የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት
አቶ ታጋይ አድማሱ
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ኃላፊ

ዓላማ

የማህበራዊ ጥበቃ ስራዓትን በመዘርጋት የአካል ጉዳተኞችንና አረጋዊያንን እንዲሁም ሌሎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ የህ/ሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የማህበራዊ ደህንነት አገልግሎቶችን በማስፋፋት የዜጎችን ተጠቃሚነት ማሳደግ፣ እንዲሁም ሙሉ ቁመና ያለው የተቋሙ የለውጥ ሰራዊት መገንባት፣ ምቹ የስራ ሁኔታዎችን በመፍጠር የኢንዱስትሪ ሰላምን ማስጠበቅ፣ የስራ ስምሪትና የስራ ገበያ መረጃ አገልግሎቶችን በማስፋፋት የሀገሪቱን የሰው ኃይል ፍላጎትና አቅርቦት የሚጣጣምበትን ሁኔታ ማመቻቸት ፡፡

ዝርዝር ዓላማ

  • የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ደንበኞችን መሠረት ያደረገ ግንዛቤ በመፍጠር በዝቅተኛ ወጪ ቀልጣፋና ከፍተኛ ጥራት ደረጃ ያለው አገልግሎት በመስጠት በድህነት ፤ በመገለልና በተጋላጭነት አደጋ ውስጥ የሚገኙ የህ/ሰብ ክፍሎች ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ ፡፡
  • ቀልጣፋና ዘመናዊ የሆነ የስራ ስምሪት አገልግሎት በመስጠት ስራና ሰራተኛን ለማገናኘትና በወረዳው የሚታዩ የስራ አጥነት ችግሮችን ለማቃለል ጥረት ማድረግ ፡፡
  • በስራ ምክንያት በሰራተኞች ደህንነትና ጤንነት ላይ እንደዚሁም በልማት ድርጅቶች ሀብትና ንብረት ላይ የሚደርሱ አደጋዎችንና ጉዳቶችን መቀነስና የስራ ሁኔታዎችንና የስራ አካባቢዎችን ማሻሻል ፡፡
  • ሠራተኞችና አሰሪዎች በነፃ በመደራጀትና አደረጃጀታቸውን በማጠናከር መብትና ጥቅማቸውን እንዲያስጠብቁና የልማት ተሳትፎአቸውን እንዲያጎለብቱ ማብቃት ፡፡
  • በአሰሪዎችና በሰራተኞች መካከል ጤናማ የስራ ግንኙነት እንዲመሰረትና እንዲጠናከር ለማብቃት በመካከላቸው የሚፈጠሩ የስራ ክርክሮችን በስራ ቦታ በሁለትዮሽና በሶስትሽ እንዲሁም በስራ ክርክር ፈቺ አካላት ወቅታዊና ፍትሃዊ እልባት እንዲያገኙ ለማድረግ ፡፡
  • አሰሪዎች፣ ሰራተኛና ባለድርሻ አካላት በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ፤ ህጎችና ሌሎች የህግ ማዕቀፎች ላይ የጠራ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ ፡፡

ራዕይ/Vision/

/፡-በ2022 የኢንዱስትሪ ሰላም የሰፈነበት የስራ ዕድሎች ተስፋፍተው ምርትና ምርታማነት ያደገበትና የማህበራዊ ችግሮች ተወግደው የህ/ሰቡ ማህበራዊ ደህንነት የጎለበተበት ወረዳ እውን ሆኖ ማየት

ተልዕኮ/Mission/

  • የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት በሚመለከት የወጡ ፖሊሲዎችን ፤ አዋጆችን ፣ደንቦች፣መመሪያዎችንና ኮንቬንሽኖችን ተግባራዊ ማድረግ
  • የህ/ሰቡ በተለይም የጎዳና ተዳዳሪዎች፣የአካል ጉዳተኞች፣ ፣በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ የህ/ሰብ ክፍሎችን ተደራሽ ያደረገ ድጋፍ ማድረግ ፡፡ የማህበራዊ ችግሮችን መከላከልና ማህበራዊ ደህንነት ልማትና የተሃድሶ አገልግሎቶችን ማስፋፋት
  • የሴክተሩ የማስፈጸም አቅም በመገንባት በወረዳችን ጤናማ የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት እንዲዳብር የሰራተኞች ደህንነትና ጤንነት እንዲጠበቅ የስራ አካባቢ እንዲጎለብት እና የስራ ስምሪት እንዲስፋፋ ማድረግ
  • የስራ ስምሪትና የስራ ገበያ መረጃ አገልግሎቶችን ማስፋፋት
  • ለልማትና ለዲሞክራሲ በተደራጀ ሁኔታ የህ/ሰብ ተሳትፎ ለማረጋገጥ ጠንክረን እንሰራለን
  • ለኢንዱስትሪ ሰላም መስፈን በቁርጠኝነት እንሰራለን
  • በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ የህ/ሰብ ክፍሎች ደህንነትን ማስጠበቅ መለያችን ነው ፡
  • የሙያ ብቃትና የስራ ጥራት መለያችን እናደርጋለን ፡፡
  • ለአረጋዊያን ድጋፍና እንክብካቤ እንሰጣለን ፡፡
  • ለአካል ጉዳተኞች እኩል እድልና ሙሉ ተሳትፎ ጠንክረን እንሰራለን
  • የጋራ መግባባት የተቀናጀ አሰራር የተሳታፊነት መርህን እንከተላለን ፡፡
  • ግልፀኝነት፤ተጠያቂነት፤ሰብአዊነት፣ሐቀኝነትና፣አለማዳላትን፤ከሙስና የጸዳ አሰራርን እንከተላለን
  • ቀልጣፋነትና ውጤታማነት ቶሎ ምላሽ የመስጠት የአሰራር ስርዓት እንከተላለን ፡፡
  • ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ሁሌም የስራችን አካል አድርገን እንሰራለን ፡፡
  1. ማህበራዊ ደህንነት ልማት ዳይሬክቶሬት የሚሰጡ ዝርዝር ግቦች
  • የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓት በመዘርጋት የዜጎችን ተጠቃሚነት ማሳደግ
  • የአካል ጉዳተኛ ተካታችነትና ተደራሽነት ማሳዳግ
  • የአረጋዊያን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ማሳደግ
  • የኢኮኖሚያዊና የማህበራዊ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነታቸው ማሳደግ
  • የቤተሰብ ተቋማዊ አደረጃጀት ማጠናከር
  1. በማህበራዊ ችግሮች መከላከል ዳይሬክቶሬት የሚሰጡ ዝርዝር ግቦች፡-
  • የተገልጋይ ዕመኔታን ማሳደግ
  • የፋይናንስ አጠቃቀምና ውጤታማነት ማሻሻል
  • የአረጋውያን ሁለንተናዊ ተካታችነት ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን ማሳደግ
  • የቤተሰብ ተቋማዊ አደረጃጀት ማጠናከር
  • የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ
  • የአካል ጉዳተኞች ተካታችነት ተሳታፊነት ፍትሃዊነትና ተጠቃሚነት ማሳደግ
  • የማህበረሰቡን ግንዛቤ ለመቀየር የንቅናቄ መድረክ መፍጠር
  • የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚነት ማሳደግ
  • የትብብርናና የቅንጅት ስራዎች ማስፋፋትና ማጠናከር
  • የመረጃ ስርዓት ማሻሻል
  1. ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት የሚሰጡ ዝርዝር ግቦች፡-
  • መልካም አስተዳደርን ማስፈን
  • የፋይናንስ አጠቃቀምና ውጤታማነት ማሻሻል
  • የፋይናንስ ምንጮችን ማሳደግ
  • የአሰሪዎችና የሰራተኞች በነጻ የመደራጀት ምጣኔ ማሳደግ
  • የማህበራዊ ምክክር የስራ ቦታ ትብብር ስርዓት ማጠናከርና ማስፋፋት
  • የስራ ሁኔታዎች ቁጥጥርና አገልግሎት ማስፋፋትና ማሳደግ
  • የህጻናት ጉልበት ብዝበዛን መከላከልና መቆጣጠር
  • የሙያ ደህንነትና ጤንነት አገልግሎት ማጠናከርና ማስፋፋት
  1. በስራ ስምሪት አገልግሎት ማስፋፊያ ዳይሬክቶሬት የሚሠጡ ዝርዝር ግቦች ፡-
  • የስራ ስምሪት አገልግሎት ማስፋፋት
  • ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከልና መቆጣጠር
  • የስራ ገበያ መረጃ መሰብሰብና ማጠናከር
  • የስራ ገበያ መረጃ በየደረጃው መተንተን
  • የስደት ተመላሾችን መረጃ መሰብሰብና መልሶ የማቋቋም ስራ መስራት
  • የመረጃ ስርዓት መዘርጋትና ማጠናከር
  • የስራ ገበያ መረጃ ስረዓትን ማጠናከርና ማሳደግ
  • የስራ ስምሪት አገልግሎት ማስፋፋት
  • ህገወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከል
  • የስራ ሁኔታዎችን ማሻሻልና የህግ ተፈጻሚነትን ማረጋገጥ
  • የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓትን መዘርጋት
  • ማህበራዊ ደህንነትን ማረጋገጥ
  • የስው ሃይል ማልማት
  • በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን በደቡብ ሶዶ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 የሚመለከታቸው የመንግስትም ሆነ የግል የልማት ድርጅቶችን አሰሪና ሰራተኛ የስራ ግንኙነታቸውን መሠረታዊ በሆነ መብቶችና ግዴታዎች ላይ ተመስርተው የኢንዱስትሪ ሰላምን በመፍጠር ሁለንተናዊ እድገትና ልማት በጋራ እንዲያመጡ ለማስቻል በወረዳው የሚገኙ የልማት ድርጅቶች ውስጥ ሰራተኛና አሰሪዎች የየራሳቸው ማህበር እንዲያቋቁሙ ማስቻል፤ በየወኪሎቻቸው አማካይነት ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ የህብረት ድርድር እንዲያደርጉ በማድረግ በመካከላቸው የሚነሱ የስራ ክርክሮች በአፋጣኝ መፍትሄ እንዲያገኙ ማስቻልና የሙያ ደህንነት ጤንነትና የስራ አካባቢ መቆጣጠር የሚቻልበት መንገድ ሁሉ ማመቻቸት፤የስራ ስምሪት የልማት ድርጅቶች የአገልግሎትና የስራ ገበያ መረጃ በማጠናከር በሀገራችን ያለው የሰው ኃይል ፍላጎት በተገቢው መልክ ለማሟላት መስራት ፡፡
  • በአስሪና ሰራተኛ ጉዳይ ዘርፍ በዋናነት የሀገሪቱን የሰው ሃብት ፍላጎትና አቅርቦት ለማጣጣም የሚያስችል የስራ ገበያ መረጃ ስርዓትን የመዘርጋትና የመተግበር፤የስራ ስምሪት አገልግሎት የማስፋፋት እንዲሁም የስራ ሁኔታዎችን(የሙያደህንነት ጤንነትና መሠረታዊ የሥራ ሁኔታዎችን )ቁጥጥር አገልግሎቶችን የማሳደግ አሠሪዎችና ሠራተኞች በማህበር በማደራጀት ግዴታቸውን ለመወጣትና መብታቸውን ለማስከበር የሚችሉበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር ፤ የማህበራዊ ምክክር አገልግሎት ስርዓትን በማስፋፋት የተጣለበትን ኃላፊነት ከግብ ለማድረስ የሚያስችሉ ስትራቴጂዎችን በማስቀመጥ ለኢንዱስትሪው ክፍለ ኢኮኖሚ ልማት መፍጠን የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት እየሰራ ይገኛል፡፡
  • እንዲሁም መንግስት ያወጣውን የማህበራዊ ደህንነት ልማት ፖሊሲ ፤ አዋጅ ፤ መመሪያና ደንቦችን በማስፈፀም መፍትሄ የሚሹ በማህበራዊ ኑሮ ችግር ተጠቂ የሆኑትን ቤተሰብ ፤ አረጋዊያን ፤ የአካልና የአእምሮ ጉዳተኞች ፤ ሴተኛ አዳሪዎች ፤ ጎዳና ተዳዳሪዎች ፤ ወላጆቻቸውን በተለያየ ምክንያት ያጡ ህፃናትና በአስከፊ ድህነት ለበሽታና ለልመና የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎች የመፍትሄ አቅጣጫ በመቀየስ ጥናት በማድረግ የተለያዩ ፕሮጀክቶች በመቅረፅ በየአካባቢው የሚገኙ የህ/ሰብ ክፍሎች በማወያየትና ግንዛቤ በማስጨበጥ ድጋፍ እንዲደረግላቸውና የስነ-ልቦና ጉዳት እንዳይደርስባቸው የማማከር በተለያዩ ስልጠናዎች በማሳተፍ ግንዛቤ እንዲጨብጡ በማድረግ ወደ ስራ እንዲገቡ ማስቻልና ተገልጋይና ሰው ተኮር አገልግሎቶችን በማስፋፋት የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓትን የዜጎች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚሰራ የመንግስት ተቋም ነው፡፡
  • የሴክተሩ ተገልጋዮች ስንመለከት፡-የአካል ጉዳተኞች፣ደጋፊና ጠዋሪ የሌላቸው አረጋዊያን፣ወላጅ አጥና ችግረኛ ህጻናት፣ለችግር ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ፣ለምኖ አዳሪዎች፣ ጎዳና ተዳዳሪዎች፣ሴተኛ አዳሪዎች፣የስጋ ደዌ ህሙማን፣የኤች አይቪ ህሙማን፣ወጣት ወንድና ሴት ጥፋተኞች፣ከስደት ተመላሾችና የስራ ፈላጊዎች ወ.ዘ.ተ
  • የሴክተሩ ባለድርሻ አካላቶች፡-የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣መንግሰታዊ ያልሆኑ ተቋማት/መያድ/ የመብት ማህበራት ማለትም ፡-የአረጋዊያን፣የአካል ጉዳተኛች፣የስጋደዌ ህሙማን እና የአሰሪዎችና የሰራተኞች ማህበራት፣የእድሮች ጥምረት ምክር ቤትና በየአካባቢው ያሉ ስራ አጦች፣ ስራ ፈላጊዎችና ኢንቨስተሮችን ያካትታል፡፡
  • በተቋማችን ደረጃ የተፈቀደ የሰው ሃይል ብዛት 25 ሲሆን የተሽፈነ ወ-3 ሴ-2 ድ-5 በሰው ሃይል ያልተሸፈነ መደብ ብዛት 20 ሲሆን አፈጻጸም በንፅፅር 20% ይሆናል፣
  • በአጠቃላይ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሴክተር በስሩ የሚያስፈጽማቸው 3 ፖሊሲዎች ሲኖሩት እነዚህም ፡-
  • ብሄራዊ ማህበራዊ ጥበቃ ፖሊሲ
  • ብሄራዊ የሙያ ደህንነት ጤንነት ፖሊሲ
  • ብሄራዊ የስራ ስምሪት ፖሊሲ ናቸው

የደቡብ ሶዶ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤትን ለማግኘት