የደቡብ ሶዶ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት

ራዕይ

በወረዳችን የህግ የበላይነት ሰፍኖ የህዝቡ/የማህበረሰቡ ሰላምና ደህንነት የተረጋገጠበትና ከወንጀል ስጋት ነፃ የሆነ ህ/ሰብ መፍጠር የሚችል ተቋም ተፈጥሮ ማየት ነው፡፡

ተልዕኮ

የሀገሪቱንና የክልሉን ህገ መንግስትና ሌሎች ህጎችን በማስከበርና በማክበር ህብረተሰቡን በማሳተፍ ወንጀልን መከላከል ተፈፅሞ ሲገኝም በጥራትና በፍጥነት በማጣራት ለሚመለከተው የፍህ አካል ማቅረብ የአመራርና የአባላትን የማስፈፀም አቅም መገንባትና ከሌሎች የሰላምና ፀጥታ ኃይሎች ጋር ቅንጅት በመፍጠር የህ/ሰቡን ሰላምና ደህንነት አስተማማኝ ማድረግ ነው፡፡

እሴቶች

  • ለኢፌድሪ ህገ-መንግስት ታማኝ መሆን
  • ከራስ በላይ የሀገርንና የህዝብን ጥቅም ማስቀደም
  • የተስተካከለ ፖሊሳዊ ስብዕና በማንኛውም ፖሊሳዊ ተልዕኮ የላቀ ውጤት ማምጣት

በማ/ኢ/ሕ/ክ/መ/በም/ጉ/ዞ/የደ/ሶ/ወ/ፖ/ጽ/ቤት የተቋም ኃላፊ መልዕክት በተመለከተ

  • የደ/ሶ/ወ/ፖ/ጽ/ቤት እንደ ወረዳ የተቋቋመው 2011 ዓ/ም መጋቢት ወር ጀምሮ ሲሆን ተቋሙ ከተቋቋመ ጀምሮ ማስተባበሪያ በኃላም ተሸሽሎ በመጣ የፖሊስ ሪፎርም 02 ማስተባበሪያ ተጨምሮ በጠቅላላ 10 ማስተባበሪያዎችን በመጠቀም የፖሊስ ስራዎች እየተሰራ እና የፖሊስ ተግባራት ህዝብን ባሳተፈ መልኩ ወንጀል አስቀድሞ በመከላከል፤የትራፊክ አደጋ በመከላከል እና ወንጀልም ተፈፅሞ ሲገኝ ማህበረሰብንና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ እንዲሁም አጎራባች ወረዳዎችና ክልሎች በመንቀሳቀስ ምርመራ በማጣራት በህግ አግባብ በማስወሰን ማህበረሰቡ ከወንጀል ስጋት ነፃ በማድረግ ከልማት እንዳይደናቀፍ የማድረግ ስራ የፖሊስ ዋና ተግባር መሆኑ መልክት እናስተላልፋለን፡፡