የደቡብ ሶዶ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት

አቶ ጋሻው ተረፈ ካሳ
አላማ
የሕዝብ ተአማኒነት ያለው ፣ በተሟላ ተቋማዊና ሙያዊ ነፃነት የሚያገለግል እንዲሁም ለሙያዊ ፣ ተቋማዊና ሕዝባዊ ተጠያቂነት የሚገዛ ፣ በግልጽነትና በአሳታፊነት የሚሰራ ተቋም እንዲሆን ነው፡፡
- የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የንቃተ ሕግ ግንዛቤ አግኝተው መብትና ግዴታቸውን አውቀው የራሳቸውንና የሌሎችን መብት በማክበርና በማስከበር ሰላምና መልካም አስተዳደርን እንዲሰፍን በማድረግ የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ለማስቻል ፤
- ሕብረተሰቡ የወንጀልን አስከፊነትና መጥፎ ገጽታ ለማስገንዘብና ወደ ልማት እንዲገባ ለማድረግ ፤
- በዘርፉ ላይ ምርጥ ተሞክሮዎችን ቀምሮ መተግበር ልምዶችን ማጋራት፤
- በስነ ምግባር በሙስናና በብልሹ አሰራር ዙሪያ የሚቀርቡ አስተያየቶች ፣ ጥቆማዎችና ቅሬታዎችን በአግባቡ በማጣራት ፈጣን ምላሽ መስጠት፤
- የተመዘበረ የመንግስት ሃብት እና ንብረት እንዲሁም የከተማና ገጠር የወል መሬት ወደ መንግስት የመሬት ባንክ እንዲገቡ ከሌሎች የስነ ምግባር አዉታሮች በመቀናጀት መስራት፣
- የሴቶች ፤ ሕጻናት ፤ አረጋዊያን ፤ አካል ጉዳተኞች እና በኤች አይ ቪ ኤድስ ተተቂ ተገቢውን የሕግ ድጋፍ ማድረግ፤
- የወንጀል ምርመራን በበላይነት በመምራት የተጠርጣሪዎችን መብት ባከበረ ሁኔታ ምርመራዎች እንዲካሄዱ ማድረግ
- የሕብረተሰቡ ሰላምና ደህንነት ከማረጋገጥ አንጻር የወንጀል ድርጊት በፈጸሙ ግለሰቦች ላይ ክስ በመመስረትና ተገቢውን የችሎት ክርክርና ክትትል በማድረግ የወንጀል ድርጊት ፈጻሚዎችን የሚያስተምርና ሌሎች መሰል ወንጀል ፈጻሚዎችን የሚያስጠነቅቅ የቅጣት ውሳኔ እንዲወሰን ማድረግ፣
- መንግስት ከሳሽ ወይም ተከሳሽ በሆነባቸው የፍትሐ-ብሔር ጉዳዮች የመርታት ምጣኔን ማሳደግና ልዩ ትኩረት መሥጠት፣
- ከሕገ-ወጥ የሠዎች ዝውውር ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ የወንጀልና የፍትሐ-ብሔር መዛግብት ለይ ውጤታማ ማድረግ፤
- የሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል የተጋላጭነት ሁኔታ ከቦታ ፣ ከተጎጂዎችና ከአዘዋዋሪዎች አንጻር ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ መሥራት፣
- ጠበቆችና የሕግ ጉዳይ ጸሐፊዎች በሚሰጡት የጥብቅና አገልግሎት ላይ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ፣
- የታክስ እና የሸማቾች ጥበቃ ሕጎች መዛግብትን ተንቀሳቅሶ መሥራት መቻል፤
- ከታክስ ኦዲት ጉድለት ላይ በተፈጸሙ ወንጀል ጉዳዮችን ማጠናከርና በፍትሐ-ብሔር ዕዳውን የማስመለስ ሥራን መሥራት
- በፌደራል ወይም በክልል ደረጃ የተመዘገቡና ፍቃድ ባወጡ ነጋዴዎች የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ክትትል ማድረግ፤
ራዕይ
- በ2022 ዓ/ም ዜጎች የተፋጠነና ጥራት ያለው ፍትሕ የሚያገኙበት ተቋም ሆኖ ማየት!
ተልዕኮ
- በወረዳችን ፍትሕ እንዲሰፍን ፣ የመንግስትና የሕዝብ ጥቅሞች እንዲጠበቁ ፣ በሕገ መንግስቱ ላይ የተደነገጉ ሰብዓዊና ዲሞክራሳዊ መብቶች እንዲከበሩ ለማስቻል የሕብረተሰቡን ንቃተ-ሕግ በማሳደግ ፣ ወንጀል ፈፃሚዎች ለሕግ እንዲቀርቡና ለፈፀሙት ጥፋት በሕግ እንዲጠየቁ ለማድረግ እንዲሁም የሕብረተሰቡና የተቋሙን የመደራጀት መብት በማረጋገጥ የመሪነት ሚና በመጫወት የሕግ የበላይነትንና መልካም አስተዳደርን የማስፈን ከፍተኛ ኃላፊነት የተጣለብን በመሆኑ ወረዳው የድርሻውን ተልኮ ጽ/ቤታችን ይፈጽማል!!!
- ለሕግ የበላይነት ቆመናል፣
- ፍትሐዊነት መታወቂያችን ነው፣
- ግልፀኝነትና ተጠያቂነት መለያችን ነው፣
- እኩልነትና የአገልጋይነት ስሜት፤
- በአጋርነት እንሰራለን፣
- ውጤታማነትና ተገልጋይ ተኮር መሆን፤
- ሚዛናዊነት መገለጫችን ነው፣
- የተቀናጀ የፍትሕ አገልግሎት፤
- ውጤት ያሸልማል፣
- ለለውጥ ዝግጁነት፤
- ቀልጣፋነትና ፍትሐዊነት፤
- ተደራሽነትና ወጪ ቆጣቢነት፤
ታማኝነት ፤ ግልጽኝነትና ተጠያቂነት፤
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ፍትሕ ጽ/ቤት የሥራ ሂደቶች ዝርዝር ተግባራት
- ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዓላማ አስፈጻሚና ድጋፍ ሰጪ የሰው ኃይል ክፍተት መለየት፣
- ውጤትን መሰረት ያደረገ 100% የትምህርት ዕድል ማመቻቸት፤
- በመመሪያ መሰረት ፈጻሚው 100% ጥቅማጥቅም እንዲያገኝ ማድረግ፣
- የሰው ኃይል ማሟላት፣ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግና ወደ ሥራ ማሰማራት፣
- የሰራተኛ እርካታን በማሳደግ ፍልሰትን መቀነስ
- ባለሙያዎች በሁለተኛ ድግሪ እንዲሰለጥኑ ማድረግ፣
- ባለሙያዎች፣በመጀመሪያ ድግሪ እንዲሰለጥኑ ማድረግ፣
- ባለሙያዎች በፍትህ አካላት ማሰልጠኛ ማዕከል የቅድመ ስራ ስልጠና እንዲሰለጥኑ ማድረግ፣
- ባለሙያዎች የስራ ላይ ስልጠና እንዲሰለጥኑ ማድረግ፣
- የክህሎት መሙያና ስነ-ምግባር መገንቢያ የስልጠና ሰነዶች ማዘጋጀት፤
ለባለሙያዎች የክህሎት መሙያና ስነ-ምግባር መገንቢያ ስልጠና መስጠት፣
- ለባለሙያዎች ተግባር ተኮር የአፈጻጸም ግምገማ መድረክ ማመቻቸት፤
- በስትራቴጂና በፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ስልጠናዎች መስጠት፣
- ወቅቱንና ጥራቱን የጠበቀ ዕቅድና ሪፖርት ሰነድ ማዘጋጅት
- የክትትልና ግምገማ ስርዓት መዘርጋት
- ወቅታዊና ተኣማኒነት ያለው መረጃ መሰብሰብና ማሰራጨት
- በዕቅድ ዝግጅትና አፈፃፀም ላይ የአፈጻጸም ግምገማ መድረክ ማመቻቸት፣
- የባለድርሻ አካላት በዕቅድና አፈጻጸም ላይ እንዲሳተፉ መድረኮች ማመቻቸት፣
- ለግንባር ቀደም ፈጻሚዎችና ሥራ ሂደቶች ጊዜ ማበረታቻ መስጠት፤
- ምርጥ ተሞክሮዎችን መቀምሮ መተግበር፤
- የውስጥ ኦዲት ቁጥጥርን ማጠናከር፤
- በኦዲት ግኝቶች የማስተካከያ እርምጃ የመውሰድ ምጣኔን ማሳደግ፤
- በኦዲት ግኝቶች ላይ ተጠያቂነት የማረጋገጥ ምጣኔን ማጎልበት፣
- የቋሚና አላቂ ዕቃዎች በወቅቱ የማቅረብ ምጣኔን ማሳደግ፣
- በተቋሙ የሚከናወኑ የፕሮጀክቶች አፈጻጸም ውጤታማነትን ማሳደግ፣
በስነ ምግባር በሙስናና በብልሹ አሰራር ዙሪያ ለስራ ሂደት አመራርና ፈጻሚ የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ መስራት
- ዜጎች በስታንደርድ መሰረት አገልግሎት ስለማግኘታቸው የተገልጋይ እርካታ ዳሰሳ ጥናት ማድረግ
- በተገልጋይ እርካታ ዳሰሳ ጥናት የተለዩ ተቋማዊ ድክመቶችን የማስተካከያ እርምጃ መውሰድ
- የስራ ክፍሎች የባለብዙ ዘርፍ ተግባራት በዕቅድ አካተው እንዲተገብሩ ማድረግ፣
- ለጠበቃ መክፍል አቅም የሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ነጻ የህግ ድጋፍ መስጠት
- የውስጥ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል የአሰራር መመሪያዎች ወይም ማንዋሎችን ማሻሻያ እንዲደረግባቸው አሥተያየት መሥጠት፣
- የቀረቡ የጥቆማና ቅሬታዎችን ተቀብሎ መፍታት
- በሚድያ የሚተላለፉ አስተማሪ የፍርድ ቤት ውሳኔዎች ማስተላለፍ፤
- ዕቅድና ሪፖርቶችን በወቅቱ በዜጎች ቻርተር ውይይት እንዲደረግባቸው መሥራት፤
- የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች ለህብረተሰቡ መረጃ ለመስጠት ጥቅም ላይ ማዋል
- በዕቅድና አፈጻጸም ላይ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ፣
- ለባለድርሻዎች የተደረገ ድጋፍና ክትትል፤
- የሚቀርቡ አስተያየቶች ፣ ጥቆማዎችና ቅሬታዎችን በአግባቡ በማጣራት ፈጣን ምላሽ መስጠት
- የሴክተሩ አገልግሎት አሰጣጥ ከሙስና እና ከብልሹ አሰራር የፀዳ እንዲሆን የተቀመጡ የአሰራር ስርዓቶች ተግባራዊ ስለመደረጋቸው በየሩብ ዓመቱ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ
- ዕለት ተዕለት የሚከሰቱ ሙስናና ብልሹ አሰራር ለመከታተል ያመች ዘንድ የተዘረጉ የቅሬታ አቀባበል እና አፈታት ስርዓቶችን በማጠናከር በቀረቡ ጉዳዮች ላይ ፈጣንና ቀልጣፋ ምላሽ በመስጠት አገልግሎት አሰጣጡን የተሻለ ማድረግ፣
- የሙስናና ብልሹ አሰራር ጉዳዮችን ለመከታተል ያመች ዘንድ በቢሮ የተዘረጉ የአስተያየት ቅሬታ ጥቆማ አሰራሮችን የበለጠ በማጠናከርና ዜጐች አስራሩን በአግባቡ ተገንዝበው እንዲጠቀሙበት ማስቻል፤
- ወረዳችን ሙስናና ብልሹ አሰራር ከመከላከል በተቋሙ ስር-ነቀል ለውጥ ለማምጣት መላው ህዝብን ያሳተፈ ትግል ለማድረግ በዓቃቢያነ ህጐች የሚሰሩ ስራዎች ከአድልኦ በፀዳ ሁኔታ ለትክክለኛ ፍትህ ማዕከል ሆኖ እንዲያገለግል ጠንካራ የፍትህ ልማት ሰራዊት መገንባት ክትትልና ድጋፍ ስራዎችን ማጠናከር፣
- የተመዘበረ የመንግስት ሃብት እና ንብረት እና የወል መሬት ወደ መንግስት እንዲመለሱ ከሌሎች የስነ ምግባር አዉታሮች በመቀናጀት መስራት፣
- በሴቶችና ህጻናት አረጋውያን ፤ በአካል ጉደተኞች እና የኤች አይ ቪ ኤድስ ተጠቂዎች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች የፍርድ ውሳኔዎችን የማስፈጸም አቅም ወደ 100% ማድረስ፣
- በሴቶችና ህጻናት፣ አረጋውያን ፤ የኤች አይ ቪ ኤድስ ተጠቂዎች እና አካል ጉዳተኞች የፍትሐብሔር አቤቱታዎች ላይ የመርታት ምጣኔን 100% የደረሰ
- የኤች አይ ቪ ኤድስ ተጠቂ ማህበረሰቦችን ድጋፍ ማድረግ
- አቅም የሌላቸውን ሴቶችን መደገፍ
- ወላጆቻቸውን ያጡ ሕፃናትን በቋሚነት መደገፍ
- የተግባር አፈጻጸምን በቲም ውይይቶች አጠናክሮ ማስቀጠል፤
- የማኔጅመንት አደረጃጃቱን ማጠናከር፤
- ከዕዳና ኦዲት ጉድለቶች ላይ የተደራጁ አደረጃጀቶችን ውጤታማ እንዲሆን ማድረግ
- የተቋሙን የዜጎች ቻርተር ውይይትን ማጠናከር፣
- በተቋሙ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መለየት፤
- በተቋሙ የተለዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እንዲፈቱ ማድረግ፣
- በተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶች እና አሰራሮችን ለተገልጋዮች ግልጽ የማድረግ ስራን አጠናክሮ ማስቀጠል፤
- የጥቅም ግንኙነት በመፍጠር ፍትህ በሚያዛቡት ላይ አስተማሪ እርምጃ መውሰድ
- ከየቀበሌው በሕገ ወጥ መንገድ የተያዙ የወል መሬት እና የከተማ መሬቶች መረጃዎች እንዲቀርቡ ማድረግ እና ውሳኔ እንዲሰጥባቸው ማድረግ
- ከፖሊስ ጋር በጋራ ሊጣሩ በሚገቡ የወንጀል ጉዳዮች ምርመራ ምጣኔ ወደ ማድረስ፣
- ምመራቸው የተጠናቀቁ መዛግብትን ተቀብሎ ሕጋዊ ውሳኔዎችነና አሥተያየቶችን መሥጠት፤
- በቀላል መካከለኛና ከባድ የወንጀል መዛግብት ላይ ክስ አዘጋጅቶ ፍርድ ቤትፋይል ማስከፈት፤
- በሕዝብና በመንግሥት ጥቅም ላይ የሚደርሱ ወንጀሎችን ለይቶ ትኩረት ሠጥቶ በሙሉ ሃይል መሥራት፤
- ከፖሊስ ጋር በጋራ ሊጣሩ በሚገቡ የወንጀል ጉዳዮች ምርመራ ምጣኔ ወደ 99% ማድረስ፣
- በዕርቅ ማለቅ የሚገባቸው ቀላል የወንጀል መዝገቦች 95% ማድረስ፣
- የፍርድ ቤት ውሳኔዎችን የማስፈጸም አቅም 95% ማሳደግ፣
- በጠቋሚዎችና በምስክሮች የሚቀርቡ የከለላ ጥያቄዎች ምላሽ የመስጠት ምጣኔን ወደ 90% ማሳደግ፣
- በውል ክፍተት የሚከሠቱ ክርክሮችን ወደ ዝቅ ማድረግ፣
- መንግስት ከሳሽ በሆነበት ፍትሐ-ብሔር ጉዳዮች የመርታት ምጣኔን ማሳደግ፣
- መንግስት ተከሳሽ በሆነበት የፍትሐ-ብሔር ጉዳዮች የመርታት ምጣኔ ማሳደግ፣
- የፍትሐ-ብሔር ጉዳዮች የተሰጠ የሕግ ምክር ሽፋን ምጣኔ ማሳደግ፣
- ከሚወረሩ የወል መሬቶች ላይ በዓመቱ በክስና በድርድር ተመላሽ ማድረግ፤
- ከሚወረሩ የከተማ መሬቶች ላይ ተመላሽ ማድረ
- የፀረ-ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ግብረ-ኃይል የዕቅድና ሪፖርት ግምገማ ማድረግና ግብረ-መልስ መስጠት፣
- ከሕገ-ወጥ የሠዎች ዝውውር ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ የወንጀልና የፍትሐ-ብሔር መዛግብት ለይ ውጤታማ ማድረግ፤
- በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ቁጥጥርና መከላከል ዙሪያ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግና ለማዳበር የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በማስተባበር ግንዛቤ መፍጠር፣
የሕገ-ወጥ ሰዎች ዝውውር ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል የተጋላጭነት ሁኔታ ከቦታ፣ ከተጎጂዎችና ከአዘዋዋሪዎች አንጻር ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ መሥራት፣
- ማነኛውም የወረዳችን ነዋሪ ላይ ለሚነሱ የሰብዓዊ መብት ጥያቄዎችን ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን እንዲፈቱ ማድረግ፤
- ከሰብዓዊ መብት አያያዝ ጋር ተያይዞ ማረፊያና ማረሚያ ተቋምን በየቀኑና በየወሩ ድጋፍ ማድረግ መገምገምና በቃልና በጽሁፍ ግብረ-መልስ መስጠት፣
- በሰብዓዊ መብት አያያዝ ጋር ተያይዞ ማረፊያና ማረሚያ ተቋምን ድጋፍ ማድረግ እና የሕግ ግንዛቤ ማስጨበጫ ዕድሎችን መፍጠር፣
- የተጠርጣሪዎችና የታራሚዎችን መብት የሚጥስን አካል ላይ ሕጋዊና አሥተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድበት ማድረግ፤
- በተመረጡ የሕግ ጉዳዮች ላይ ጥናት ማድረግና ለሚመለከተው አካል የውሣኔ ሃሳብ ማቅረብ፣
- ለሕብረተሰቡ የንቃተ ሕግ ለመስጠት የሚያስችል የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ማድረግ፣
- የሕግ ግንዛቤ ማስጨበጫ ክበባትን በየትምህርት ቤቱ ማቋቋም እና የልተቋረጠ ድጋፍ ማድረግ፤
- ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚሰጡ የንቃተ ሕግ ግንዛቤ መስጫ ማንዋሎችን ማዘጋጀት፣
- የተለያዩ የማስተማሪያ ዘዴዎችን የንቃተ ሕግ ግንዛቤ ትምህርት መስጠት፣
- የሕጎችን መሠብሠብና የተሰበሰቡ ሕጎች በተቋሙ ድህረ-ገጽ በመልቀቅ ለሕብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ፤
- ጠበቆችና የሕግ ጉዳይ ጸሐፊዎች በሚሰጡት የጥብቅና አገልግሎት ላይ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ፣
- በጠበቆችና የሕግ ጉዳይ ጸሐፊዎች ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን 100% በዐቃቤ ሕግ ውሳኔ ማሰጠት፣
- እንደ ወረዳ ገቢ የቴምብር ሽያጭ አገልግሎትና ተገልጋዮችም በቅርበት አገልግሎት እንዲያገኙ መሥራት፤
- የሲቪል ማህበራት ለተቋቋሙበት ዓላማ ስለመንቀሳቀሳቸው ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣
- የሠነዶች ማረጋገጥና ምዝገባ አገልግሎትን በሕጉ መሰረት ማከናወን፣
- የሲቪል ማህበራት ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን በጊዜ ገደቡ አጣርቶ በሚሠጡን ውክልናና ሥልጣን መሠረት ምላሽ መስጠት፣
- ለጠበቃ የመክፈል አቅም ለሌላቸው ሴቶች ፣ ሕጻናት ፣ አካል ጉዳተኞች ፤ ለአረጋውያን እና የኤች አይ ቪ ኤድስ ተጠቂ ነጻ የጥብቅና አገልግሎት 100% እንዲያገኙ ማድረግ፣
- የሥነ-ምግባር ጉድለት በሚያሳዩ ጠበቆችና የህግ ጉዳይ ጸሐፊዎች ላይ የሚቀርቡ ክሶችን በድስፕሊን ጉባኤ 100% ውሳኔ መስጠት፣
- የጉምሩክ ጉዳዮች የሚታዩት በፌደራል ወይም በክልል ደረጃ የሚታዩ ሲሆን በስራ ሂደቱ የሚሸፈን በመሆኑና ጉዳዩ ሲያጋጥም ለሚመለከታቸው ማሳወቅ
- የታክስ ሕጎችን (የታክስ አስተዳደር አዋጅ ፣ የገቢ ግብር ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ፣ ኤክሳይስ ታክስ ፣ ተርን ኦቨር ታክስና በሌሎች የታክስ ሕጎች የተጠቀሱት ወንጀሎች) መዛግብትን ተንቀሳቅሶ መሥራት መቻል፤
- ከታክስ ኦዲት ጉድለት ላይ በተፈጸሙ ወንጀል ጉዳዮችን ማጠናከርና በፍትሐ-ብሔር ዕዳውን የማስመለስ ሥራን መሥራት
|
- የንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃን የሚመለከቱ ወንጀሎች ላይ ተገቢውን የሕግ ቁጥጥርና ክትትል ማድረግ፤
- እንደ ተቋማችን ቴሌ-ግራምና ፌስቡክ እንዲሁም የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች ለሕብረተሰቡ መረጃ ለመስጠት ጥቅም ላይ ማዋል፣
- የስራ ክፍሎች የባለብዙ ዘርፍ ተግባራት በዕቅድ አካተው እንዲተገብሩ ማድረግ፣
- የውስጥ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል የአሰራር መመሪያዎች ወይም ማንዋሎችን ለማሻሻል አዲስ ለማዘጋጀት አሥተያየት መሥጠት፤
- የቅሬታ ማቅረቢያ ስርዓትን ምጣኔን ቀላልና የሚፈጸም ሥርዓት መዘርጋት እና ወደ 100% ማሳደግ፤
- በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ የቀረቡ አቤቱታዎችና ቅሬታዎች በውስጥ አሠራራችን በኩል ምላሽ መስጠት፣
- የውስጥ መረጃ አያያዛችንን በቴክኖሎጂ የታገዘና ለተገልጋይ ግልጽና ምቹ እንዲሆን መሥራት፤
- የተቋሙን መረጃዎች ደህንነት መጠበቂያ የሚሆን ማደራጀት፣
- ወቅታዊና ተዓማኒነት ያለው መረጃ መሰብሰብና ማሰራጨት፣
- በተቋሙ አዲስ የመረጃ ቋት ማልማት፣
- በተዘጋጀው የመረጃ ቋት መረጃዎችን 100% ማስገባት፣
- የተቋሙን መረጃ ደህንነት የማስተዳደር ስራ 100% ማከናወን፣
- በተቋሙ ዲጂታላይዝድ የሚሆን መረጃ 100% መሰብሰብ፣
- ዲጂታላይዝድ የሚሆን 100% የተሟላ መሰረተ ልማት መዘርጋት፣
- የተቋሙን ደህንነት መጠበቂያ የሚሆን መረጃ 100% ማደራጀት፣
- የውስጥ ኦዲት ቁጥጥርን ማጠናከር፤
- የቋሚና አላቂ ዕቃዎች በወቅቱ የማቅረብ ምጣኔን ማሳደግ፣
- በተቋማት ኦዲት ግኝቶች የማስተካከያ እርምጃ የመውሰድ ምጣኔን ወደ 100% ማሳደግ፤
የበጀት አጠቃቀም ምጣኔን ወደ 99% ማሳደግ፤
- ከፖሊስ ጋር ያለውን የሁለትዮሽ የቅንጅታዊ አሰራር ስለመተግበሩ የውይይት መድረኮችን ማመቻቸት፤
- ከፖሊስና ከፍ/ቤት ጋር ያለውን የሶስትዮሽ የቅንጅታዊ አሰራር ችግር ፈቺ በሆነ መንገድ ስለመተግበሩ ውይይት ማድረግ፤
- ከአሥተዳደር ፤ ምክር ቤት እንዲሁም ከአበዳሪ ተቋማት ጋር ውይይት ማድረግ፤
- ሴቶችና ሕጻናት ፍትሕ ፎረም ፤ የዜጎች ቻርተርና የሕዝብ ክንፍ ውይይቶችን ውይይት ማድረግ፤
- የመግባቢያ ሰነድ ከተፈራረሙ ባለድርሻ አካላት ጋር የተደረጉ በተቀመጠላቸው ጊዜ መሠረት መድረኮችን ማመቻቸት፤
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ፍትሕ ጽ/ቤት አጠቃላይ ገላጭ መረጃ
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ፍትሕ ጽ/ቤት ከመጋቢት ወር 2011 ዓ/ም ጀምሮ ከነባሩ ሶዶ ወረዳ ለሕዝብ ተጠቃሚነት አዲስ መዋቅር ሆኖ በወጣው ደቡብ ሶዶ ወረዳ ውስጥ እንደወረዳው ሌሎች የመንግሥት ተቋማት እኩል ሥራዎችን እየሠራ ሲገኝ የተቋማችን መቀመጫ የወረዳው ዋና ከተማ በሆነው ኬላ ከተማ ውስጥ ከኬላ ቱሉቦሎ በሚወስደው ዋና መንገድ በሥተግራ በኩል ይገኛል፡፡ተቋማችን እንደሌሎች መዋቅሮች በተለመደ መልኩ ከወረዳችን ፍርድ ቤት ጋር በአንድ ግቢ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በርካታ የፍትሕ ጥያቄዎች ላይ በተቋምና ከተቋምም ውጪ እየተንቀሳቀሰ አገልግሎት እየሰጠም ይገኛል፡፡የደቡብ ሶዶ ወረዳ ፍትሕ ጽ/ቤት በበርካታ ችግሮች ውስጥም ሆኖ የማሕበረሰቡን ችግር በፍትሕ ጉዳይ እየፈታ ይገኛል፡፡ተቋሙ እንደ መዋቅሩ አዲስነት ጋር ተያይዞ የራሱ ቢሮ ባይኖረውም የወረዳው መንግሥት በፈጠረው የመፍትሔ መንገድ እስከዛሬ ድረስ በኪራይ ቤት ውስጥ ተቋማዊ ተልዕኮውን እያሳካ የሚገኝ ነው፡፡በዚህን ወቅት እንደተቋም 9 ዓ/ሕግና 7 ድጋፍ ሰጪ በድምሩ 16 ባለሙያዎችን ይዞ ተቋም መሥርቶ አገልግሎት እየሠጠ ይገኛል፡፡የባለሙያዎቻችን የጾታ ሥብጥር 7 ወንድና 9 ሴቶች ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥ 8 የማኔጅመንት አባል አለን፡፡ተቋማዊ አደረጃጀቶችን እና ሌሎች ውጫዊ አደረጃጀቶችን እየተጠቀምን ተግባራትን እያቀላጠፍን ማሕበረሰባችንን እያሥጠቀምንና እያገለገልን እንገኛለን፡፡በተቋም ደረጃ የማኔጅመንት ፤ የቲም ፤ የቲም በማኔጅመንት ፤ የቴክኒክ እና ሌሎች መሠል የተግባራት መፈጸሚያ አደረጃጀቶች ሲኖሩን ከተቋም ውጪ ከወረዳው ፍርድ ቤት ፤ አሥተዳደር ፤ ምክር ቤት ፤ ሕብረት ሥራና ኦሞ ተቋማት ጋር ወቅታዊ ውይይቶችን እያደረገ ጠንካራ ተቋም ለመገንባት ተሞክሯል፡፡
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ መልዕክት
የደቡብ ሶዶ ወረዳ ፍትሕ ጽ/ቤት ከመጋቢት ወር 2011 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ሥራ የገባ ሲሆን እንደ ተቋም ከፌደራል የአስፈጻሚ አካላት ሥልጣንና ኃላፊነት ለመወሰን በወጣውአዋጅ ቁጥር 1263/2014 አንቀጽ 40 መሠረት በወጣው የፌደራል የጠቅላይ ዓ/ሕግ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 943/2008ና የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት የጠቅላይ ዓ/ሕግ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 177/2011 እና ማስፈጸሚያ ደንቦቻቸው ላይ በተሠጡት ተግባርና ሃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል፡፡የፌደራል ፍትሕ ሚኒስቴርና የፌደራል መንግሥት ልዩ ትኩረት ሠጥተው ከሚሰሩባቸው መንግስታዊ ተቋማት መካከል የፍትሕ ተቋም አንዱ ነው፡፡ ለዚህም ሲባል በክልላችን ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፍትሕ ቢሮ በኩል በተደረገው የተዋረዳዊ የፍትሕ ተቋማት አጠቃላይ ተሃድሶ ሥራ ላይ በቅርቡ በዚሁ ባሳለፍነው 2016 ዓ/ም አጋማሽ የሥራ ዘመን ላይ ንቅናቄ መፍጠሩን ተከትሎ በምሥራቅ ጉራጌ ዞን ፍትሕ መምሪያ በመጋቢት ወር 2016 ዓ/ም ዞናዊ የሪፎርም ሥራውን ወደ ተግባር ለመቀየር የጋራ መድረኩን አድርጎ ለወረዳዎች ተልዕኮ ሰጥቷል፡፡ በዚህም መሠረት እንደ ወረዳ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ ተቋማት ጋር ባደረግነው የጋራ መግባባትና ባገኘነውም የቢሻሻሉ አስተያየቶችን በተገቢው መንገድ ወስደን ከትላንት በተሻለ ሁኔታ በቁርጠኝነት ተቋማዊ ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባናል በማለት ተግባቦት ላይ በደረስንበት መልኩ መሥራትና የፍትሕን ጥያቄ በተገቢው ለመመለስ እንዳለን፡፡
በወረዳችን ውስጥ ባሉ ሁሉም ቀበሌዎች ላይ የሕግ ግንዛቤ እየተፈጠረባቸው ነዋሪዎቻችን ላይ ከሚፈጠሩ የወንጀል ድርጊቶች ለመከላከል ከወረዳው ባለድርሻ ተቋማት ጋር በጋራ እየሰራን መልካም ውጤቶችን እያስመዘገብን ይገኛል፡፡ እንደ ወረዳችን ማሕበረሰብ የሕግ ግንዛቤ አንፃር ዕጥረቱ ባይኖረም በርካታ ወንጀሎች ግን እየተፈፀሙ ተገቢውን እርምጃ እየወሰድን መጥተናል፡፡ ከቀላል ስርቆት እስከ ከባድ ስርቆት ፣ ከመሸሸግ እስከ ከባድ ዕምንት ማጉደል ፣ ከቀላል አ/ጉ/ማ እስከ ግድያ የሚደርሱ ወንጀሎች ፤ በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ጨምሮ የሚፈፀምበትን ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ እንዲመጣና ማሕበረሰባችንን ከሥጋት መታደግ በሚቻል መልኩ እየተሰራ ይገኛል፡፡እንደ ወረዳችንና እንደ ከተማችን የንግድ ማዕከልነት በሕራይ አንፃርም በተደጋጋሚ የሚፈፀሙ ከንግድ እንቅስቃሴ ጋር የተያያዙ ወንጀሎች ማለትም የሐሰተኛ ገንዘብ ማዘዋወር ፤ ሕገ-ወጥ የንግድ ዕቃ ዝውውር ፤ የነዳጅና የደን ውጤቶች ዝውውር ላይ ከነበረበት አፈጻጸም ለመቀነስ የቻልነው ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት በመቻላችን ነው፡፡ ሌላው በቸልተኝነት የተሸከርካሪ ግጭቶች ጋር ተያይዞ በንብረት በአካልና በሕይወት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ከነበሩበት ደረጃ መቀነስ በተሰጡ የሕግ ግንዛቤና ቅንጅታዊ ሥራ መነሻ በማድረግ የሠራናቸው ሥራዎች ውጤት ናቸው፡፡ በቅርቡ በተለይም አሁን ካለው የሃገራችን የፖለቲካ ሁኔታችን አንፃር ብቅ ብቅ ከሚሉ በኮምፒውተርና በድረገጾችና በመገናኛ ብዙሃን አማካይነት እየተፈጸሙ የተሳሳተ መረጃና የጥላቻ ንግግር ወንጀሎች ላይ እየታዩ ያሉ ሲሆን እዚህ ላይ እንደ ተቋማችን ትኩረት ሰጥተን የምንሰራበት ቢሆንም በሚለቀቁ መረጃዎች ላይ ተገቢውን ጥንቃቄ ወስዶ ከተጠያቂነት መዳን እንደሚገባው በዚህ አጋጣሚ ለማሳሰብ እወዳለሁ፡፡
የፍትሕ ጉዳይ የሁሉም ነገር ማሰሪያ ነው ፍትሕ ከሰፈነ ሠላም ይኖራል የሕግ የበላይነትና የመልካም አስተዳደር መስፈን ይችላል፡፡ ማሕበረሰብ ወደ ተፈለገው የልማት እንቅስቃሴዎች ውስጥ ገብቶ ኢኮኖሚውን መቋቋምና ማገዝ ይችላልና እንደተቋም የተቋቋመለት መሰረታዊ ዓላማ ለማሳካት ከፍ ብሎ አስቦና አቅዶ ወደ ተግባር ገብቶ መስራት ይኖርብናል፡፡ ሌላው የፍትሕ ጥያቄ የግለሰቦችንና የሰው ሰራሽ ሰዎችን መብትና ግዴታን አውቆ መከባበርን መቻቻልን ፣ መረዳዳትንና ለሕግ አጋዥ መሆንን ያካተተ ተግባር ፈፅሞ በተግባር ማሳየት ነው፡፡ ይህ ሲባል በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን መቆጣጠርና ከመፈፀማቸው በፊት መከላከል ከተፈፀሙም በኃላ በቶሎ ተበዳዮችን መካስ የሚቻልበት ሁኔታ ፈጥሮ አጥፊዎችን ለሕግ አሳልፎ መስጠትን ያካተተ ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ግለሰቦች መብታቸውን እንዲያስከብሩ ግዴታቸውን ሲወጡና ይህንን በተግባር ሲያሳዩ ፣ የተበደሉ ሰዎችን ለመካስ መረጃዎችን ከፍ አድርጎ ማስረጃዎችን ከመስጠትና ማስረጃ መሆን ድረስ ሥራን ማገዝ ሲቻልና መሠል እውነታዋችን መፈፀም እንዲቻል ከተቋማዊ ተልዕኮዎቻችን ጋር አስተሳስረን የምንሰራበት ሁኔታ መፍጠር አለብን፡፡
የፍትሕ ጥያቄን ከፍ አድርጎ የሚያሳይበትና እንደተቋምም እንደሙያም ለመስራት አቅደን እየተንቃሳቀስን በትና ውጤትም እያመጣንበት የሚገኘውን አንዱ የሙስናና ብልሹ የአስራር ሥራዎችን ላይ የምንሰራው ነው፡፡ ሙስና የሃገርን ልማት የሚያጓትት ፣ ጥቂቶች ለጊዜያዊ ደስታ አጋልጦ የሕሊና ሸክም አንዲበዛባቸው የሚያደርግ ፣ ታታሪዎችን የስነ-ልቦና ወድቀት እንዲደረስባቸውና ሰነፎችን ባልተገባና በተሳሳተ መልኩ የሚሽልም ከሰነፍናቸው ሳይወጡ ነጋቸውን የሚያጨልም ፣ በራስ መተማመንን የሚወስድና የእርስ በርስ ጥርጣሬ ፈጥሮ በአንድነት እንዳይቆሙ የሚደርግ የስግብግቦችና የራስ ወዳዶች መገለጫ እኩይና ነውር የሆነ ተግባር ነው፡፡ከዚህ ጋር ተያየዞ እንደ ሃገር በርካታ ልማቶች በወቅቱ እንዳይፈጸሙ ሲያደርግ የቆየ ቢሆንም እንደወረዳችን የተሻሉ ነገሮች እንዲፈጠሩና የማሕበረሰቡ ስለሙስና ያለውን ግንዛቤ አሳድገን ተቋማዊ ተልዕኮዎቻችንን ከፍ አድርገን ማሳየት ይጠበቅብናል፡፡ ለዚህም ከሚመለከታቸው ባለድርሻዎቻችን ጋር እንደጉዳዮቹ ክብደትና የማሕበረሰባዊ ጉዳታቸውን እየለየን ተግባራትን እየፈፀምን የምንሄድ መሆን አለበት፡፡
ከሙስና ጋር ተያይዞ ትኩረት የሚያሻቸው ከአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍና ጋር ተያይዘው በገጠርም ይሁን በከተማ ከመሬት አስተዳደር ሥራዎቻችን ፤ በፍትሕ መስጫ ተቋማት ከቀበሌ ሚሊሻ ጀምሮ እስከ ወረዳ ፍ/ቤታችን ድረስ ከፖሊስና ዓ/ሕግ አገልግሎቶቻችን ከተገልጋዮች ፍላጎትና ከባለሙያዎች አቅምና የአገልግሎት ሠጪነት አመለካከት ተደምሮ ተጋላጭነታቸው ታይቶ የዕለት ተለት ሥራዎች ላይ የማሕበረሰባችን የቀድሞ ግምት የአመለካከት ለውጥ ፈጥረን በሕግ አግባብ መንቀሳቀስ እንደሚገባን አምነን እየሰራን እንገኛለን፡፡ ሌላው እንደ ኦዲት ግኝት የወንጀልና የፍትሐ-ብሔር ጉዳዮች ጋር ተያይዞ ልዩ ትኩረት እየሰጠን ተግባራትን እያቀላጠፍን መሄዳችን ይታወቃል፡፡በአጠቃላይ የደቡብ ሶዶ ወረዳ ማሕበረሰብ ያለውን አንፃራዊ የሰላም ሁኔታ ፤ የመልማት ዕድሎችና ፍላጎቶችን በማገናዘብ ይህንን የማሕበራዊ ፣ የኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሁለተናዊ ልማት ዕድገቱን እያገዝንና ፍትሕንና መልካም አስተዳደርን በማስፈን ረገድ የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ተግተን እየሰራን ቢሆንም በተለይ ከሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርና ከሴቶችና ሕጻናት እንዲሁም ልዩ ትኩረት ከሚሰጣቸው የማሕበረሰብ ክፍሎቻችንን ከማገዝና ልዩ የሕግ ድጋፍ ከማድረግ አንጻር አሁን ካለንብት ከፍ አድርገን ለመስራት ወጣቱ ፣ የሃገር ሽማግሌውና ፍትሕ እንዲሰፍንና ሕግ እንዲከበር የሚመለከተው ሁሉም ከተቋማችን ጎን ሆኖ ሠላማዊና የሕግ የበላይነት የሚከበርበት ወረዳን እንፍጠር እላለሁ፡፡
አመሠግናለሁ!!!
Phone Number
Phone Number
046-322-80-85
Phone Number
046-464-0468