሬም ጋዜጠኛ ሶዶ ለማ የትውስታ ገጠመኞች መካከል ይነሳል።

 

ሶዶ ለማ በዚሁ የአፍላ ዕድሜ የጥበብ ሥራዎቹ በመቀጠል በኬላም ከትምህርት ቤት አልፎም ከተማው ውስጥ በነበረ ”ኖኅ አማተር የጋዜጠኞችና ፀረ ኤድስ ክበብ” የተሰኘ የወጣቶች የኪነጥበብ ማህበር በንቁ ተሳትፎው ቀጥለ።

 

በዚሁ ጊዜም ከአቻዎቹ ጋር እስከ አጎራባች ወረዳዎች እና ከተሞች በመጓዝ ድራማዎችን፣ ሥነ-ፅሁፍ እና የፀረ ኤችአይቪ ትምህርት መረጃ ይሰጥ ነበር። የኬላ ከተማን በመወከልም የተለያዩ የጥበብ ሥራዎችን አቅርቧል።

 

ጋዜጠኛ ሶዶ ለማ የመሰናዶ ትምህርቱን ለመከታተል ወደ ቡኢ ከተማ ሲያቀናም እነዚሁን ክህሎቶቹ አሳድጎ በመሆኑ በትምህርት ቤቱ እና አንዳንዴም በወረዳው ሚኒ-ሚዲያ የነቃ ተሳትፎ ያደርግ ነበር።

 

ሶዶ በቡኢ ቆይታውም የ12ኛ ክፍል ትምህርቱን አጠናቆ ዩኒቨርስቲ ሊገባ ሲሰናዳ ሁሉም ሰው በከፍተኛ ትምህርት ተቋም የጋዜጠኝነት ትምህርትን መከታተል እንዳለበት ነበር ምክረ-ሃሳብ ይሰጠው የነበረው። ጋዜጠኛ ሶዶም በምርጫው መሠረት ዲላ ዩኒቨርስቲ የደረሰው ሲሆን በድጋሚ በምርጫው መሰረት የጋዜጠኝነት እና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ክፍልን በከፍተኛ ውጤት ተቀላቀለ። አሁን የዘልማድ የነበረው የሶዶ ጋዜጠኝነት ሙያዊ መስመር ያዘ!

 

በዲላ ዩኒቨርሲቲ ባሳለፋቸው 3 የትምህርት አመታትም እንደ መቅረዝ የኪነጥበብ አፍቃሪያን ሕብረት እና ቻሪቲ የበጎ አድራጎት ክበብ ውስጥ የፊትለፊት ሚና ነበረው። በግቢው ውስጥ በአጭር ጊዜ በሁሉም ሰው ዘንድ ታዋቂና ተወዳጅ መሆን ቻለ። በትምህርት ክፍሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቋቋመውን ”ተስፋ ጋዜጣ” ከመሰረቱ የጋዜጠኝነት ተማሪዎችም አንዱ ነው። ያኔም ”ለጋዜጠኝነት የተፈጠሩ…” ይባሉ ከተበሩ የግቢው ተማሪዎች አንደኛው የነበረው ሶዶ ለማ በ2003 ዓ.ም በከፍተኛ ውጤት ተመርቆ አጠናቀቀ። ዲላንም ለቀቀ።

 

ከዚያ በኋላ የሚቀጥለው የሥራ ገበታ ማፈላለግ ነው። ታዲያ ሶዶ ተመርቆ እንደወጣ ሥራ አላገኘም። የሚዲያ ማዕከላት ቁጥር እንዳሁኑ ለምርጫ የበዙ አልነበሩምና ሶዶ ለአንድ ዓመት ተቀመጠ። በዚህ ሁሉ ጊዜ ግን ከወረዳና ዞኖች በኮሙኒኬሽን ባለሙያነት እየተወዳደረ ያልፍ የነበረ ቢሆንም ጋዜጠኝነቱን በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ( ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን) ለመጀመር ከነበረው ፅኑ ፍላጎት የተነሳ ጥሪ ሲደረግለት ውድቅ እያደረገ ነው የቆየው።

 

በመጨረሻም በደቡብ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት የወልቂጤ ቅርንጫፍ ማስታወቂያ አወጣ። ሶዶ ለማ በወቅቱ (ሌላ መንገድ ስላልነበረ) በአዲስ አበባ በኩል አድርጎ ተጉዞ ፈተናውን ወሰደ። አንደኛ በመውጣትም የወልቂጤ ኤፍ.ኤም 89.2 ሬዲዮን ተቀላቀለ። በሙያውም የወልቂጤ ኤፍ ኤምን ስም ማስጠራት ከቻሉ ጥቂቶች ውስጥ አንዱና ዋነኛው ሆነ። በከተማዋም በተለያዩ የሙያ አገልግሎቶቹ ተወዳጅነትን አተረፈ።

 

በወልቂጤ ኤፍ ኤም ለ3 አመት ገደማ ከሰራ በኋላ በነበረው ከፍተኛ አፈጻጸም ወደ ዋናው ተቋም ሐዋሳ ተዘዋወረ። በሐዋሳም በመዝናኛ እና ዜና ክፍል ለ2 ዓመታት በማገልገል በመላ የቀድሞ ደቡብ ክልል አድማጮች ተቀባይነትን ያተረፈ ሲሆን በነበረው የማያቆም ጉጉት ወደ አዲስ አበባ አማተረ። ከደቡብ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ወደ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አቀና። በፋና ኤፍ. ኤም 98.1 እና የኋላኋላ በተመሠረተው ፋና ቴሌቪዥን ፋና ዘጠናና ፋና ዜና በተፅዕኖ ፈጣሪነቱ ቀጠለ። በፋና ቆይታው ትልልቅ ሁነቶች ውስጥ በነበረው የቀጥታ ዘገባና አቀራረብ ልዩነት ፈጥሮ ስመጥር ሆነ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አደጋ እና የትግራይ ክልል ጦርነት ከነዚህ መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

 

ጋዜጠኛ ሶዶ ለማ ለውጥ ናፋቂ ስለመሆኑ ብዙዎች ይናገራሉ። በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ለ6 ዓመታት ገደማ የነበረውን ቆይታ (ለጊዜውም ቢሆን) በማቆም ወደ ሃገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አመራ። በዚያም ለአንድ አመት ያህል በዜና፣ ወቅታዊ እና የውጭ ዜና ዲፓርትመንት ስር ከሰራ በኋላ ዳግም ወደ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በመመለስ በቴሌቪዥን እና ሬዲዮ እያገለገለ ይገኛል።

 

በተጓዳኝ በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በኮሙኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ሥራ አስኪያጅነት እየሰራ ይገኛል።

 

ጋዜጠኛ ሶዶ ለማ በወረዳችን  ከተመሰረተ ጀምሮ ወረዳው ለማቋቋምና የተለያዩ በዓላት ላይ በሚዘጋጁበት ፕሮግራሞች ላይ በመገኘት የማስተባበር  እና ድጋፍም ጭምር አድርጓል። በተጨማሪም የፅ/ቤታችን አካል ለሆኑት የፈርሻታ የኪነት ቡድን ጓደኞቹን በማስተባበር  በጋራ በመሆን የሞንታርቦ ድጋፍ አድርጎልናል።የክስታኔ ባህል ከፍ ብሎ እንዲታይ የሚያደርግ እና አርአያ የሆነ እውቅ ጋዜጠኛ ነው።

 

ጋዜጠኛ ሶዶ ለማ በሐገራዊና አካባቢያዊ ጉዳዮች እጅግ ተቆርቋሪ ነው። በተለይም ለትውልድ አካባቢው ቋንቋ እና ባሕል እጅግ ቀራቢ መሆኑ ይወደድለታል። በማሕበራዊ ትስስር ገፆቹም ተፅዕኖ ፈጣሪ ጋዜጠኛ ነው።

 

ወጣቱ ጋዜጠኛ ሶዶ ለማ ባለትዳር እና የአንድ ሴት ልጅ አባት ነው።