የሙሽሮች ወግ፤ ማዕረግ በክስታኔ ጉራጌ(ጠፍር)
በክስታኔ ቤተ-ጉራጌና አካባቢው ባሕል ሙሽሮች የሠርግ ወቅታቸው ሲቃረብ ወግ፤ ማዕረግ መቀበልና መስጠት ይጀምራሉ። ከነዚህ ስር-ሰደድ ባሕላዊ ኹነቶች መካከል አንዱ ”ጠፍር” ይባላል በክሥታኒኛ። ሙሽሮቹ ወደ ቤተሰብ ተጠርተው የተለየ እንክብካቤ፣ ክብርና ፍቅር የሚያገኙበት ክዋኔ አዘል ባሕላዊ ሥርዓት ነው-ጠፍር። ”ጠፍር” የሚለውን ቃል አመጣጥ በድሮው ባሕል ተመስርተን ስንመለከት በተለይ ሴቷ ሙሽራ በዘልማድ ከእናቷ ጎን የማትጠፋ በመሆኑ ”ጥፍሯን ካልተቆረጠች በቀር ሥራ አታቆምም” በሚል የተጀመረ እንደሆነ አፈታሪክ ያስረዳል። ምንም እንኳ አንዳንዴ ተጨማሪ ወይም የተለየ የተቃራኒ ፆታ ግንኙነት ምክንያት ቢቀመጥለትም!
”ሴቷ ጥፍሯን ካልተቆረጠች ያገኘችውን እቃ የማንሳትና ሥራ የመስራት አጋጣሚ ስለሚኖራት የሙሽርነት ውበቷ ፍክት ብሎ እንዳይወጣ ያደርጋል” የሚል እምነት ተይዞም ነበር ሥነ-ሥርዓቱ የሚከናወነው። ስለዚህም ሙሽሪት ጥፍሯ ተቆርጦ ቤት ቁጭ ብላ እና ሚዜዎቿን ይዛ ቤተሰብ ጋር እየተዟዟረች ራሷን እንድትጠብቅ ይደረጋል። ታዲያ በደንብ ትለብሳለች። ታጌጣለች። ታምራለች። ባለጊዜ ናትና!ይህ ባሕል ከጥንት ጀምሮ ከህዝቡ ጋር አብሮ የመጣ ነው። ጥፍር የመቁረጡ ነገር አሁን ቀርቷል።

ሥነ-ሥርዓቱ በጠቃሚ ጎኑ እንዳይቀጥል ”ዘመናዊው ዘመን” ደግሞ አጥልቶበታል። ይህንን በመታገል አንድ አካባቢ ከማህበራዊ ባሕል ሊያገኝ የሚችለውን ትርፍ ማስጠበቅ ያስፈልጋል።ሶሳዬ…Sosina Daniel Sosina ከተወዳጅና ተናፋቂው የእናትና አባቶቻችን ባሕል የ”ጠፍር” ሥነ-ሥርዓት እንድናዘጋጅልሽ ምክንያት ስለሆንሽን ደስ ተሰኝተናል።#ማለሲ የጌሚትዲ ቁጢሱ ቡሩም ንዎድሹ! #ጠፍሪ ያለም ጠፍር ያዱኛ ዬቀናልሽ! ያበላሺነኾም ፈያቃይ እንበላሽ ንቤር! ኧዳር፤ ቢተንደሽ ዬጫም!