የደቡብ ሶዶ ወረዳ አስተዳደር ፅ/ቤት

አቶ እንዳሻው መለሰ ይመሩ
የደቡብ ሶዶ ወረዳ አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊ
ዓላማ
ዋና ዓላማ
በህብረተሰቡ ቀጥተኛ ተሳትፎ መንግስታዊና መግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የጋራ ጥረት ማደረግበኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ እና በማህበራዊ ዘርፎች /መስኮች የተሻለና የላቀ ወረዳዊ እድገትና ብልጽግና ለማስመዝገብ ህ/ሰቡም የዴሞክራሲያዊ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ስርዓት ተጠቃሚ እንዲሆን ማስቻል እና የተቋሙ ሰብዓዊና ቁሳዊ ሀብት አቀናጅቶ ለመምራትና ውጤታማ የእቅድ አፈጻጸም በማስመዝገብና ህብረተሰቡን በየደረጃው ተጠቃሚ ማድረግ ማስቻል ነው፡፡
ዝርዝር ዓላማ
- በወረዳው ዴሞክራሲያዊ አሰራር እንዲሰፍን ማድረግ
- በወረዳው መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን ማደረግ
- የወረዳው ህዝብ በሃይማኖት፣በዘር በፖለቲካና በአጠቃላይ ማህበራዊ አመለካከቶች ተግባብቶና ተቻችሎ እንዲኖር መስራትበሁሉም የወረዳ ተቋማት ተግባራት በአግባቡ እንዲፈፅሙ ተገቢዉን ቴክኒካዊ ድጋፍ ማድረግ
ራዕይ
የወረዳው ማህበረሰብ በዘር፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካና በአጠቃላይ ማህበራዊ አመለካከቶች ተግባብቶና ተቻችሎ የሚኖርበት የመልካም አስተዳደር ስርዓት ተዘርግቶ ማየት፡፡በወረዳው ሰላምና ፀጥታ ተረጋግጦ እና መልካም አስተዳደር ሰፍኖ ዘላቂ ልማትን በማምጣት ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ሆኖ ማየት፡፡
- የስልጣን ባለቤት ህዝብ መሆኑን ማረጋገጥ
- የህግ የበላይነት ማክበር
- ፍትሃዊ አስተዳደር ማስፈን
- ከአድሎ የነፃ አገልግሎት መስጠት
- ስልጣንን በአግባቡ መጠቀም
- የስነ ምግባር መርሆዎችን ማክበር
በወረዳው ውስጥ ያሉ መሰረተ ልማቶች ማ/ሰቡ በአግባቡ እንዲጠቀሙ ማድረግ
- ፈጣንና ፍትሓዊ ውሳኔ በመስጠት የተገልጋይ እርካታ ማሳደግ
- የውሳኔዎችን ተፈፃሚነት በማረጋገጥ ማሳደግ
- መልካም አስተዳደርን በማስፈን የሕዝቡን ተጠቃሚነት ማሳደግ
- የበጀትና የፊዚካል ዕቅድ አፈፃፀም ውጤታማነት ማረጋገጥ
- የአገልግሎት አሠጣጥ ጥራትና ቅልጥፍና ማሳደግ
- በአሠራር ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ማሻሻል
- የዕቅድ አፈፃፀም ክትትልና ግምገማ ከ75% ወደ 100%ማሳደግ
የሴክተሩን የማስፈፀም አቅም ማሳደግ
ወረዳው በስሩ ላሉ 17 የገጠር ቀበሌዎች፤በ1 የከተማ እና በ1 ታዳጊ ማዘጋጃ ቤት መልካም አስተዳደርን በማስፈን ዘላቂና አስተማማኝ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦችን በፍጥነት ለማስመዝገብ ለህ/ሰቡ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት ሁለገብ አስተዳደራዊ ተግባሮችንና ስርዓቶች ተግባራዊ ማድረግ፡፡
የደቡብ ሶዶ ወረዳ አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊ
አቶ እንዳሻው መለሰ ይመሩ መልክት
የደቡብ ሶዶ አስተዳደር ፅ/ቤት መላው የወረዳው ህብረተሰብን ተጠቃሚ ለማድረግ ፈጣን፣ቀጣይና ፍትሀዊ የኢኮኖሚ ዕድገት በማስመዝገብና ልማትን በማፋጠን ድህነትን ደረጃ በደረጃ ለማስወገድ የሚያስችሉ አላማዎችን ያነገቡ የተለያዩ ስትራቴጂዎችን፣ የልማት መርሀ ግብሮችና ዕቅዶችን በማዘጋጀት ሲተገብር ቆይቷል፡፡ ፅ/ቤቱ የወረዳችንን ህዝቦች የልማት ፣የዴሞክራሲና የፍትህ ፍላጎት ለማሟላት የተቀመጡ ግቦችና ትግበራው ውጤታማ በሆነ ሁኔታ ሲፈፅም ቆይቷል፡፡ ስለሆነም ዕቅዱን ለመተግበር ሁሉም የሴክተራችን ሰራተኞችን በማቀናጀት ርብርብ አድርጓል፡፡ በዚህም መሰረት በሴክተሩ በኢኮኖሚ፤ በመሰረተ ልማት ፤በማህበራዊ ጉዳይ እና በመልካም አስተዳደር የህዝቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ውጤቶች የተመዘገቡበት እንደሆነ ለማየት ተችሏል፡፡ በመሆኑም በፅ/ቤቱ ስር ያሉ ስራ ሂደቶች ምንም እንኳን ባለሙያ ባይሟላም ባለው የሰው ሃይል የወረዳውን ህዝብ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመፍታትና በኢኮኖሚና በማህበራዊ መሰረተ ልማት ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ፡፡ ስለሆነም ወረዳው ለኢንቨስትመንት ምቹ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመስራትና ባለሃብቱን ተጠቃሚ ከማድረግ ባሻገር የወረዳውን ማህበረሰብ እና ወጣቱን የልማቱ ተጠቃሚ ለማድረግና የስራ እድል ለመፍጠር ሰፊ ስራ እየተሰራ ቢሆንም በቀጣይ የማህበረሰቡን የልማት ተጠቃሚነት ለመረጋገጥ ያስችል ዘንድ ሁሉም የጽ/ቤቱ አመራርና ባለሙያ በተሰማራበት የስራ መስክ የሚጠበቅብት ሃላፊነት በመወጣትና የልማቱ ተጠቃሚ ህዝብ መሆኑ ተረድተው በተደራጀ መልኩ ለማንቀሳቀስ በተደረገው ርብርብ ህዝቡ በልማቱ ላይ ባለቤትነቱን ያረጋገጠበትና ለተግባራዊነቱ በጋራ የተነሳሳበት ሁኔታ ታይቷል፡፡ በአጠቃላይ በደቡብ ሶዶ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት የሚሰጡ አገልግሎቶች ማህ/ሰብ በዘር፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካና በማህ/በራዊ አመለካከቶች ተግባብቶና ተቻችሎ የሚኖርበት የመልካም አስተዳደር ስርዓት በመዘርጋት ሁሉም የወረዳችን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ማድረግ፡፡





የተመረጡ የትኩረት መስኮች ማብራሪያ
ክትትል፣ድጋፍ፣ግምገማና ማማከር
ውጤት ፡– ዉጤታማ የዕቅድ አፈጻጸምና ውሳኔ
ሴክተሩ ከሀገራዊና ክልላዊ ፖሊሲዎች፣ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች አንፃር ተቃኝተው የተዘጋጁ የሴክተሮችን ዕቅድ ከተጣሉ ሀገራዊና ክልላዊ ግቦች አኳያ በመገምገም፣አፈፃፀማቸውን በመከታተል፣በመደገፍና ግብረ-መልስ በመስጠት ዉጤታማ የዕቅድ አፈጻጸም እንዲኖር በማስቻል እና ውሳኔ የሚሹ ጉዳዮችን አጣርቶ የማቅረብና የማማከር ሥራዎችን በመስራት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ስለሚጠበቅበት
“ክትትል፣ድጋፍ፤ግምገማና ማማከር አንዱ የትኩረት መስክ ሆኖ ሲመረጥ
የሴክተሮች ዕቅድ ዝግጅት ከፖሊሲዎች፣ ከፕሮግራሞችና ከተጣሉ ግቦች አንፃር ተቃኝተው መዘጋጀታቸውን የመገምገምና የማረጋገጥ፣
- ውሳኔ በሚሹ ጉዳዮች ላይ የማማከር
- የሴክተሮች ዕቅድ ከተጣሉ ግቦች አንፃር እየተፈፀሙ መሆናቸውን የመከታተል፣ የመደገፍ፣ የመገምገምና ግብረ-መልስ የመስጠት፣
- የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቶችን የመገምገም፣ የማጠናቀርና ለሚመለከተው አካል የማቅረብ፣
- በክትትል፣ድጋፍና ግምገማ ሂደት የተለዩ የአሰራር ክፍተቶች እንዲሻሻሉ አስተያየት የማቅረብ ስራ የሚሰራበት ስለሆነ የትኩረት መስክ ሆኖ ሊመረጥ ተችሏል፡፡
ውጤት፡– የጎለበተ የግልጸኝነትና የተጠያቂነት አሰራር
ቀጣይነት ያለው ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ልማት በማስመዝገብ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ መንግስት የመልካም አስተዳደር ፕሮግራሞችና ፓኬጆችን ቀርፆ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህ አንፃር ሴክተሩ በቅሬታ መንስኤዎችና መፍትሄዎች ላይ የጥናት ሥራ በመስራት፣የሪፎርም ማሻሻያ ፕሮግራሞች በተሳለጠ መንገድ እንዲተገበሩ በማድረግ፣አስተዳደራዊ ቅሬታዎችንና አቤቱታዎችን በመፍታት፣የወረዳው ሰላምና ፀጥታ እንዲረጋገጥ በማስተባበር እንዲሁም በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች የፈፃሚውና የህብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲያድግ በማድረግ የጎለበተ የግልጸኝነትና የተጠያቂነት አሰራር እንዲኖር ይህ
“መልካም አስተዳደር” የትኩረት መስክ ሆኖ የተመረጠ ሲሆን ፡-
- የቅሬታና አቤቱታ መንስኤዎችንና መፍትሔዎቻቸውን በጥናት የመለየት፤
- አስተዳደራዊ ቅሬታዎችንና አቤቱታዎችን የመፍታት፣
- የሪፎርም ፕሮግራሞችና ፓኬጆች በተሳለጠ መንገድ እንዲተገበሩ የማድረግ፣
- በመልካም አስተዳደር ዙሪያ የህብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲጎለብት የማስተባበር፣
- የህብረተቡ ሰላምና ፀጥታ እንዲረጋገጥ የማስተባበርና ከአጎራባች ወረዳዎችና ቀበሌዎች ጋር በጋራ መስራት በማስፈለጉ አንዱ የትኩረት መስክ ሆኖ ተመርጧል ፡፡