እንኳን ወደ ደቡብ ሶዶ ወረዳ በሰላም መጣቹ

በተመሳሳይም የዘቢደር ተራራ አካል በሆነው በደቡብ ሶዶ ወረዳ ከፍተኛው ተራራ ላይ የሚገኘውም የጉንባር ናዳ ጥቅጥቅ ደን ሲሆን የሚሸፍነውም ወደ 4.3 ሄክታር ነው

የዳዮ አቦ ተራራ

በሶዶ ወረዳ ከሚገኙ ከፍተኛ ተራራማ ቦታዎች በዋናነት ከሚታወቁት መካከል የዳዮ አቦ ተራራ ማራኪ መልከአ ምድራዊ አቀማመጥ መቀመጡ ዋነኛ ተጠቃሽ መሆኑን ገልፀው ይህ ለአይን ማራኪና ውብ ቦታ ከባህር ጠለል በላይ 3ሺ 24ሜትር ከፍታ ላይ ሲገኝ በውስጡ ጥንታዊ ቤ/ክርስቲያን፣ እድሜ ጠገብ ዛፎች፣ ምቹና ተስማሚ የአየር ፀባይ፣ እንደሚገኝና በአመት ሁለት ጊዜ ጥቅምት 5 እና መጋቢት 5 የሚከበሩ አመታዊ ክብረ በዓላት እንዳለና በክብረ በአሉ ወቅት በርካታ ቁጥር ያለቸው ምዕመናን

በዳሙ-1 ቀበሌ ደን

ዳሙ-1 ቀበሌ በደቡብ ሶዶ ወረዳ ከሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች አንዱ ሲሆን ቀበሌው ቱሪስቶችን ቀልብ ሊስቡ፣ሊያማልሉና ግርምታ ሊያጎናጽፉ የሚችሉና ለአካባቢውም ማህበረሰብ የመንፈስና የአዕምሮ ግርካታ ሊሰጡ የሚችሉ ተፈጥሯዊና ማራኪ የመሬት አቀማመጥ፤እድሜ ጠገብ ሀገር በቀል ዛፎችና ደን የሚገኙበት ሲሆን ይህ ደን በርካታ የዱር እንሰሳቶችንም መኖሪያ ሲሆን ደኑ የአየር ንብረት እንዳይዛባ ያደረገው አስተዋጸኦ ቀላል አይደለምል፡፡

በዳሙ-2 ቀበሌ ውስጥ የጂገና ጊዮርጊስ ደን ነው

የጎሴ ሳለ ቀበሌ ጥብቅ ደን ሲሆን ወደ 20 ሄክታር ነው