የደቡብ ሶዶ ወረዳ ወጣቶች እና ስፖርት ጽ/ቤት

አቶ ሰለሞን ፈቀደ ሲማ
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ወጣቶች እና ስፖርት ጽ/ቤት ሀላፊ
ዋና አላማ
የወጣቶችን ሁለንተናዊ ብቃት በመገንባት ብቁና ተወዳደደሪ ዜጋ ሆነው፤ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ተሳታፊነታቸውንና ተጠቃሚነታቸውን በማረጋገጥና የስፖርት ዘርፍ ልማትን በማስፋፋት ንቁ ህብረተሰብንና ውጤታማ ዜጎችን በማፍራት በሀገር አቀፍ መድረኮች ተፎካካሪ በወረዳችን በመፍጠር ለሀገር ብልጽግና ያለውን ሚና ማሳደግ
ዝርዝር ዓላማ
- የወጣቶችን ሁለንተናዊ ብቃት በመገንባት ብቁና ተወዳደደሪ ዜጋ ማፍራት፤
- የወጣቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ በሁሉም ዘርፎች የወጣቶች ጉዳይን ማካተትና ተቋማዊነት ማሳደግ
- የወጣቶችን ስብዕናና መልካም አመለካከት ማጎልበት
- የወጣቶች ጉዳይን በተመለከተ የግንዛቤ፣ የንቅናቄ ሥራዎችንና የውይይት መድረኮችን ማጠናከር፣
- የመንግስታዊ እና ህዝባዊ ተቋማትና አደረጃጀቶች በማጠናከር የዘርፉን የመፈፀም፣ የማስፈፀም እና የፋይናንስ አቅም ማጎልበት ፣
- የስፖርት መሰረተ ልማቶች እና ቁሳቁሶች እንዲስፋፉ፣ እንዲጠበቁ እና አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ማድረግ፣
- ተደራሽ እና ፍትሀዊ የሆነ የማህበረሰብ አቀፍ ስፖርትን በማስፋፋት፣ ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ንቁ፣ጤናማና አምራች ዜጎችን መፍጠር፣
- የባለሙያዎችን አቅም በማጎልበት በአህጉርና በአለም አቀፍ የውድድር መድረኮች ውጤት የሚያስመዘግቡ አትሌቶችን በማፍራት፣ ስፖርት ለሁለንተናዊ ሀገራዊ ዕድገት ያለውን ሚና ማሳደግ



ራዕይ
“በ2023 ወጣቶች ኢኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊና፣ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ተረጋግጦ ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ጤናማ ህብረተሰብ፣ መልካም ስብዕና ያለው ወጣት፣ ተወዳዳሪና ውጤታማ የሆኑ ስፖርተኞች ተፈጥረው ማየት፡፡
ተልዕኮ
የወረዳችን ወጣቶች ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ምቹ ሁኔታ በመፍጠርና ህዝባዊ መሰረት ያለውን ስፖርት በማስፋፋት የዜጎችን አካላዊና አእምሮአዊ ብቃት በመገንባት በወረዳችንና የሀገርን ብልፅግና ማረጋገጥ፣
- አሳታፊነትና ፍትኃዊነት፣
- ግልጽነትና ተጠያቂነት፣
- ፈጠራን ማበረታታት፣
- ቅልጥፍናና ውጤታማነት፣
- የአገልግሎት ጥራት፣
- ለለውጥ ዝግጁነት፣
- በቡድን መስራት፣
- ህዝባዊነት፣
- የሃብት አሰባሰብና የበጀት አጠቃቀም ውጤታማነትን ማሳደግ
- የወጣቶችንና የህብረተሰቡን ግንዛቤና ተሳትፎ ማሳደግ
- የወጣቶችና የወጣት አደረጃጀቶችን አቅም ማሳደግ
- የወጣቶችን የፖለቲካ ተሳትፎና የውሳኔ ሰጭነት ሚና ማሳደግ
- የወጣቶችን ጉዳይ ተቋማዊነት ማሳደግ
- የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናንና ጥራትን ማሳደግ
- የሴክተሩን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ማሳደግ
- የሀብት አሰባሰብና አጠቃቀም ውጤታማነት ማሳደግ
- የስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራዎች መገንባትና በ 5 ቀበሌወዋች ማስፋፋትና ፖል የመትከል ስራ መስራት መቻል
- የስፖርት አደረጃጀቶችን ማጠናከር አቅማቸውን ማሳደግ
- የስፖርት ተሳትፎ ውጤታማ ነት ማሳደግ
- የአማተር ባለሙያዎች አቅም ማሳደግና የፕሮጀክተሮች ጣቢያዎች ማስፋፋት
- የባለብዙ ዘርፍ ሥራዎችን በተመለከተ
- የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልን
የትኩረት መስክ
- የተገልጋይ እርካታና አመኔታ ማሳደግ
- የወጣቶችን ተጠቃሚነት ማሳደግ
- ያደገ የወጣቶች ማህበራዊ ተጠቃሚነት
- የቀነሰ የወጣቶች የማህበራዊ ችግሮች ተጋላጭነት
የሴክተሩ አጠቃላይ ገጽታ
በምስራቅ ጉራጌ ዞን የደቡብ ሶዶ ወረዳ አጠቃላ 37 የሰው ሀይል የተፈቀደ ሲሆን በአሁኑ ሰአት 2 የወል እና 5 ዋና ስራ ሂደቶች በአጠቃላይ በ-5 የሰው ሀይል ተግባራትን እየፈጸመ ይገኛል፡፡