የጥያ ድንጋይ
በምስራቅ ጉራጌ ዞን ደበቡብ ሶዶ ወረዳ ባህል፣ቱሪዝም ጽ/ቤት በባህልና ቱሪዝም መስኩ የማህበረሰቡ የማንነቱ መገለጫዎች፣እድሜ ጠገብ ቱባ ባህልና ወግ እንዲሁም ልምዶች በመዳሰስና በጥናትና ምርምር በማዳበር ከትውልድ ትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጉልህ ድርሻ እየሰራ ይገኛል:: ለዚህም ይረዳ ዘንድ የቅድመ ምልከታና ዳሰሳ ስራዎች በማድረግ ብሎም ሰነድ ከመሰነድ ባለፈም እውቅና እንዲያገኙ በማድረግና ቀጥሎም በማስተዋወቁ ረገድ ሚናውንም እየተወጣ ነው::
ይህንን መነሻ በማድረግም ደቡብ ሶዶ ወረዳ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎች የመስክ ምልከታና ልየታ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም መካከል በዳሙ 1 ቀበሌ በመገኘት ምልከታ ተድርጓል:: በዚሁ ቀበሌ ግቢ ልማት ቡድን የወንድ ልጅ ብልት የሚመስሉ ትክል ድንጋዮች እንዲሁም ልጅ የተሸከመች በጥበብና ስዕል የተዋበች ሴት ምስል ትክል ድንጋይም ለብቻው ይገኛል::
በአካባቢው ማህበረሰብ በእድሜ ገፋ ያሉ ሽማግሌዎች ስለነዚህ ትክል ድንጋዮች ታሪክ ያውቁ እንደሆን ጠየቅን፣መልሳቸው ተመሳሳይ ነበር:: በ15ኛው ክፍለ ዘመን የግራኝ መሀመድ ወደዚህ አካባቢ እንደመጣና የወንድ ብልት የሚመስሉት ትክል ድንጋዮችም በሰሙት ልክ ለፈረሶቹ ማሰሪያ ሲባል የቆሙ መሆኑን ይናገራሉ:: ነገር ግን ጉዳዩ እጅግ ስለሳበን ባየነው ልክ ለማነጻጸር ሞከርን፣ግን ደግሞ የተባልነው በከፊል ብናምንም ብዙ ጥያቄዎችን በውስጣችን ፈጠረብን ::በግልጽ የሚታዩት ትክል ድንጋዮች አብዛኛው የወንድ ብልት ቅርጽ ያለው ነው፣በዚያው የጥንት መቃብር አጠገብ ነው አብዛኛው ተተክሎ የሚገኘው ታዲያ ለምን የፈረስ ማሰሪያ?ለምንስ የወንድ ብልት ቅርጽ መቃብር አጠገብ?






ግን ደግሞ ስራ የሚፈልጉ ጉዳዮችም አሉ፣ትክል ድንጋዮቹ ተበታትነው እና በየግለሰው ቤት በርና አጥር ተደርገው የሚገኙ ሲሆን መሰብሰብና በርከት ብለው የሚገኙበት ስፍራ መከለል ቢቻል መልካም ነው::ጥሩነቱ ማህበረሰቡ እንዲጠናለትና እንዲታወቅለት በመፈለጉ የሚያደርግላቸው እንክብካቤም ይበልየሚያሰኝ በመሆኑ እድሉ ያገኘ ሁሉ ቢያየው እና የራሱን አስተዋጽኦ ቢያደርግ ብሎም የተጻፉ መጽሐፍት ካሉ ቢጠቁም መልካም ነው፡፡