የደቡብ ሶዶ ወረዳ
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ
አቶ መስፍን አድማሱ
የደቡብ ሶዶ ወረዳ በምስራቅ ጉራጌ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች አንዱ ሲሆን ወረዳውን ከሰሜን ወደ ደቡብ ከ8'9'00°N-8'19'00°S ላቲቲዩድና ከምዕራብ ወደ ምስራቅ 38'20'00°E-38'36'00°W ሎንግቲዩድ ላይ የሚገኝ ሲሆን የወረዳው ዋና ከተማ ኬላ ከመዲናችን አዲስ አበባ 113 ኪ/ሜ ፣ከክልሉ ዋና ከተማ ሆሳዕና 125 ኪ/ሜ እንዲሁም ከዞን ዋና ከተማ ቡታጅራ በ25 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
በስተ ሰሜን ሶዶ ወረዳ በስተ-ደቡብ ከመስቃን ወረዳ ፤በስተ ምስራቅ ሶዶ ወረዳ በስተ ምዕራብ ሰዴን ሶዶ (ኦሮሚያ ክልል) አቅጣጫዎች ይዋሰናል፡፡ በወረዳው ውስጥ በዋናነት የጉራጌ ማ/ሰብ የሚኖር ሲሆን በተጨማሪ ሌሎችም የሀገሪቱ ብሔር ብሔረሰቦች ይኖራሉ፡፡በቅርቡ በአዲስ በተለካው መሠረት የመሬት ልኬቱ በጥቅሉ 32,807 ሄ/ር የቆዳ ስፋት ሲኖረው የመሬት አቀማመጡም 50.03% ሜዳማ፣11.3% ኮረብታማ፣15.07% ወጣገባ እና 23.6% ተራራማ ሲሆን ፣የአፈር አይነቱ ፤ 60% ቡናማ፤12%ቀይ እና 6% ግራጫ ነው፡፡ የአየር ሁኔታው ስንመለከት 58% ወ/ደጋማና 42% ደጋማ የአየር ንብረት አለው፡፡
ወረዳው በ17 የገጠር ቀበሌዎች እና በ2 ከተሞች በጥቅሉ በ19 የአስተዳደር እርከኖች የተከፋፈለ ነው ፡፡ ደጋማው አካባቢ በብዛት በእንሰት አብቃይነቱ ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም ከአዝዕርት አይነቶች ገብስ ፤ ስንዴ ፤ ጤፍ ፤ከአገዳ ሰብሎች በቆሎና ማሽላ ፤ ከጥራጥሬ ሰብሎች አተር፣ባቄላ፤ሽንብራና የመሳሰሉት በወረዳው በብዛት የሚመረቱ የሰብል አይነቶች ናቸው፡፡
አጠቃላይ የወረዳው የህዝብ ብዛት 57,749 ወንድ 27,968 ሴት 29,781 ሲሆን 91.6%የሚሆነው በገጠሩ የወረዳው ክፍል ሲሆን 8.4% የሚሆነው በከተማ ይኖራል፡፡የህዝብ ስርጭት ከአየር ንብረት አንፃር ሲታይ 58% የሚሆነው የወረዳው ህዝብ በወ/ደጋማው የአየር ንብረት አካባቢ ሲሆር 42% የሚሆነው ህዝብ ደግሞ በደጋማው የአየር ንብረት ክፍል ውስጥ ይኖራል፡፡አመታዊ የዝናብ መጠን 820-880 ሚሜ እንዲሁም አመታዊ የሙቀት መጠን ደግሞ 26027 ዲ/ሴ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ፡፤ ከፍታው ከባህር ጠለል በላይ 1840-3600 ሜትር ነው፡፡
የደቡብ ሶዶ ወረዳ በምስራቅ ጉራጌ ዞን ከሚገኙ ለውጡን ተከትለው ከተፈጠሩ መዋቅሮች አንዱ ሲሆኑ በወረዳው ለኢንቨስትመንት ምቹ ከሚባሉት ሃብቶች አንዱ የተፈጥሮ የመሬት አቀማመጠው ወሳኝ በመሆኑ በግብርና ዘርፍ ባለ-ሃብቶች በሚፈልጉት ልክ ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ያለበት እና ምርትና ምርታማነቱን ከዞን እስከ ክልል ባለው መዋቅር የሚታወቅ ቀጠና ነው፡፡ በመሆኑም በወረዳው በማዕድን ፣በማኒፋክቸሪን፣ በአገልግሎት፣በንግድ እና በሌሎች ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለ-ሃብቶች አጠቃላይ በወረዳው ካለው የተፈጥሮ ሃብት የሚስማማ የመሰረተ ልማት እና ምቹ የአየር ንብረት ያለው በመሆኑ የወረዳው መቀመጫ ከአዲስ አበባ ያለው ርቀት በ113 ኪ/ሜ መሆኑ ደግሞ በአካባቢ ያለው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ይበልጥ እንዲፈጥንና ብዙ ባለሃብቶች መጥተው እንዲያለሙ እድል የሚጥር ነው፡፡ ስለሆነም ወረዳው በኢንቨስትመንት ለሚሰማሩ ባለ ሃብቶች ከተፈጥሮ የአየር ንብረት ምቹነት ባሻገር የማህረሰቡ የልማት ወዳድነት እና እንግዳ ተቀባይነቱ በግብርናና በሌሎች ዘርፍ ተስማርተው ለሚሰሩ ኢንቨስተሮች በሚፈልጉት መልኩ ውጤት ማስመዝገብ ይችላሉ፡፡





Views This Year : 50