የደቡብ ሶዶ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት
ወ/ሪት አዳምነሽ ደበላ
የደቡብ ሶዶ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ
ዓላማ
ዋና ዓላማ:

የሚዲያ ብዝሃነትና ተደራሽነት ማሳደግ

ዝርዝር ዓላማ

ዘመናዊና ውጤታማ የኮሚኒኬሸን አሰራር ስርአት በመዘርጋት ህብረተሰቡን የኢንፎርሜሽን ተጠቃሚ ማድረግ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ማህበረሰብን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ጉልህ አስተዋፆፅኦ ማበርከት ነው:: 

ራዕይ

በ2022 ዓም የወረዳችን ህዝቦች በላቀ መረጃ በልፅገው  የውሳኔ ሰጪነታቸው ተረጋግጦ     በመካከላቸው እኩልነት-አንድነትና ወንድማማቸነት ተጠናክሮ ማየት  ነው::

ተልእኮ

ሁሉ አቀፍና አዳዲስ  የኮሚኒኬሽን    መገናኛ ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም    ለህብረተሰቡ የማህበራዊና እኮኖሚያዊ ልማቶቸን  አንዲሁም  የኢንቨስትመንት መረጃዎቸን የሚሰጥ በጥናትና ምርመር የታገዘ አካታቸ የኮሚኒኬሽን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስቸል ምቹ አካባቢ መፍጠር ነው::

  • የላቀ አገልግሎትመስጠት
  • የፈጠራና የሀሳብ አመንጪነት
  • አክብሮትናአንድነት
  • የሀሳብ አሸናፊነት ማመን
  • ትብብርና የቡድን ስራ
  • የአመራር ብቃት ሀላፊነትን መውሰድ
  • የተገልጋይ ተጠቃሚነትና እርካታ ማሰደግ
  • የሃብት አጠቃቀም ውጤታማነትን ማሳደግ
  • የተቋሙን ጥራት ማሳደግ
  • የተቋሙን አገልግሎቶች ተደራሽነት ማሳደግ
  • የአገልግሎት ቅልጥፍናና ውጤማነት ማሳደግ
  • የመፈፀምና የማስፈፀምአቅም ማሳደግ
  • የመረጃ አደረጃጀት ስርዓትና አጠቃቀም ማሻሻል
  • የመንግስት ኮሚኒኬሽንና ሚዲያ ግንኙነት
  • የሚዲያ ሞኒተሪንግና ጥናት ምርምር
  • የመንግስት መረጃ ማዕከልና ዲጂታል ሚዲያ
የደቡብ ሶዶ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ መልዕክት

ተቋማችን መላውን የወረዳው ማህበረሰብ በፖለቲካ፤ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ ዘርፍ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከባለድርሻ ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን እየሰራ ሲሆን፤ በተጨማሪም መንግስትና ህዝብ ከማገናኘትና ከህዝብ ወደ መንግስት የሚመጡ  ሀሳቦችና ከመንግስት ወደ ህዝብ የሚወርዱ በወረዳው በልማትና መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን በህዝቡ ዘንድ የሚነሱ በአሉታዊ እና በአዎንታዊ አስተያየቶች በመቀበል በመለየት ለሚመለከተው ተቋም በማድረስ ችግሮች እንዲፈቱ ስራ ከመሰራቱም ባሻገር የወረዳው ባህልና እሴት ከማስተዋወቅ አንጻር ሰፊ ስራ ቢሰራም በቀጣይ አካባቢው ለኢንቨስትመንት ምቹ ከመሆኑ አንጻር በርካታ ኢንቨስትመንት ለመሳብና አካባቢውን ለማስተዋወቅ ስራ የምንሰራ ይሆናል፡፡

Phone Number

046-322-95-18