የኢንቨስትመንት አማራጮች
የደቡብ ሶዶ ወረዳ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጉራጌ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች አንዱ ሲሆን ወረዳውን ከሰሜን ወደ ደቡብ ከ8’9’00°N-8’19’00°S ላቲቲዩድና ከምዕራብ ወደ ምስራቅ 38’20’00°E-38’36’00°W ሎንግቲዩድ ላይ የሚገኝ ሲሆን የወረዳው ዋና ከተማ ኬላ ከመዲናችን አዲስ አበባ 113 ኪ/ሜ ፣ከክልሉ ዋና ከተማ ሆሳዕና 125 ኪ/ሜ እንዲሁም ከዞን ዋና ከተማ ቡታጅራ በ25 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ በስተ-ደቡብ ከመስቃን ወረዳ ፤በምስራቅ ሶዶ ወረዳ እና በተቀሩት አቅጣጫዎች ከኦሮሚያ ክልል ጋር ይዋሰናል፡፡ በወረዳው ውስጥ በዋናነት የጉራጌ ማ/ሰብ የሚኖር ሲሆን በተጨማሪ ሌሎችም የሀገሪቱ ብሔር ብሔረሰቦች ይኖራሉ፡፡በቅርቡ በአዲስ በተለካው መሠረት የመሬት ልኬቱ በጥቅሉ 32,807 ሄ/ር የቆዳ ስፋት ሲኖረው የመሬት አቀማመጡም 50.03% ሜዳማ፣11.3% ኮረብታማ፣15.07% ወጣገባ እና 23.6% ተራራማ ሲሆን ወረዳው በ17 የገጠር ቀበሌዎች እና በ2 ከተሞች በጥቅሉ በ19 የአስተዳደር እርከኖች የተከፋፈለ ነው ፡፡ ደጋማው አካባቢ በብዛት በእንሰት አብቃይነቱ ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም ከአዝዕርት አይነቶች ገብስ ፤ ስንዴ ፤ ጤፍ ፤ከእገዳ ሰብሎች በቆሎና ማሽላ ፤ ከጥራጥሬ ሰብሎች አተር፣ባቄላ፤ሽንብራና የመሳሰሉት በወረዳው በብዛት የሚመረቱ የሰብል አይነቶች ናቸው፡፡

አጠቃላይ የወረዳው የህዝብ ብዛት 53,565 ወንድ 24,651 ሴት 28,914 ሲሆን 91.6%የሚሆነው በገጠሩ የወረዳው ክፍል ሲሆን 8.4% የሚሆነው በከተማ ይኖራል፡፡የደቡብ ሶዶ ወረዳ በጉራጌ ዞን ከሚገኙ ለውጡን ተከትለው ከተፈጠሩ መዋቅሮች አንዱ ሲሆኑ በወረዳው ለኢንቨስትመንት ምቹ ከሚባሉት ሃብቶች አንዱ የተፈጥሮ የመሬት አቀማመጠው ወሳኝ በመሆኑ በግብርና ዘርፍ ባለ-ሃብቶች በሚፈልጉት ልክ ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ያለበት እና ምርትና ምርታማነቱን ከዞን እስከ ክልል ባለው መዋቅር የሚታወቅ ቀጠና ነው፡፡ በመሆኑም በወረዳው
በማዕድን ፣በማኑፋክተሪን፣ በአገልግሎት፣በንግድ እና በሌሎች ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለ-ሃብቶች አጠቃላይ በወረዳው ካለው የተፈጥሮ ሃብት የሚስማማ የመሰረተ ልማት እና ምቹ የአየር ንብረት ያለው በመሆኑ የወረዳው መቀመጫ ከአዲስ አበባ ያለው ርቀት በ113 ኪ/ሜ መሆኑ ደግሞ በአካባቢ ያለው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ይበልጥ እንዲፈጥንና ብዙ ባለሃብቶች መጥተው እንዲያለሙ እድል የሚጥር ነው፡፡ ስለሆነም ወረዳው በኢንቨስትመንት ለሚሰማሩ ባለ ሃብቶች ከተፈጥሮ የአየር ንብረት ምቹነት ባሻገር የማህረሰቡ የልማት ወዳድነት እና እንግዳ ተቀባይነቱ በግብርናና በሌሎች ዘርፍ ተስማርተው ለሚሰሩ ኢንቨስተሮች በሚፈልጉት መልኩ ውጤት ማስመዝገብ ይችላሉ፡፡
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ካለው አጠቃላይ እምቅ አቅም አንፃር ባለሀብቶችና ድርጅቶች በሎጅ፣በማዕድን፣በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በአዝዕርት ምርቶች ላይ በልዩ ትኩረት ዕቅድ አቅደው ቢንቀሳቀሱም የበለጠ ትርፋማ የሚሆኑባቸው ዘርፎች፡-
በሎጅ አገልግሎት
ኢንቨስት ለሚደረግ የሚፈልጉ ባለሀብቶች የደቡብ ሶዶ ወረዳ መዲና የሆነችው የኬላ ከተማን ምቹነት ማየት በቂ ነው፡፡ይህም ሲባል ከተማዋ ካለው የመንገድ ኮሪደሮች አኳያ ባለ አራት በር ማለትም ከአ/አበባ ወላይታ ሶዶ እና ከቱሉ-ቦሎ መቂ ያለው የመንገድ አማራጭ ለቱሪዝም ዘርፍ ወሳኝ ሚና ያለው እንደመሆኑ መጠን በዚህ መሐል በሎጅ አገልግሎት ዘርፍ ፕሮጀክት ፕሮፖዛል ቀርፆ የሚሰራ ባለሀብት በዘርፍ ማግኘት ያለበት ትርፍ አሁንም አካባቢው ላይ ያለው እንቅስቃሴ ማየት በቂ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በመሆኑም በወረዳው ያለው ተስማሚ የአየር ንብረት ማለትም ከደጋማ እስከ ቆላማ የአየር ንብርት ያላት እንደመሆኑ መጠን ወደዚህ አካባቢ ዘና ለማለት የሚመጡ የሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ ዜጎች ሚፈልጉትን አይነት በልተው ጠጥተው እና ተዝናንተው በሰላም ሰገነት በሆነችው አካባቢ ሰላማዊ እረፍት አድርገው መመለስ ይችላሉ፡፡


በማዕድን ዘርፍ በተለይ የሲልካ ሳንድ ክምችት በተመለከተ
ቀደም ሲል ቆላ ኑረና አካባቢ የሚገኘው ሳይት በኒው ኢራ ማይኒግ የተጀመረ ፕሮጀክት ያለ ቢሆንም በዚህ ዘርፍ እስካሁን በዚህ ግባ የሚባል ስራ መስራት ያልተቻለ ሲሆን ይህ ፕሮጀክት በሙሉ አቅሙ ወደ ተግባር ሲገባ በአካባቢው የሚገኙ ዕድሎች ሰፊ ሰፊ የስራ ዕድል እና ከፍተኛ የኢንዱስትሪ ተቋማት መበራከት ዕድል የሚፈጥር ተስፋ ሰጪ የማዕድን ክምችት ያለበት አካባቢ እንደመሆኑ መጠን ማዕድኑ ለብዙ አይነት የመስታወት ውጤቶች ለጥሬ እቃነት የሚጠቅም ምርት በስፋት ማምረት የሚቻልበት አካባቢ ነው፡፡


በአትክልትና ፍራፍሬ ግብርና ስራ የሚሰማራ ባለሀብት
- ፡- በአካባቢው ያለው ተስማሚ የአየር ንብረት የአፈር አይነት በዚህ ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው ሲሆን እስካሁን በወረዳችን በዚህ ዘርፍ ውጤታማ ስራ እየሰራ ያለበት ኮርነር ስቶን ኃ/የተ/የግ/ማህበር እየሰራ ያለው የአትክልት ስራ ለአብነት ማየት ይቻላል፡፤ በመሆኑም በዚህ ግብርና ስራ ለመሰማራት የሚፈልጉ ድርጅቶችና የግል ባለሀብቶች ለዚህ ተግባር ሚሆን ተስማሚ የአፈር ዓይነት እና የአየር ንብረት ወሳኝ እንደመሆኑ መጠን በዚህ አካባቢ ዓመታዊ የዝናብ መጠን 820-880 ሚሜ ከ26-27 ዲ/ሴ ዓመታዊ የሙቀት መጠን እና የቦታው ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ 1840-3600 ሜትር የተመዘገበ መረጃ እንዳለ የሚያሳይ ሲሆን እዚህ አካባቢ የሚገኘው የአፈር አይነት 60% ቡናማ፣22% ጥቁር12%ቀይ እና 6%ግራጫ ነው፡፡ የአየር ሁኔታ ስንመለከት 58%ወ/ደጋማእና 42%ደጋማ የአየር ንብረት ያለው መሆኑን በዚህ ዘርፍ ለሚሰማሩ ፕሮጀክቶች እጅግ ተፈላጊ እና ምቹ ሁኔታዎች እንዳሉ ያሣያል፡፡













የአዝዕርት ምርቶች በተመለከተ
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ለዚህ ግብርና ስራ የሚሆኑ ሰፊ ምቹ ሁኔታዎች ያሉ ሲሆን ከዚህም አኳያ ወረዳው አሁን ካለንበት ክልል ማለትም ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ ከሚባሉ ቀጠናዎች በአዝዕርት ምርት በተለይ በጤፍ በስንዴ እና በቆሎ ምርት ታዋቂ ነው፡፡ ይህም ሲባል ቀተናው እንዚህን የግብርና ሰብሎች ለማምረት ከላይ የተጠቀሱት የአየር ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆነው በተጨማሪም እነዙህን ተግባር በመስኖ ማልማት የሚቻልበት የውሃ አማራጮች ያሉበት አካባቢ




ሲሆን ለአብነት አመቱን ሙሉ የሚፈሱ ወንዞች መቂ እና ለቡ የሚባሉ በአካባቢው ታዋቂ ወንዞችና በወረዳችን ሰፊ የአርሶ አደሮች ህይወት የቀየሩ የውሃ አማራጮች ናቸው፡፡ በመሆኑም ወደዚህ አካባቢ መጥቶ በአዝዕርት ምርት መስራት የሚፈልጉ ድርጅቶችና ባለሀብቶች አሁን ካለው አጠቃላይ የሰብል ምርት ትመና አንፃር በጣም ውጤታማ በሆነ መልኩ ሊሰሩበት የሚችሉ ከ50%በላይ ሜዳማና ተስማሚ የአፈር ለምነት ያለበት አካባቢ ነው፡፡