መስቀልን በሶዶ ክስታኔ

መስቀልን በሶዶ ክስታኔ ስናከብር መንፈሳዊና ባህላዊ እሴቱ ለትውልድ ተሻጋሪ ከማድረግ ባሻገር ማህበራዊ ፋይዳውን በማሳደግ የማህበረሰቦች ግንኙነትና ትስስር በማጠናከርና የማህበረሰቡን መልካም እሴቶችና አጠቃላይ መስተጋብሩን በማልማትና በማበልጸግ ለቱሪዝም ልማት በማዋል ተጠቃሚነታችንን ለማረጋገጥ ነው፡፡

መስቀል በሶዶ ክስታኔ ፋይዳው ከፍተኛ ሲሆን ጥቂቶችን እንኳ ብንጠቅስ በተቃራኒ ፆታዎች መሀከል የጮኝነት ጥያቄ የሚቀርብበት ፣በሁለት ጥንዶች መሀከል ጋብቻ የሚመሰረትበት ፣ወላጆች የሚያስፈልጋቸውን በመያዝ በልጆቻቸው የሚጎብኙበት፣በአካባቢ ያሉ ድሆች የሚታሰቡበት፣የተጣላ የሚታረቅበት፣የሙት ቤተሰቦች የሚፅናኑበት፣ስለ ቀጣዩ የሕይወት ዘመን ምክክር የሚደረግበት፣ለበዓሉ የመጡ ተወላጆች ሲመለሱ በአንጋፋ አባቶችና እናቶች ተመርቀው የሚሸኙበት፣በጉራጌ የጋራ ጉዳዮች የሚመከርበት፣ቀጣይ አቅጣጫ የሚመላከትበትና አንድነታችንን በማጠናከር ፍፁም ተግባቦትን በመፍጠር ረገድ ዓላማው እጅግ ሰፊ ነው፡፡

በሶዶ ክስታኔ የመስቀል በዓል የመጨረሻ ምዕራፍ ዝግጅትና የቀናት አሰያየም፡-

የመስቀል በዓል በሶዶ ክስታኔ አስቀድሞ ሰፊ ቅ/ዝግጅት ከተደረገበት በኋላ በዓሉ ከመስከረም 12 እስከ ጥቅምት 5 ድረስ ለበዓሉ ተብሎ የተዘጋጁ ምግቦችና መጠጦች እየተጠቀሙ በታላቅ ደስታና ጭፈራ እንዲሁም በህዝቡ ማህበራዊ ህይወት ውስጥ ልዩ ልዩ ክንዋኔዎችን በማከናወን የሚከበር ሲሆን የቀናቶቹ ስያሜና የሚከናወኑት ተግባራት ቀጥለን እንመለከታለን፡፡

የሚባል ሲሆን በመስቀል በዓል ለምግብም ሆነ ለመጠጥ ማቅረቢያነት የሚውሉ ቁሳቁሶች ከየግድግዳውና ከተሰቀለበት ስፍራ ሁሉ በማውረድ ታጥበውና ጸድተው እስከ ጥቅምት 5 ድረስ ለምግብ ማቅረቢያነት አገልግሎት የሚቆዩ ሲሆን ይህ ቀን በሶዶ ክስታኔ አጠራር “ሌማት ይዎርድቦ ቀነ” ይባላል:

የሚባል ሲሆን በዚህ ቀን ሴቶች የመስቀል በዓል ዝግጅታቸውን አጠናቀው ለመስቀል ተብሎ በተዘጋጀው በሁሉም የምግብ አይነቶች ላይ ሙከራ ስለሚደረግ ሴቶች የሚጠግቡበትና ልጆች እንቅልፍ የሚያጡበት ቀን ነው፡፡

ዎልቀነ ዎልቀነ

ምሽት ይገራቦ ቀነ

ታምብል ይጋም ኮነ

ለሁሉም የቤተሰብ አባል በተዘጋጀለት “ደንጋሳ” የጎመን ክትፎ የሚበላበት ቀን ነው፡፡ በዚህ እለት ማታ በየደጃፉ ትንንሽ ዳመራ የሚያቃጥል ሲሆን “የባዮች ኧሳት” ይባላል፡፡

የሚባል ሲሆን ይህ ቀን በማህበረሰቡ ዘንድ ዋናው የመስቀል በዓል የሚከበርበት እለት ነው:በዚህ ቀን አባወራው ያረደው ስጋ ድንገት ጉፋያ ከሆነ ሴቶቹ በግጥም ይሳደባሉ፣

ጩሮደም ኧጭንን

ቅብዲም ነስጭንን

ዬመናጊ ጠብጠት

ንቶናም በጨበር

መልክኛ ንዥንን፣ይላሉ

በእርድ ቀን ቤተሰቦቹ ዘንድ ሳይደርስ በነበረበት ከተማ ለቀረ አባወራ፣እማወራዋ፣

በርበሬም ዎቀጥኩም፣ጥወም አክላለትኩም

አምብልም አረጥኩም ጉንስም አልባበጥኩም

አናቀርብሆም ዬጌ አቢ ቀበጥኩም እያሉ ይገጥማሉ፣በሌላ መልኩ የእማወራዋ አደራ ለአባወራው በዓል መዳረሻው፣

አክራሚ ይዎሉም ይሰላው መስቀለ

አደራ ዬሁንከ በሚዳ አትዋለ፣ትላለች፣

ትልቁ ዳመራ/ምጅር የሚቃጠልበት እለት በአብዛኛው ኃይማኖታዊ ይዘትን ይላበሳል ከቤተክርስቲያን መልስ ሁሉም በየደጁ በተናጠል/በጋራ ዳመራ ያቃጥላል፣ከዚያም ወደ ቤት በመግባት ታዋቂው የጉራጌ ክትፎ በየጣባው የረጋ ክትፎ ይቀርብና ይበላል፡

ሴት ልጃገረዶች ስንደዶ ለቀማ የሚሰማሩበት ቀን፣ከዚህ ቀን በፊት ማንም ሰው ስንደዶ ለቀማ አይሰማራም፣ተሰማርቶም የተገኘ እንደሆነ እንደ ነውር ይቆጠራል፣ለዓመቱ የመስቀል በዓል የስፌት ጌጦችን ለመስፋት የሚዘጋጁበት እለት ነው∶∶

በሶዶ ክስታኔ የመስቀል ማሳረጊያ ቀን የመጨረሻ አዳብና በዋለበት ማለት ነው፣ቀኑ መስቀል ከወጣ ከሰባት ቀን እስከ ጥቅምት 5 ቀን ድረስ ቋንጣ ክትፎ የሚበላበትና የሚጠናቀቅበት ይሆናል∶∶በማግስቱም የተገለገሉባቸው ዕቃዎች ታጥበው ይሰቀላሉ∶∶እንኳን አደረሳችሁ፣መልካም በዓል